Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የቤኔዲክቶስ 16ኛ ስንብት፡ ‘በጌታ የወይን እርሻ ቦታ ትሑት ሠራተኛ’ ነበሩ!

የቤኔዲክቶስ 16ኛ ስንብት፡ ‘በጌታ የወይን እርሻ ቦታ ትሑት ሠራተኛ’ ነበሩ!
Benedict 16 deathየ95 ዓመቱ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ቤኔዲክቶስ 16ኛ ቅዳሜ ታኅሳስ 22 ከቀኑ 05፡34 ላይ በቫቲካን ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመኖሪያ ቤታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገለጸ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ ወደ ዘላለማዊ የመኖሪያ ቤታቸው የተመለሱ ሲሆን የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ክፍል ባወጣው መግለጫ እንደ ገለጸው ከሆነ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ እ.አ.አ በ2013 ዓ.ም በገዛ ፈቃዳቸው የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስናቸውን አገልግሎት በመልቀቅ በቫቲካን ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የቤተክርስቲያን እናት በተሰኘው ገዳም ውስጥ መኖር ጀምረው የነበረ ሲሆን በ95 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

“ርእሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ከቀኑ 05፡34 ላይ በቫቲካን በሚገኘው የቤተክርስቲያን እናት ገዳም ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን በሀዘን አሳውቃችኋለሁ። ተጨማሪ መረጃ በተቻለ ፍጥነት ይቀርባል። ምእመናን ለእርሳቸው ያላቸውን አክብሮ እንዲገልጹ እና እንዲጸልዩላቸው ከሰኞ ጥዋት ታኅሣሥ 24/2015 ዓ..ም ጀምሮ፣ የጳጳሱ አስክሬን በቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሆናል” ሲል የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ተቋም በመግለጫው ገልጿል።

እየተባባሰ የመጣ የጤና ሁኔታ ዜና

የፕሬስ ጽ / ቤቱ ስለ ሁኔታውን በተመለከተ እንደዘገበው ለብዙ ቀናት የጳጳሱ የጤና ሁኔታ በእድሜ መግፋት ምክንያት ተባብሷል በማለት በተከታታይ መግለጫ ማውጣቱ የሚታወስ ሲሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እራሳቸው በዓመቱ የመጨረሻ የጠቃላላ አስተምህሮ መጨረሻ ላይ ታኅሣሥ19/2015 ዓ..ም ስለ ቀድሞው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የጤና ሁኔታ መባባስ ዜናውን በይፋ አካፍለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጌታ እንዲያጽናናቸው እና እንዲደግፋቸው "እስከ መጨረሻው በዚህ የቤተክርስቲያኑ ፍቅር ምስክርነት እንዲጸኑ" እንዲጸልዩ ምዕመናን በሙል እንዲጸልዩ መጋበዛቸው ይታወሳል።

ይህንን ግብዣ ተከትሎ በሁሉም አህጉራት የፀሎት ተግባራት ተጀምረው የነበረ ሲሆን ከተለያዩ የዓለማችን አገራት የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክቶች መጉረፋቸው ይታወሳል።

የቀብር ሥነ ስረዓት እቅዶች

በቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት ገለጻ ላይ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ የቀብር ሥነ ሥርዓት እ.አ.አ በታኅሥሥ 27/2015 ዓ.ም በ5፡30 ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በሚደርገው የፍትኅት ጸሎት እንደ ሚከናወን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ዳይሬክተሩ ማትዮ ብሩኒ ተናግረዋል። በቅዳሴ ላይ ለመሳተፍ ምንም ዓይነት የመግቢያ ቲኬቶች እንደ ማያስፈልጉ ከወዲሁ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ቫቲካን ሬድዮ ድረ ገጽ

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።