Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ዜናዎች

አበምኔት አግኝተናል!

እንኳን ደስ አለን!

"እንደ ልቤም እረኞችን እሰጣችኋለሁ፤ በእውቀት እና በማስተዋልም ይጠብቋችኋል" (ኤር 3፡15)

20220910125216በኢትዮጵያ የሲታውያን መነኮሳን  በመጋቢት 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረጉት ጠቅላይ ጉባዔ ክቡር አባ ዳንኤል ጌታቸው በኢትዮጵያ የሲታውያን ማኅበር አበምኔት ሆነው ተመርጠዋል። በዚህም ኃላፊነታቸው ክቡር አበምኔት አባ ዳንኤል ጌታቸው በኢትዮጵያ የሲታውያን መነኮሳን መምህረ ገዳም በመሆን ለሚቀትሉት ስድስት ዓመታት ገዳሙን ያስተዳድራሉ። ለክቡር አበምኔት አባ ዳንኤል ጌታቸው የአገልግሎት ዘመን መሳካት በጸሎት እየበረታን ለክቡር አበምኔት አባ ዳንኤል ጌታቸው መልካም የአገልግሎት ዘመን እንመኛለን!

በኢትዮጵያ የሲታውያን ገዳም  ደረ ገጽ አዘጋጅ ኮሚቴ 

"I shall give you shepherds after my own heart, who will pasture you wisely and discreetly" (Jer 3, 15)

On March 6, 2023, the General Chapter of the Cistercian Order in Ethiopia elected Rev. Fr. Daniel Getachew as Abbot General of the Cistercian Order in Ethiopia.
We pray for his ministry and give thanks to God.

Ethiocist web team

 

Write comment (1 Comment)

ፈረንሳይ ውስጥ አንድ ካህን በቅዳሴ ላይ ሳሉ በአይኤስ ተገደሉ

Martyr Catholic Priest86 ዓመት እድሜያቸውም ቢሆን አገልግሎታቸው ቀጥሏል፤ መሆን ያለበትን ነገር ሁሉ በትክክል ማከናወናቸውንና የክህነት አገልግሎታቸውን ማለትም ሕፃናትን ማጥመቅ፤ መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረግ የቁምስና ምእመናንን በሌሎች ምስጢራት ማገልገል ብዙ የሕይወት ጊዜያቸውን ባሳለፉባት ኖርማንዲ ከተማ እየቀጠሉ ነበር። “75ዓመት በሞላቸው ጊዜ ከቆሞስነት አገልግሎት መገለል ይችሉ ነበር ግን የካህናት እጥረት መኖሩን ስላወቁ በዚህ ሁኔታ ምድራዊው ሕይወታቸው በአሳዛኝ ሁኔታ እስከተደመደመባት እለት ምእመናንን ማገልገል መረጡ” ይላሉ አባ ሐሜል እንደ ረዳት ቆሞስ ያገለገሉባት ቁምስና ዋና ቆሞስ ካህን። ቆሞሱ አክለው ሲናገሩ “አባ ሐሜል ሁላችንም የምንወዳቸውና የአያትነትን አብሮነት የሚያሳድሩ ነበሩ፤ እርሳቸው አብረውን ሲሆኑ ደስ ይለን እንዲሁም በሆነ ነገር ከኛ ጋር ከሌሉ ደግሞ ይሰማን ነበር” ብለዋል።

አባ ጃክ ሐሜል ትላንት ማክሰኞ ሐምሌ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ጠዋት በቅዳሴ ላይ ሳሉ ነበር ሁለት ግለሰቦች ጩቤ ይዘው በመግባት የአባን ጉሮሮ የቆረጡት፡ ይህም ዜና ለፈረንሳይንና ለመላው ዓለም ዘግናኝ ሆነ። እስላማዊ መንግሥት ብሎ ራሱን የሚጠራው ቡድን /አይኤስ/ ይህን ጭካኔ የተሞላ ዜና ተከትሎ እነዚህ ሁለት ወንጀለኛ ግለሰቦች የእርሱ ወታደሮች መሆናቸውን ገልጧል። ይህን ድርጊት ሲያድርጉ ከአባ ጃክ ሐሜል ጋር አራት ሌሎች ሰዎችን አግተው እንደነበርና ከነርሱም አንዳቸው ከበድ ያለ ጉዳት እንደደረሰባችው ተዘግቧል። የፈረንሳይ ፖሊሶች በቦታው ተገኝተው በከፈቱት ተኩስ ይህን ወንጀል የፈጸሙት ግለሰቦች መገደላቸው ታውቋል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ይህን ድርጊት ሲያወግዙ፤ የተለያዩ የፈረንሳይ ባለሥልጣናት የድርጊቱን አሳዛኝነትና የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸዋል። የቦታው ሊቀ ጳጳስም ይህ ድርጊት የተፈጸመበት ቁምስና ምእመናንን ለማጽናናት በፖላንድ ክራኮቭ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የካቶሊካውያን ወጣቶች ትልቅ ስብሰባን በማቋረጥ ወደ ካቴድራላቸው ተመልሰዋል።  

አባ ጃክ ሐሜል መስዋዕተ ቅዳሴ እያሳረጉ ሳሉ የተገደሉበት ሁኔታ በ1980 ዓ.ም. እኤአ ብዙዎች በጊዜው እሳቸው የሚያስተምሩትን የወንጌል ትምህርት ይቃወሙ የነበሩ ታጣቂዎች በተመሳሳይ ሁኔታ በቅዳሴ ጊዜ ተኩሰው የገደሏቸውነ የኤልሳቫዶር ሊቀ ጳጳስ የነበሩትን ኦስካር ሮሜሮን አስታውሰዋል። በየማሕበራዊ ገጾችም “እኔም ካህን ነኝ”፤ “እኔም ካቶሊክ ነኝ”፤ እንዲሁም “እኔም ክርስቲያን ነኝ” የሚሉ አጫጭር መፈክሮች እንደ ማንነት መገለጫ በመጠቀም ላይ ይገኛሉ። አንዳንድ ክርስቲያኖችም “አባ ሐሜል ከምድራዊው የቅ. ቁርባን ማዕድ ወደ ሰማያዊው የጌታ ማዕድ ተሸጋገሩ” በማለት የክርስቲያን ሞት ፍጻሜ ሳይሆን ወደ ክብር መሻገር መሆኑን ጽፈዋል። የክርስትናን እምነት ከሚያንጸባርቁ ብዙ የግለሰቦች አስተያየት አንዱ “የገዳዮቹ ጩቤ የአባ ጉሮሮ ላይ እንጂ ነፍሳቸው ላይ አይደርስም” ሲል ተነቧል። 

Write comment (0 Comments)

“ሄሮዱስን ሳይፈሩ እምነት የሚያስተምሩ፣ ስደትንና ሞትን ሳይፈሩ ለምእመናን ምስክርነት የሚሰጡ... እረኞች እጅጉን ያስፍልጋሉ” ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

“ሄሮዱስን ሳይፈሩ እምነት የሚያስተምሩ፣ ስደትንና ሞትን ሳይፈሩ ለምእመናን ምስክርነት የሚሰጡ፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በመስቀሉ የማያፍሩ እረኞች እጅጉን ያስፍልጋሉ” ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

Peter Paulየላቲን ሥርዓተ አምልኮ በምትከተው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ባለፈው ሰኞ የቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ ዝክረ በዓል በታላቅ መንፈሳውነት የተከበረ ሲሆን፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካም ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከአንድ መቶ በላይ በሚሆኑ ካርዲናሎችና ጳጳሳት እንዲሁም እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ካህናት በኁባሬ መሥዋዕተ ቅዳሴን አሳርገዋል።

ቅዱስነታቸው በቅዳሴው መካከል ባሰሙት ስብከት የእነ ቅዱስ ጴጥሮስና ጳውሎስ ሰማዕትነት የቤተ ክርስትያን ስደትን እንደሚያስታውሰንና ዛሬም በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ክርስትያኖች በብርቱ ስደት ላይ እንደሆኑ በመግለፅ ነገር ግን ሁሉም ምንም እንዳላዩና ምንም እንዳልሰሙ ዝም ማለታቸው አሳዛኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በመሥዋዕተ ቅዳሴ ከተነበቡ ንባቦች የመጀመርያዊ ከሓዋርያት ሥራ ምእራፍ 12 የተወሰደው “በዚያም ዘመን ንጉሡ ሄሮድስ መከራ ያጸናባቸው ዘንድ ከቤተ ክርስቲያኑ በአንዳንዶቹ ላይ እጁን ጫነባቸው። የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው። አይሁድንም ደስ እንዳሰኛቸው አይቶ ጨምሮ ጴጥሮስን ደግሞ ያዘው። የቂጣ በዓልም ወራት ነበረ።በያዘውም ጊዜ ወደ ወኅኒ አገባው … እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍራ ክፍል አሳልፎ ሰጠው። ጴጥሮስም በወኅኒ ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አጥብቆ ይደረግ ነበር። … በዚያች ሌሊት ጴጥሮስ በሁለት ሰንሰለት ታስሮ ከሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባቂዎችም በደጁ ፊት ሆነው ወኅኒውን ይጠብቁ ነበር። እነሆም፥ የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፤ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና። ፈጥነህ ተነሣ አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ። መልአኩም ታጠቅና ጫማህን አግባ አለው፥ እንዲሁም አደረገ። ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ አለው። ወጥቶም ተከተለው፤ ራእይንም የሚያይ ይመስለው ነበር እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም። … ባስተዋለም ጊዜ እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ።ጴጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሉአት አንዲት ገረድ ትሰማ ዘንድ ቀረበች፤ የጴጥሮስ ድምፅ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሣ ደጁን አልከፈተችም፥ ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ጴጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች። ... ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ። ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ አለ።” የሚል ክፍል ነበር፣ ቅዱስነታቸውም ይህንን ምንባብ ጠቅሰው ያኔ ይፈጸሙ ስለነበሩ ጨካኝ አያይዝ ስቃይና ኢሰብአዊ ስደቶች ስንናገር ዛሬ በዓለማችን ስላሉ የክርስትያን ስደቶች የተመለክተን እንደሆነ ከዛኛው በሚብስ ሁኔታ እየተካሄደ ነው፣ የመጀመርያ ማኅበረ ክርስትያን አባሎች ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ባሳዩት ጅግነንት ሞትንና ስደትን ሳይፈሩ ወንጌልን ለሁሉም ለማዳረስ መቻላቸው የሚደነቅ ሆኖ ዝክራቸውን ስናደርግ ለጸሎትና ለእምነታችን ምስክርነት እንድንሰጥ ጥሪ ያቀርብልናል ብለዋል።

ቤተክርስትያናችንን እስካሁን ወደፊት ያስኬዳት ማኅበራዊ ጸሎቱ በቀጣይነት መደረጉ ነው፣ አንዱ ምሳሌ የጴጥሮስ ሲሆን በሮማ ከተማ ታሪክ ያሉትን ካታኮምብ የሚባሉ ጉድጓዶች የተመለከትን እንደሆነ በስደት ጊዜ ማኅበረ ክርስትያኖች በኅበረት በተለይ ደግሞ እሁድ እሁድ ጸሎት የሚያሳርጉባቸው ቦታዎች እንደነበሩ እንረዳለን፣ በሐዋርያት ሥራ ውስጥ ወደ ጴጥሮስ መልአክ እንደተላከ ሁሉ እኛም ስንጸልይና እግዚአብሔር ለጸሎታችን መልስ ሲሰጥ ወደ እኛም ይላካል።

እስቲ እናስተንትን ስንት ጊዜ ነው በችግር ተውጠን ጸሎት ስናሳርግ እግዚአብሔር እንደዚሁ መልአኩን ልኮ ከችግር ያወጣን? ጴጥሮስን ከእንቅልፉ እንደቀሰቀስው ስንት ጊዜ ብቻህን አይደለህም እንደማለት በጉዞአችን ይሸኘናል? የኛ ሁኔታ ግን አብዛኛውን ጊዜ በብርቱ ፍራቻ ተውጠን ወይንም ትንሽ ድል ካገኘን በድሉ ሰክረን ሁሉን እንረሰዋለን፣ ወይንም ልክ ጴጥሮስን እንዳጋጠመው ህልም ሆኖ ይሰማናል፤ ወይንም ያች ጴጥሮስን የተቀበለች በሩን እያንኳኳ ሳትከፍትለት ትታው የሄደችወን እንሆናለን።

ታሪክን የተመለከትን እንደሆነ ቤተክርትያንን ለማጥፋት ብዙ ኃይሎች ተነስተዋል ነገር ግን ቤተክርስትያን እስካሁን ጸንታ ትኖራለች፣ የዚህ ዋስትና የማኅበረ ክርስትያኖች የማያቋርጥ የእምነት ጸሎት ነው፣ ለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ጢሞቴዎስ በጻፈው ሁለተኛ መልእክቱ “ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፥ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ። ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል ለሰማያዊውም መንግሥት ይጠብቀኛል፤ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።”(4፤17-18)፣ ይላል፣ እግዚአብሔር ልጆቹን ከዓለም አይለያቸውም እንዲሁም ከክፉ ፈተና ነገር ሁሌ ችግሮችን ለማሸነፈ ጸጋውና ኃይሉ ይሰጣቸዋል፣ በእውነት የሚያምን ሰው ብቻ ነው “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚጐድለኝ ምንም ነገር የለም”(መዝ 23፤1) ማለት የሚቻለው።

ከውጭም ይሁን ከውስጥ ቤተክርስትያንን ለማጥፋት ብዙ ጠላቶች ተነሥተዋል ነገር ግን ራሳቸው ጠፉ እንጂ ቤተክርስትያን ተርፋለች ሁሌም ሕያውና ፍሬያማ ናት፣ በዚህ ምክንያትም ቅ.ጳውሎስ እንደሚለው “ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን” ለማለት ይቻላል።

ቤተ ክርስትያን የአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ወይንም የጳጳሳት ወይንም የምእመናን አይደለችም የጌታ ኢየሱስ ክርስቶ ናት፣ ሁሉ ነገር ስለሚያልፍና ጌታ ግን ለዘለዓለም ስለሆነ ብዙ ነገሥታት ሕዝብ ባህሎች አገሮች ርእዮተ ዓለሞች ሥልጣኖች አልፈዋል ቤተክርስትያን ግን በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ስለተመሠረተች ምንም እንኳ ብዙ ማዕበልና ኃጢአቶቻችን ቢከብድዋት ለዘለማለም በአገልግሎትዋ ታማኝ የእምነት መዝገብ ሆና ትኖራች፣ ይህም በእምነት ኃይልና ልጆችዋ በሚሰጡት ብርታት የተሞላው ምስክርነት ሲሆን ዛሬ የምናስታውሳቸው በደማቸው የመሰከሩ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ እንደሌሎቹ ሓዋርያት የጌታን ጽዋ በመጠጣት በደማቸው ቤተክርስትያንን በዚሁ ምድራዊ ሕይወትዋ እንድትፈራ አደረጉ፣ ለዚሁ ምስክርነት ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ “በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል። መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።”(2ጢሞ 4፤6-8)፣

“አንዲት ቤተ ክርስትያን ወይንም አንድ ክርስትያን ያለምስክርነት መኻን ነው፣ ልክ በሕይወት እንዳለ የሚመስለው የሞተ ሰው ዓይነት ወይንም ፍሬ የማይሰጥ የደረቀ ተክል ወይንም እንደደረቀ ወኃ የሌለው ኩሬ ነው፣” ብለው በአጠቃላይ ስለምስክርነት ተናገሩ በኋላ ርሊጳ ፍራንቼስኮስ ወደ አዳዲሶቹ ሊቃነ ጳጳሳት መለስ በማለት የጸሎት የእምነትና የምስክርነት ሰዎች መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል፣

“የተከበራችሁ ሊቃነ ጳጳሳት ዛሬ የምትቀበሉት አክሚም/ፓልዮ እረኛ በትከሻው የተሸከማት በግ ምሳሌ ሆኖ ይህም መልካሙ እረኛ የሆነው ኢየሱስ ምሳሌ በመከተል ዋነኛው ተልእኮአችሁ ይህ መሆኑን እንዳትዘነጉ አደራ ካሉ በኋላ ልሂቅ ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛ በበዓለ ጴጥሮስ ወጳውሎስ እ.አ.አ 2005 ዓ.ም. በመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ ያሉትን ስለ ሊቃነ ጳጳሳት ተልእኮ እንዲህ ብለዋል፣

“ይህ ምልክት በሥርዓተ አምልኮ የውህደትና የአንድነት ምልክት ሆኖ መንበረ ጴጥሮስንና ተከታዮቹ ሜትሮፖሊታዊ መንበሮች በማያያዝ በአማካኝነታቸውም በመላው ዓለም ከሚገኙ ጳጳሳት ጋር ያስተሳስራል፣ ዛሬ ይህንን አክሚም/ፓልዮ ስሰጣችሁ ይህንን ለጸሎት ለእምነትና ምስክርነት የሚጠራ ተልእኮን በመተማመን እሰጣችኋለሁ፣ ቤተክርስትያናችን ዛሬ የጸሎት ሰዎች ጸሎት የሚያስተምሩ ያስፍልጋታል፣ የተመዛዘነ ሕይወት ከሌለ ምስክርነት የለም። ሄሮዱስን ሳይፈሩ እምነት የሚያስተምሩ፣ ስደትንና ሞትን ሳይፈሩ ለምእመናን ምስክርነት የሚሰጡ፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በመስቀሉ የማያፍሩ እረኞች እጅጉን ያስፍልጋሉ በማለት ስብከታቸውን ደምድመዋል።

በዚሁ ዓመት የሊቀ ጵጵስና መዓርግ ለሰጥዋቸው ከመላው ዓለም ለመጡም አክሚም/ፓልዮ (ለሊቀ ጳጳሳት የሚሰጥ በትከሻ የሚጠልቅ ምልክት) ባርከው ሰጥተዋል፣ የአሥመራ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መንግሥተአብ ተስፋማርያምም ከእነዚሁ አዳዲስ ሊቃነ ጳጳሳት አንዱ ነበሩ፣ የዚሁ ታላቅ የብፁዕነታቸው በዓል ተሳታፊ ለመሆን የእምድብር ሃገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ እና የባረንቱ ሃገር ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቶማስ የሚገኙባቸው ከአሥር በላይ የሆኑ ካህናት አብረው በኁባሬ የቀደሱ ሲሆን ደናግል ውሉደ ክህነትና በሮም የሚገኙ ም እመናን በሥርዓቱ ተሳትፈዋል፣

ምንጭ፡- ራድዮ ቫቲካን http://am.radiovaticana.va/

Write comment (0 Comments)

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።