በአባ ፍስሐ ገብረ አምላክ አማልጅነት ከእግዚአብሔር ጸጋን ለመለመን የሚደረግ ጸሎት

አባ ፍስሐ ገብረ አምላክ የመጀመሪያው ሲታዊ ሓበሻ

አባ ፍሥሐ ገብረአምላክ ሰኔ 16 ቀን 1887 ዓ.ም. በኤርትራ በከረን አካባቢ “ዓዲ በሃይማኖት” በምትባል መንደር ተወለዱ። በከረን ቅ.ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተጠምቀው ኃይለማርያም ተባሉ። ከልጅነታቸው ጀምሮ ክፋትን የሚጠሉና ሰብአዊ ርኅርኄ ያላቸው ሰው ነበሩ። በጽኑ በሽታ በሥጋ ሞት እስካረፉባት እድሜያቸው በነበራቸው የሕይወት ቅድስና መልካም ምስክርነትን ሲሰጡ ነበር። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ይህ ምስክርነታቸው ለብዙኀን ትሩፋት ይሆን ዘንድ ሕይወታቸው በቤተ ክርስቲያን ወጋዊ የቅድስና ሂደት ላይ ይገኛል...ተጨምሪ የሕይወት ታሪካቸውንና የቅድስና ገድላቸውን ለማንበብ ይህን ይጫኑት በአማልጅነታቸው ከእግዚአብሔር ጸጋን ለመለመን የሚደረገውን ጸሎት ለማድረስ ከታች ይመልከቱ። (ሐምሌ 2000 ዓ.ም. ለዕረፍታቸው 75ኛ ዓመት በካዛማሪ የተደረገው ቅዳሴ ፎቶዎች)

Abba_Fissiha4

የእግዚአብሔር አገልጋይ አባ ፍስሐ ገብረአምላክ።

አባ ፍስሐን ብፁዕ ለማለት በቤ/ያን የሚያስፈልገው ቅድመ ጥናት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በርሳቸው አማላጅነት ከእግዚአብሔር ተአምር ማግኘት ከተቻለ በይፋ ብፁዕ ይባላሉ ለዚህም ያግዝ ዘንድ በቤተ ክርስቲያን ፈቃድ በአማላጅነታቸው ጸጋ ለማግኘት የሚደረገው ጸሎት አነሆ:-


እግዚአብሔር አብ ሆይ! የምሕረትህን ብዛት በቅዱሳንህ የገልጽህ፤ ለአገራችን የሚሆን ካቶሊካዊ ምንኩስናን በአባ ፍስሐ የጀመርክ፤ ቅድስናቸውን ግለጽልን በአማላጅነታቸውም የሚያስፈልገንን ጸጋ ስጠን።
በሰማይ የምትኖር፣ ጸጋ የሞላሽ፣ ምስጋና…


እግዚአብሔር ወልድ ሆይ! እውነተኛ ብፅዕና በተአዝዞ፣ በትሕትና እና በድህነት እንደሚገኝ ያስተማርክ፤ የአባ ፍስሐን ቅድስና ግለጽልን በአማላጅነታቸውም የሚያስፈልገንን ጸጋ ስጠን።
በሰማይ የምትኖር፣ ጸጋ የሞላሽ፣ ምስጋና…


እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሆይ! በአባ ፍስሐ ልብ የአምላክንና የሰውን ፍቅር ያሳደርክ፤ እኛም አብነታቸውን ተከትለን እርሳቸውን እንድንመስል አድርገን ቅድስናቸውን ግለጽልን በአማላጅነታቸውም የሚያስፈልገንን ጸጋ ስጠን።
በሰማይ የምትኖር፣ ጸጋ የሞላሽ፣ ምስጋና…

{jathumbnail off}