ንኡሳን ገጾች
Chaplet of Divine Mercy
Home (ቅድመ ገጽ)

በቅርብ የተጨመሩ ጽሑፎች

የገዛ ራስህን ድካም መገንዘብ

ቫቲካን ሬድዮ - “የገዛ ራስህን ድካም መገንዘብ ከሁሉ መቅደም ያለበት ተገቢ ነገር ነው”፣ ይህን ያሉት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ ሮማ  በሚገኘው የቅድስት ሳቢና ባዚሊካ በሥርዓተ ላቲን የጾም ጅማሬ የቅዳሴ ሥርዓተ በመሩበት እና ባሰሙት ስብከት ነው። አያይዘውም ሰው ዳግም ፍትሐዊ መሆን የሚችለው በክርስቶስ በኩል በተገለጠው የእግዚአብሔር ፍትሕ እና ምሕረት መሆኑ አስገንዝበዋል።

በዚሁ ጾመ አርባን በምንጀምርበት ጊዜ አንድ ፍትሐዊ ኅብረተ ሰብ ለመገንባት እና የሰው ግርማን የጠበቀ ሕይወት ለማሳለፍ ቤተክርስትያን ግላዊ እና ማኅበረ ሰባዊ መቀየር ወይም መለወጥ እንደሚያሻ ትጠይቃለች ብለዋል። የሰው ልጅ በየዕለቱ በሚያጋጥሙት አሉታዊ ነገራት ሲሰላችም አሁን ካለው የተሻለ ፍትሕ ያለው ዓለም እንደሚመኝ አመልክተዋል።

በመቀጠል ለሰው ልጅ ድኅንነት ሞቶ በተነሣው ክርስቶስ ሰው ከሚሰጠው ፍትሕ የተለየ ግልጸት መለኮታዊ ፍትሕ መከሰቱ አስረድተዋል። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ፍትሕ የፍቅርና የምሕረት ፍትሕ በመሆኑ ዘለዓለማዊ ፍትሕ እንደሆነ ቅድስነታቸው ገልጸዋል።

ቅድስነታቸው ቀጥለው ፡ በጾም ግዜ መጾም መጸለይ እና ማስተንተን፡ ከልብ የፈለቁ ካልሆኑና ከልብ የመጸጸት ምልክት ከሌላቸው በእግዚአብሔር ዘንዳ ተቀባይነት እንደሌላቸው አስገንዝበዋል። እውነተኛነት የሌለው እና ተጸጽቶ የመቀየር ውሳኔ የሌለው ጾም እና ተጋድሎ ከንቱና ውጤቱም ብላሽ እንደሆነ ያመለከቱት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ ከሁሉም የባሰ ደግሞ ለይምሰል የሚድረግ ጸጸት እና ተግባራዊ የማይሆን ከሆነ ራስህን ማታለል እና ፋይዳ ቢስ መሆኑ ገልጠዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ የንባበ መለኮት ምሁር መሆናቸው የሚታወስ እና ጥልቅ የቤተክርስትያን ትምህርትን ለዓለም ምእመናን እያበረከቱ መሆናቸው የማይዘነጋ ሲሆን አያይዘው፡ ክርስቶስ በምድረ በዳ ለአርባ ቀናት ያደረገው ቆይታ ፡ ሰው በጾም ግዜ ምን ማድረግ እንዳለበት በምን ዓይነት እኳኀን መጾም እንዳለበት ያመላክታሉ ብለዋል።

በእግዚአብሔር ፈቃድ ክርስቶስ በምድረ በዳ ሲቆይ በፈቃዱ የጠላት ጥቃት ሰለባ ለመሆን ስለፈለገ ነው ካሉ በሁዋላ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት፤ አዳም ፈተና ላይ ወድቆ መሞቱም የሞት ጅማሬ መሆኑን አመልክተው፡ ክርስቶስ ለጠላት ሲጋለጥ የከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር ፍቅርን እና ፍላጎትን ለማሟላት መሆኑን አስረድተዋል። ሆኖም የክርስቶስ ትንሣኤ ተሳታፊ ለመሆን ክርስቶስ በምድረ በዳ የተወጣውን ተጋድሎ በመከተል ሞትን ማሸነፍ እንደሚገባና ሞት ማለትም ዘለዓለማዊ ጥፋት ነው እና ሞትንም ማሸነፍ እንደሚቻል አስገንዘበዋል።

በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው ሰው በፈጸመው ኃጢአት የራሱን ንጽሕና እንዳጠፋ የጠቀሱት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ፡ በእግዚአብሔር መሐሪነት እና ሐቀኛ ፍትህ ንጽሕናውን መልሶ ለመቀዳጀት እንደሚችል ገልጸዋል።

ቅድስነታቸው ስበከታቸውን በማያያዝ እግዚአብሔር ሰውን እንዲጠፋ በኃጢአቱ ተጨማልቆ እንዲኖር ስላልፈለገ ምሕረቱን ሰጠው ጸጋውንም አፈሰሰለት። ጾም አመለካከታችንንና አስተሳሰባችንን እንድናሰፋ፣ ፊታችንን ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት እንድናቀና እና በዚች ዓለም እንግዶች መሆናችንን ያስረዳናል ብለዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ፡ ቅዱስ አባታች ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔነዲክቶስ ፊታችን መጋቢት አስራ አራት ቀን ሮማ ውስጥ የምትገኘውን ወንጌላዊት ሉተራን ቤተክርስትያን እንደሚጐበኙ የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል። የቤተክርስትያኒቱ ክቡር ቄስ ጂንስ ማርቲን ክሩሰ እንደገለጡት፡ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጉብኝት ለኤኩመኒካዊ (ለክርስትያን አንድነት)እጅግ ጠቃሚ ይሆናል ፡ ወንጌላዊት ሉተራዊት ቤተክርስትያንም ጉብኝቱ በጉጉት ትጠባበቀዋላች ብለዋል።

Last Updated (Friday, 26 February 2010 05:47)

 

ስቃይ መልስ የለውም ማለት ትርጉም የለውም ማለት አይደለም!

ቫቲካን ሬድዮ - እ.ኤ.አ. የካቲት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በመላው ዓለም 18ኛው የሕሙማን ቀን ይከበራል። ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛው በዕለቱ በሮም ሰዓት አቆጣጠር 10.30 በቫቲካን ባዚሊካ መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ በዕለቱ የሉርድ ብፅዕት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓልም ታውሶ ይውላል።
የዘንድሮው የዕለተ ሕሙማን መሪ ቃል “ቤተ ክርስትያን ለሚሰቃዩት የምታበረክተው የፍቅር አገልግሎት” የሚል ነው ሲሆን ከአሁን በፊት ቅዱስነታቸው በሕመምና በስቃይ የሚገኙ የሰው ልጆች ክብርን አስመልክተው ብዙ ትምህርት ሰጥተዋል። ለምሳሌ እ.ኤ.አ.ታሕሣሥ 2 ቀን 2007 ዓም በቅዱስ ዮሓንስ መጥምቅ ሆስፒታል ሲናገሩ፥ “ለምን እንሰቃያለን? የስቃይ ሕይወት አዎንታዊ ትርጓሜ ሊኖረው ይችላልን? ከስቃይና ከሞት ነፃ ሊያወጣን የሚችል ማን ነው? እነኚህ የኑሮ መሠረታዊ ጥያቄዎች ናቸው። ስቃይ በአእምሮ ሊታወቅ የማይቻል ምሥጢር ስለሚያንሣብን፣ እነኚህ ጥያቄዎች በሰው ልጅ አነጋገር ብዙውን ጊዜ መልስ አይኝላቸውም። ይህ ግን ስቃይ ትርጉም የለውም ማለት አይደለም። በሕመምና በስቃይ በምንገኝበት ጊዜ እግዚአብሔር ምሥጢራዊ በሆነ መንገድ ይጐበኘናል፣ ሁሉመናችንን ለፈቃዱ የተውነው እንደሆነ የፍቅሩን ችሎታ መቅመስ እንችላለን።" ብለው ነበር።
ነገ በሚካሄደው ሥርዓት ቅዱስነታቸው ከሕሙማን ጋር ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ እንዲሁም ሁል ጊዜ በዚህ አጋጣሚ እንደሚያደርጉት 18ኛው ዓለም አቀፍ የሕሙማን ቀንን የሚመለከት መልእክታቸውን ያስተላልፋሉ።

Last Updated (Thursday, 11 February 2010 11:01)

 

ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ላይ የግድያ ሙከራ ያደረገው ቱርካዊ ከማረምያ ቤት ወጣ

alg_pope_agcaIndependent Catholic News - Tuesday, January 19, 2010 - በ1973 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ ላይ የግድያ ሙከራ ያደረገው ቱርካዊ ከእስር ተለቀቀ። ግለሰቡ ከዚህ በኋላ የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ግዳጁን እንደሚፈጽምም የቱርክ መገናኛ ብዙኀን ዘግቧል።

በአሁኑ ሰዓት 52 ዓመት ዕድሜ ያለው መህሜት አሊ አጅካ በር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ላይ ባደረገው የግድያ ሙከራ በጣልያን 19 ዓመታትን በእስር ያሳለፈ ሲሆን፤ በመቀጠል ደግሞ ከዚያ በፊት የአንድ ጋዜጣ አርታዒን በመግደሉ ሌላ 10 ዓመታትን በመታሰሩ በድምሩ 30 ዓመታት በእስር ቤት ማሳለፉ ታውቋል።

ምንም እንኳ በወቅቱ በቁጥጥር ሥር ሲውል ከማንም ጋር ትብብር የሌለው ግላዊ ድርጊት መሆኑን ቢገልጽም፤ ር.ሊ.ጳጳሳትን ለመግደል ለአጅካ ምክንያት የሆነው ነገር እስካሁን ምስጢር እንደሆነ ቀርቷል። በአንድ ወቅት የቱርክ አንድ አገራዊ ቡድን አባል የነበረ ሲሆን፤  በሌላ አጋጣሚም በቡልጋርያ የደኅንነት አገልግሎት እንደሚመራ ገልጾ የነበረ ቢሆንም እንኳ በ1970ዎቹ በጣልያን 22 ወራትን የፈጀው ምርመራ መረጃ ሳያገኝለት ቀርቷል።

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በ1975 ዓ.ም. ከአጅካ ጋር ከተገናኙ በኋላ ይቅር ማለታቸው ይታወቃል።

በተደጋጋሚ የሚታዩት ኃይለኛ ቁጡነቱና "አዲስ መሲሕ ነኝ" የሚሉት ንግግሮቹ ስለአጅካ የአእምሮ ጤነኝነት ጉዳይ ቀጣይ የሆነ ጥያቄ አስነሥተዋል። ትላንትና ከእስር ሲለቀቅ ባደረገውም ንግግር "የዓለምን ፍጻሜ አውጄያለሁ፤ በያዝነው ክፍለ ዘመን መላው ዓለም ይወድማል፤ ሁሉም ሰውም ይሞታል። እኔ ዘላለማዊው ክርስቶስ ነኝ" ሲል ተደምጧል።

Last Updated (Wednesday, 20 January 2010 21:19)

 
የሳምንቱ መልእክት
"ለሰው ይኽን ያህል ታላቅ ክብር ለመስጠት ያነሳሳህ ምን ይሆን?...ወደር የሌለው ፍቅርህ እንደሆነ አይጠረጠርም! በፍቅሩ ተማርከሃል፤ በአውነትም በፍቅር ፈጥረኸዋል፤ በፍቅርም ዘላለማዊ መልካምነትህን የሚያጣጥም ስብእናን ለግሰኸዋል።" ቅድስት ካተሪና ዘሲየና
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ያን መዝሙሮች (ብዛት 110!)
ባለፉት 12 ሰዓታት የጎብኚዎች አገር
Top 5:
United States flag 36%United States (4)
Ethiopia flag 27%Ethiopia (3)
Russian Federation flag 18%Russian Federation (2)
Moldova, Republic of flag 9%Moldova, Republic of (1)
Switzerland flag 9%Switzerland (1)
11 visits from 5 countries