ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ላይ የግድያ ሙከራ ያደረገው ቱርካዊ ከማረምያ ቤት ወጣ
Independent Catholic News - Tuesday, January 19, 2010 - በ1973 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ ላይ የግድያ ሙከራ ያደረገው ቱርካዊ ከእስር ተለቀቀ። ግለሰቡ ከዚህ በኋላ የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ግዳጁን እንደሚፈጽምም የቱርክ መገናኛ ብዙኀን ዘግቧል።
በአሁኑ ሰዓት 52 ዓመት ዕድሜ ያለው መህሜት አሊ አጅካ በር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ላይ ባደረገው የግድያ ሙከራ በጣልያን 19 ዓመታትን በእስር ያሳለፈ ሲሆን፤ በመቀጠል ደግሞ ከዚያ በፊት የአንድ ጋዜጣ አርታዒን በመግደሉ ሌላ 10 ዓመታትን በመታሰሩ በድምሩ 30 ዓመታት በእስር ቤት ማሳለፉ ታውቋል።
ምንም እንኳ በወቅቱ በቁጥጥር ሥር ሲውል ከማንም ጋር ትብብር የሌለው ግላዊ ድርጊት መሆኑን ቢገልጽም፤ ር.ሊ.ጳጳሳትን ለመግደል ለአጅካ ምክንያት የሆነው ነገር እስካሁን ምስጢር እንደሆነ ቀርቷል። በአንድ ወቅት የቱርክ አንድ አገራዊ ቡድን አባል የነበረ ሲሆን፤ በሌላ አጋጣሚም በቡልጋርያ የደኅንነት አገልግሎት እንደሚመራ ገልጾ የነበረ ቢሆንም እንኳ በ1970ዎቹ በጣልያን 22 ወራትን የፈጀው ምርመራ መረጃ ሳያገኝለት ቀርቷል።
በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በ1975 ዓ.ም. ከአጅካ ጋር ከተገናኙ በኋላ ይቅር ማለታቸው ይታወቃል።
በተደጋጋሚ የሚታዩት ኃይለኛ ቁጡነቱና "አዲስ መሲሕ ነኝ" የሚሉት ንግግሮቹ ስለአጅካ የአእምሮ ጤነኝነት ጉዳይ ቀጣይ የሆነ ጥያቄ አስነሥተዋል። ትላንትና ከእስር ሲለቀቅ ባደረገውም ንግግር "የዓለምን ፍጻሜ አውጄያለሁ፤ በያዝነው ክፍለ ዘመን መላው ዓለም ይወድማል፤ ሁሉም ሰውም ይሞታል። እኔ ዘላለማዊው ክርስቶስ ነኝ" ሲል ተደምጧል።
Last Updated (Wednesday, 20 January 2010 21:19)
የልደተ ክርስቶስ ድባብ በቫቲካን መንበረ ጴጥሮስ
የልደተ ክርስቶስ ድባብ በቫቲካን መንበረ ጴጥሮስ አደባባይና ቤተ ክርስቲያን...(ፎቶዎች)
በቫቲካን ከተማ የሚገኘው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ደብር - መንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ - በዓለማችን ካሉ ተጎብኚ ቦታዎች የብዙዎችን ቀልብ በመሳብ ቀዳሚው መሆኑ ይታወቃል። ከአደባባዩ ጀምሮ እስከ ደብሩ ሥነ ሕንፃው ቅርጽና ውበት፣ እንዲሁም በውስጡ ያሉ ዓለማችን ያፈራቻቸው ታላላቅ ሥነ ጥበብት የሳሏቸውና የቀራረጿቸው የጥበብ ሥራዎች፣ የተለያዩ ታሪካዊ ሰነዶችና ንዋየ ቅዱሳት...ወዘተ በተለያየ መልኩ ብዙ ሰዎች በቦታው ሲገኙ ከጊዜና ቦታ ውጭ የሆነ ወደሚመስል ስሜት ፈጥነው እንዲሻገሩ ያደርጋቸዋል።
ከነዚህ ተያዥና ተጨባጭ ነገሮች ባሻገር ለመላው ክርስቲያኖች በተለይም ደግሞ ለካቶሊካውያን ክርስቶስ ቅዱስ ጴጥሮስን እኔም እንዲህ እልሃለሁ፦ ጴጥሮስ አንተ ዓለት ነህ፤ በዚህችም የመሠረት ድንጋይ ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ ይህችንም ቤተ ክርስቲያን የሞትኃይል እንኳ አያሸንፋትም። እነሆ ለአንተ የመንግሥተ ሰማይን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሆናል ማቴ.16:17-19 በማለት ሰማይና ምድር ቢያልፉ እንኳ በማያልፍ ቃሉ የሰጠውን ተስፋ ተቀብሎ እስከ ሰማዕታዊ ሞቱ ድረስ ለክርስቶስ የኖረው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የተቀበረበትና ከ2 ሺህ ዓመታት በላይ ይህን የርሱን ኃላፊነት ያለማቋረጥ በመቀባበል በመተግበር ላይ ያሉ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚቀመጡበት ስፍራ ስለሆነ የእግዚአብሔር ጸጋ ልዩ ሞገስን ያላበሰው ደብር መሆኑን አብዛኛው ሰው የሚመሰክረው እውነታ ነው።
ከዚህ በታች የሚመለከቷቸው ፎቶዎች ከላይ የገለጽነውን እውነታ ለማስተላለፍ አቅም ባይኖራቸውም፤ የዘንድሮውን የክርስቶስን ልደት በዓል -ገና- ምክንያት በማድረግ በቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ ደብርና አደባባይ የተዘጋጀውን ጌታ ሲወለድ የነበረውን ድባብ የሚያሳይ ዝግጅት ለማሳየት እንሞክራለን። ወንጌሉ እንደሚለው በከብቶች መመገቢያ ግርግም ውስጥ በመላእክት፣ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና በቅዱስ ዮሴፍ መታጀቡን፤ በእረኞችና በነገሥታት መጎብኘቱን...ያሳያሉ። መልካም ቆይታ።
ክፍል 1 - የቅዱስ ጴጥሮስን ቤተ ክርስቲያን ከውስጥ በኩል በመጠኑ የሚያሳዩ ፎቶዎች (ይጫኑት)
ክፍል 2 - የቅዱስ ጴጥሮስን ቤተ ክርስቲያን ከውጭ በኩል የሚያሳዩ ፎቶዎች (ይጫኑት)
Last Updated (Monday, 18 January 2010 22:09)
ተስፋችን እግዚአብሔር ነው
ትምህርታቸውም እንደሚከተለው ነው፣ ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፦...
- ማንም ሰው ብቻውን እንዳይሆን፤ ማንም ሰው እንዳይነጠል፤ ማንም ሰው ተጥሎ እንዳይቀር
- በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ የመነኮሳውያት ቁጥር ዕድገት ሕንድ ትመራለች
- በኢራቅ የአናሳ ሃይማኖቶች ህልውና
- እርቅን፣ ፍትሕ እና ሰላምን ተግባራዊ ለማድረግ ንጹሕ ልብ፣ አዲስ አመለካከትና ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት
- በሚሊየን የሚቆጠሩ ጽንስ የማስወረድ ሕጋዊነትን ተቃዋሚዎች በስፔን
- ቤተ ክርስትያን የስብከተ ወንጌል ተልእኮ ቀንን አስታውሳ ዋለች
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ ያሰሙት ንግግር
- ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያቀረቡት ሰላምታ
- የሰው ልጅ ሁሉ መመዘኛ ክርስቶስ ነው
- የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ተጀመረ
- ለእውነት ክፍት መሆን ይገባል
- ር.ሊ.ጳ. በሚስዮናዊው መገደል የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ












