ማንም ሰው ብቻውን እንዳይሆን፤ ማንም ሰው እንዳይነጠል፤ ማንም ሰው ተጥሎ እንዳይቀር
ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛ ትናንትና በቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ በየዓመቱ ለነዳያን በሚያዘጋጁት የምሳ ግብዣ ላይ ከ2000 ድኆች ጋር ምሳ በልተዋል። ተጋባዦቹ ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት የመጡ ስደተኞችና ምንም የሌላቸው የሮማ ድኆች ናቸው። ቅዱነታቸው እቦታው በደረሱበት ጊዜ የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር የማኅበሩ መሥራች ፕሮፈሰር ኣንድረያ ሪካርዲ የማኅበሩ ሊቀ መንበር ማርኮ ኢምፓጝልያዞ ከአንድ ሮም ሴትና የሰነጋል ስደተኛ ወጣትና የተርኒ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቪንቸንዞ ፓጝልያ እና ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ልዊጂ ሞረቲ ከድኆቹ አብረው ተቀብለዋቸዋል፣
ፕሮፈሰር አንድረያ ሪካርዲ በእንኳን ደህና መጡ ንግግራቸው፣ “ብፁዕ አባታችን ይህንን ቦታ እንደቤታቸው ከሚቈጥሩት የዚህ ልዩ ኅብረተሰብ ጓደኛ በመሆን ከእኛ አብረው ሲበሉ፣ እርስዎን በቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር ማእድ ከእኛ ጋር ማየት ትልቅ ደስታ ይሰማናል”፣ ሲሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጠው በቦታው በየቀኑ ከአንድ ሺ በላይ እንደሚመገቡ፣ ሰዎቹም በተለያዩ ችግሮች የተጠቁ መሆንቸውን አልደበቁም፣ እንደ ቤተሰብ ሆነው መግብ ብቻ ሳይሆን በፍቅርና በጓደኝነት እንደሚኖሩም ኣብራርተዋል። የድኆች ጓደኛና አለኝታ መሆን ክርስትያንን ያሳድጋል በማለት ትልቁ ጎርጎርዮስ ድኆችን በማገልግል ኃይልና ብርታት እንደሚገኝ ያስተማረውን አስታውሰዋል።
ቅዱስነታቸው ከተለያዩ ኣገሮች ከመጡ ስደተኞች በተለይም በማኅበሩ ብተደራጀ የጣልያነኛ ቋንቋ ትምህርት የሚከታተሉትን ትንሽ ቡድን ሲያነጋገሩ፣ “ቋንቋ በአንድነት ለመኖርና አንድ ቤተ ሰብ ለመሆን የመዋሃሃድ ቍልፍ ነው፣ በቋንቋ ባህልና የባህል ታሪክ እንዲሁም የባህሉ ዕጣ ፈንታ ተደብቆ ይገኛል፣ ይህንን የቋንቋ ትምህርት ዕድል ላበረከተላችሁ የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር አመሰግናለሁ”፣ ሲሉ የተሰጣቸውን ዕድል እንዲጠቀሙበት አደራ ብለው፣ ካበረታቱ በኋላ ማኅበሩ የሠራውን የቤተ ሰቡ የልደት የቤተ ልሔም ግርግም አይተው ምሳ በልተዋል። በምሳ ጊዜ ከቅዱስነታቸው የተለያየ ችግር ያላቸውና ከተለያዩ ወገኖች የመጡ 12 ሰዎች በአንድ ጠረጲዛ ተመግበዋል።
ቅዱስነታቸው እንደ ኢየሱስ ልዩ ጓደኞች የጠርዋቸው የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበረሰብ አብረው በመመገባቸው የተሰማቸውን ደስታና እርካታ ገልጠዋል። ግብረ ሠናዩንም እንዲህ ሲሉ አመጕሰውታል፣ “ኢየሱስን በሚከተሉ የዘመናችን ሓዋርያት በሚደረግ ግብረ ሠናይ እግዚአብሔር በመጀመርያ እንደወደደንና ገናም እንደሚወደን የሚያሳይ እውነት ግልጽ ይሆናል፣ ለዚህም መልስ የምንሰጠው በፍቅር ነው፣ ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። ይህንን ምግባረ ሠናይ ለማን መሆኑን ለመግለጽ ደግሞ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል። እነዚህን ቃላት ስንሰማ ኢየሱን ከሚያመለክቱ ከተቸግሩት ጋር አጋርነት እንድናሳይ አይቀሰቅስምን፣ ጓደኝነትና ኣጋርነት ብቻ ሳይሆን ቤተ ሰብ መሆናችንስ አይሰማንምን” ብለዋል።
ስደትና ችግርን አስመልክተውም፣ የኢየሱስ ቤተሰብም ችግር አጋጥሞታል፣ ገና ቤተሰብ ለመመሥረት ሲጀምሩ በቤተልሔም የሚቀበላቸው አጥተዋል፣ ወደ ግብጽ እንዲሰደዱ ተገደዋል፣ እናንተ የስደትን ችግር ጥሩ ኣርጋችሁ ታውቃላችሁ፣ በችግርና በመከራ ብትገኙም እዚህ እናንተን ለማንከባከብና ለማገልገል የተዘጋጁ የእግዚአብሔር ፍቅር ምልክት የቅዱስ ኤጅድዮ ማኅበር አለላችሁ፣ ዛሬ እዚህ በየቤታችሁ ልታገኙት የምትችሉትን ታገኛላችሁ። ይህ የእውነተኛ ቤተ ሰብ ቤት ነው፣ በቤተሰብ እኔ የሚለው በእኛ ይተካል፣ ማኅበር ይቆማል፣ የፍቅር ማኅበር ስለሆነም እግዚአብሔር ማሃከላችን ይገኛል።
ኢየሱስ የሚሰቃዩትንና ችግር ያላቸውን ሰዎች የሱ ጓደኞች እንደሚያደጋቸውና እንደሚወዳቸው በመረዳት እሱን በመከተል ለሁሉም በተለይም ለተጐዱትና ረዳት ለሌላቸው ለመርዳት ዝግጁነታችን ማረጋገጥ እንድለብን አሳስበዋል፣ “ማንም ሰው ብቻው እንዳይሆን፣ ማንም ሰው እንዳይነጠል፣ ማንም ሰው ተጥሎ እንዳይቀር” ሲሉም አደራ በልዋል።
ፕሮፈሰር አንድረያ ሪካርዲ በእንኳን ደህና መጡ ንግግራቸው፣ “ብፁዕ አባታችን ይህንን ቦታ እንደቤትዎ በመቁጠርና የዚህ ልዩ ኅብረተሰብ ጓደኛ በመሆን ከእኛ ጋር አብረው በመሳተፍዎና እርስዎን በቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር ማእድ ከእኛ ጋር በማየታችን ትልቅ ደስታ ይሰማናል”፣ ሲሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጠው በቦታው በየቀኑ ከአንድ ሺ በላይ ነዳያን እንደሚመገቡ፣ ሰዎቹም በተለያዩ ችግሮች የተጠቁ መሆንቸውን ገልጠው፣ እንደ ቤተሰብ ሆነው መመገብ ብቻ ሳይሆን በፍቅርና በጓደኝነት እንደሚኖሩም ኣብራርተዋል። የድኆች ጓደኛና አለኝታ መሆን ክርስትያንን ያሳድጋል በማለት ትልቁ ጎርጎርዮስ ነዳያንን በማገልግል ኃይልና ብርታት እንደሚገኝ ያስተማረውንም አስታውሰዋል።
ቅዱስነታቸው ከተለያዩ ኣገሮች ከመጡ ስደተኞች በተለይም በማኅበሩ በተደራጀ...
Last Updated (Sunday, 31 January 2010 21:29)
በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ የመነኮሳውያት ቁጥር ዕድገት ሕንድ ትመራለች
Independent Catholic News - በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የመነኮሳውያት (የእማሆዮች) የቅርብ ዓመታት ቁጥራዊ ዕድገት ሕንድ ግንባር ቀደሙን ቦታ መያዟ ተገለጠ።
የ"Catholic Culture" ድረ ገጽ ባደረገው አኀዛዊ ዳሰሳ መግለጫ መሠረት ባጠቃላይ ሲታይ እስያና አፍሪካ እ.ኤ.አ. ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ ጥሩ የመነኮሳውያት ቁጥር መጨመር ሲታይ፤ በአውሮፓ፣ አሜሪካና ኦሺኒያ የቁጥር ማቆልቆሉ ታውቋል።
እ.ኤ.አ. ከ2002-2007 ዓ.ም. በእስያ ውስጥ ሕንድ የ9,838 ፣ ቬትናም የ2,545 እንዲሁም ፊሊፒንስና ደቡብ ኮሪያ እያንዳንዳቸው የ500 መነኮሳውያት ቁጥር ዕድገት አሳይተዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የመነኮሳውያት ቁጥር ዕድገት ካሳዩት ማኅበራት ውስጥ ሦስት በከራላ (ሕንድ) ውስጥ የተመሠረቱና የብፅዕት እማሆይ የፍቅር ልኡካን እህቶች ላቅ ያለውን ስፍራ ይይዛሉ።
Last Updated (Sunday, 31 January 2010 21:26)
በኢራቅ የአናሳ ሃይማኖቶች ህልውና
ቫቲካን ሬድዮ - በኢራቅ የአናሳ ሃይማኖቶች ህልውና ላደጋ በመጋለጡ ምክንያት ዐቢይ የደኅንነት ጥበቃ እንደሚያስፈልገው የነዚህ አናሳ ሃይማኖቶች ተጠሪዎች የጸጥታ እና የደኅንነት ጥበቃን ጥሪ በማቅረብ በተለይ ደግሞ እ.ኤ.አ. ጥር ወር 2010 ዓ.ም. በአገሪቱ በሚካሄደው ሕዝባዊ መርጫ ወቅት ተገቢ የጸጥታ እና የደኅንነት ዋስትና ያገኙ ዘንድ ለአገሪቱ መንግሥት ጥሪ አስተላልፈዋል።
በኢራቅ አናሳ ሃይማኖቶች ለተለያዩ አደጋዎች በመጋለጣቸው ምክንያት መፍትሔው ራስን ለማዳን አገር ጥሎ መሰደድ ብቻ በመሆኑ የተያያዙት ስደት እንዲወገድ ከመንግሥት የጸጥታ እና የደህንነት ዋስትና መረጋገጥ ይኖርበታል። በኢራቅ አናሳ ከሚባሉት ሃይማኖቶች ውስጥ የእስልምና እና የክርስትናን አንዳንድ የእምነት ሥርዓቶችና ትምህርተ ሃይማኖትን በአንድ በማቀላቀል የሚያስተምር 300 ሺሕ ኢራቃውያን የሚከተሉት የሻባክ ሃይማኖት አንዱ ሲሆን፣ ሌላው የያዚዲ ሃይማኖት፣ የከለዳያን ሥርዓት የምትከተል ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን፣ የኦርቶዶስክ፣ የአሲሪያ፣ የአርመን፣ የአንግሊካን አቢያተ ክርስትያን የሚመለከት ጉዳይ ሲሆን፣ በኢራቅ በመንግሥት ደረጃ ሳይሆን በአቋም ስነ ሓሳብ የተደገፈ ጸረ የአናሳ ሃይማኖት ተግባር እየተስፋፋ መሆኑ ይነገራል።
Last Updated (Sunday, 31 January 2010 21:26)
- እርቅን፣ ፍትሕ እና ሰላምን ተግባራዊ ለማድረግ ንጹሕ ልብ፣ አዲስ አመለካከትና ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት
- በሚሊየን የሚቆጠሩ ጽንስ የማስወረድ ሕጋዊነትን ተቃዋሚዎች በስፔን
- ቤተ ክርስትያን የስብከተ ወንጌል ተልእኮ ቀንን አስታውሳ ዋለች
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ ያሰሙት ንግግር
- ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያቀረቡት ሰላምታ
- የሰው ልጅ ሁሉ መመዘኛ ክርስቶስ ነው
- የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ተጀመረ
- ለእውነት ክፍት መሆን ይገባል
- ር.ሊ.ጳ. በሚስዮናዊው መገደል የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ
- የናዝሬቱ ኢየሱስ ላንተ ማነው?
- ጸረ ክርስትያን አመጽ በፓኪስታን
- ጽንስ ማስወረድ የሞት ባህል ነው








