በሚሊየን የሚቆጠሩ ጽንስ የማስወረድ ሕጋዊነትን ተቃዋሚዎች በስፔን
Independent Catholic News - ቅዳሜ ጥቅምት 7 ቀን 2001 ዓ.ም. መንግሥት ጽንስ ማስወረድ የሚመለከተውን የስፔን ሕግ ለማሻሻል ያቀረበውን እቅድ በመቃወም ከአንድ ሚሊየን በላይ የሚሆን ሕዝብ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉ ተዘገበ።
እ.ኤ.አ. ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ እስካሁን በሥራ ላይ ባለው የስፔን ሕግ መሠረት ተገድዶ በመደፈርና አስጊ የሽል ሁኔታዎች ሲከሠቱ ብቻ ውርጃን የሚፈቅድ ሲሆን፤ አካላዊ ወይም ሥነ ልቦናዊ ጤንነትን የሚያሰጋ ሁኔታ ካለም ስፔናዊት ሴት ርግዝናዋን እንድታቋርጥ ይፈቅዳል። ይህ የሁለተኛውን አማራጭበሚመለከት በተግባር ላይ የዋለው ውርጃ ሲታይ ግን እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም. ብቻ 112,000 ጽንስ ማጨናገፍ መከናውኑ ታውቋል።
Last Updated (Monday, 26 October 2009 15:41)
ቤተ ክርስትያን የስብከተ ወንጌል ተልእኮ ቀንን አስታውሳ ዋለች
ራድዮ ቫቲካን - ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ትናንት እሑድ ከሐዋርያዊ አዳራሽ መስኮት በመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡት በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩት ምእመናን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመድገማቸው በፊት ዕለቱ የስብከተ ወንጌል ተልእኮ ቀን የሚዘከርበት እሁድ መሆኑን አስታውሰው፣ ቤተ ክርስትያን ለመላው ሰው ዘር ወንጌልን መስበክ እንደሚጠበቅባትና ቤተ ክርስትያን የምትኖረው የወንጌል የተስፋ መልእክትን ለማስተላለፈ መሆኑን አሳስበዋል። በቅርቡ በብራዚል የተገደሉት ልኡከ ወንጌል ኣባ ሩቮለቶ እና በፊሊፒንስ የታገቱት አባ ሲኖት በማስታወስም በጸሎት እና በመንፈስ እንደሚዘክሩዋቸው አረጋገጠዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ ያሰሙት ንግግር
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ ለአፍሪቃ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ በእንግድነት ተገኝተው ንግግር ማሰማታቸው ከሲኖዶስ አዳራሽ የተላለፈልን ዜና ገለጸ።Last Updated (Thursday, 08 October 2009 19:29)
- ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያቀረቡት ሰላምታ
- የሰው ልጅ ሁሉ መመዘኛ ክርስቶስ ነው
- የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ተጀመረ
- ለእውነት ክፍት መሆን ይገባል
- ር.ሊ.ጳ. በሚስዮናዊው መገደል የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ
- የናዝሬቱ ኢየሱስ ላንተ ማነው?
- ጸረ ክርስትያን አመጽ በፓኪስታን
- ጽንስ ማስወረድ የሞት ባህል ነው
- ልጇን ሁለት ጊዜ የወለደች እናት - ቅድስት ሞኒካ
- እያንዳንዱ ስደተኛ የማይገረሰስ መሠረታዊ መብት ያለው ሰው ነው!
- በክርስቶስ ትምህርት ዛሬም ሰዎች ይደናቀፋሉ
- ዝክረ ቅዱስ በርናርዶስ ዘኪያራቫሌ









