ቤተ ክርስትያን የስብከተ ወንጌል ተልእኮ ቀንን አስታውሳ ዋለች
ራድዮ ቫቲካን - ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ትናንት እሑድ ከሐዋርያዊ አዳራሽ መስኮት በመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡት በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩት ምእመናን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመድገማቸው በፊት ዕለቱ የስብከተ ወንጌል ተልእኮ ቀን የሚዘከርበት እሁድ መሆኑን አስታውሰው፣ ቤተ ክርስትያን ለመላው ሰው ዘር ወንጌልን መስበክ እንደሚጠበቅባትና ቤተ ክርስትያን የምትኖረው የወንጌል የተስፋ መልእክትን ለማስተላለፈ መሆኑን አሳስበዋል። በቅርቡ በብራዚል የተገደሉት ልኡከ ወንጌል ኣባ ሩቮለቶ እና በፊሊፒንስ የታገቱት አባ ሲኖት በማስታወስም በጸሎት እና በመንፈስ እንደሚዘክሩዋቸው አረጋገጠዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ ያሰሙት ንግግር
ቫቲካን ሬድዮ
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ ለአፍሪቃ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ በእንግድነት ተገኝተው ንግግር ማሰማታቸው ከሲኖዶስ አዳራሽ የተላለፈልን ዜና ገለጸ።
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ ለአፍሪቃ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ በእንግድነት ተገኝተው ንግግር ማሰማታቸው ከሲኖዶስ አዳራሽ የተላለፈልን ዜና ገለጸ።የፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ ንግግር:- "በስም አብ ወወልድ ወንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፣...
Last Updated (Thursday, 08 October 2009 19:29)
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያቀረቡት ሰላምታ
ቫቲካን ሬድዮ
ቅ. አ. ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ በቫቲካን በመካሄድ ላይ ባለው ሁለተኛው ይፋዊ የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ በእንግድነት በመሳተፍ ላይ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ለብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ ለየት ባለ መልክ ሰላምታ ሲያቀርቡ፣ “በዚህ የአፍሪቃው ሁለተኛ በእንግድነት እንዲሳተፉ ያቀረብኩሉዎትን ጥሪ ተቀብለው አወንታዊ ምላሽ ሰጥተው እዚህ በመገኘትዎት በእኔ እና በሁለተኛው የአፍሪቅ ብፁዓን ጳጳሳት አበው ስም ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርብልዎታለሁ። የእርስዎ እዚህ መገኘትም የአፍሪቃ ጥንታዊት እና በባህል ሃብታም ለሆነቸው ቤተ ክርስትያን አንደበተ ርቱዕ እና ስሜት የሚነካ ሕያው ምስክርነት ነው። በግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ 8 ከቁጥር 26 እስከ 40 እንደምናነበው በሐዋርያት ጊዜ የክርስቶስ የድህነት መልእክት ቀርበው ከሐዋርያት አንደበት ያዳምጡ ከነበሩት አሕዛብ ውስጥ ከኢትዮጵያ የመጡ ጭምር ይገኙባቸው እንደነበርም እንረዳለን፣ የዚህ ሕዝብ ለወንጌል ያለው ታማኝነት አሁንም ቀጣይ ሆኖ ለእግዚአብሔር የፍቅር ትእዛዝ ታዛዥ መሆኑ እና እርስዎም ቀድመው እንዳሉት ይኽ ሕዝብ ስደትና መከራን ተሻግሮ ስለ ክርስቶስ ሰማዕትነትንም በመቀበል እምነቱን በመመስከር እምነቱን ጠብቆ ይኖራል”።...

More Articles...
- የሰው ልጅ ሁሉ መመዘኛ ክርስቶስ ነው
- የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ተጀመረ
- ለእውነት ክፍት መሆን ይገባል
- ር.ሊ.ጳ. በሚስዮናዊው መገደል የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ
- የናዝሬቱ ኢየሱስ ላንተ ማነው?
- ጸረ ክርስትያን አመጽ በፓኪስታን
- ጽንስ ማስወረድ የሞት ባህል ነው
- ልጇን ሁለት ጊዜ የወለደች እናት - ቅድስት ሞኒካ
- እያንዳንዱ ስደተኛ የማይገረሰስ መሠረታዊ መብት ያለው ሰው ነው!
- በክርስቶስ ትምህርት ዛሬም ሰዎች ይደናቀፋሉ
- ዝክረ ቅዱስ በርናርዶስ ዘኪያራቫሌ
- ካህን የልዕልትና ትሑት እናት የተወደደ ልጅ