ንኡሳን ገጾች
Chaplet of Divine Mercy
Home (ቅድመ ገጽ)

በቅርብ የተጨመሩ ጽሑፎች

የናዝሬቱ ኢየሱስ ላንተ ማነው?

Independent Catholic News - ኢየሱስ መንገድን ሊያሳየን ያውም ወደ ሕይወት የሚያደርሰን መንገድን እንጂ ፍልስፍና ሊያስተምረን አልመጣም፤ ይህ መንገድ የእውነተኛ እምነት መገለጫ የሆነው ፍቅር ነው" በማለት ነበር ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው ከካስተልጋንዶልፎ ባለፈው እሑድ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አስተምህሯቸው መጀመሪያ ላይ የዕለቱን ወንጌል መልእክት ማካፈል የጀመሩት።

በመቀጠልም "የእግዚአብሔር ቃል ሁለት ወሳኝ ጥያቄዎችን ያቀርብልናል፦ የናዝሬቱ ኢየሱስ ላንተ ማነው? የሚልና እምነትህ ተግባራዊ ሆኗል ወይስ አልሆነም? የሚለው ናቸው።" ካሉ በኋላ ር.ሊ.ጳ.

Last Updated (Tuesday, 22 September 2009 22:39)

 

ጸረ ክርስትያን አመጽ በፓኪስታን

ቫቲካን ሬድዮ - ባለፈው ዓርብ በፓኪስታን ፑንጃብ መንደር ሙስሊሞች የዓርብ ጸሎት አድርሰው በመመለስ ላይ እያሉ በማበር ባንድ ክርስትያን ምእመን እና ባንዲት ሙስሊም መካከል የተፈጠረው ወዳጅነት እና ፍቅር በመቃወም በክልሉ አቅራቢያ የሚገኘውን ቤተ ክርስትያን በእሳት ማጋየታቸው ሲገለጥ፣ በዚህች አገር አክራሪያን ሙስሊሞች በተከታታይ የሚፈጽሙት ጸረ ክርስትያን አመጽ ገና እንዳልተገታ ለማወቅ ተችሏል።

በመቀጠልም አክራሪያኑ...

Last Updated (Saturday, 19 September 2009 13:23)

 

ጽንስ ማስወረድ የሞት ባህል ነው

ቫቲካን ሬድዮ - በአሜሪካ የቦስቶን ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ሲን ፓትሪክ ኦማለይ ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ የአሜሪካ የጤና ጥበቃ ጉዳይ ለማደስ የወጠኑት እቅድ ጽንስ ማስወረድ ለሚደረገው የሕክምና ስልት ድጋፍ የሚሰጥ እንዳይሆን በማለት በአሜሪካ የምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያንን አመለካከት ባለፈው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቴድ ኬኔዲ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመሩበት ዕለት ባሰሙት ስብከት ገልጠዋል።

የሕክምና አገልግሎት ሁሉን አቀፍ ይሆን ዘንድ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ዘወትር የሚያቀርቡት ጥሪ እና ከጤና ጥበቃ ጉዳይ የሚገለል ማንም የኅብረተሰብ ክፍል ሊኖር እንደማይገባው በተከታታይ ያቀረቡት ሀሳብ መሆኑን ብፁዕ ካርዲናል ሲን ፓትሪክ ኦማለይ ዳግም ገልጠው፤ ጽንስ የማስወረድ ጸረ ሕይወት ተግባርን የሚደገፍ መመሪያን  ቤተ ክርስትያን መቼም ቢሆን ከመቃወም ወደ ኋላ እንደማትል አስታውቀዋል።

Last Updated (Thursday, 10 September 2009 23:04)

 
የሳምንቱ መልእክት
"ለሰው ይኽን ያህል ታላቅ ክብር ለመስጠት ያነሳሳህ ምን ይሆን?...ወደር የሌለው ፍቅርህ እንደሆነ አይጠረጠርም! በፍቅሩ ተማርከሃል፤ በአውነትም በፍቅር ፈጥረኸዋል፤ በፍቅርም ዘላለማዊ መልካምነትህን የሚያጣጥም ስብእናን ለግሰኸዋል።" ቅድስት ካተሪና ዘሲየና
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ያን መዝሙሮች (ብዛት 110!)
ባለፉት 12 ሰዓታት የጎብኚዎች አገር
Top 6:
Ethiopia flag 27%Ethiopia (3)
United States flag 27%United States (3)
Russian Federation flag 18%Russian Federation (2)
Canada flag 9%Canada (1)
Moldova, Republic of flag 9%Moldova, Republic of (1)
Switzerland flag 9%Switzerland (1)
11 visits from 6 countries