ሦስት ሺህ ሰዎችን በማዳናቸው ሚሲዮናዊው ተመሰገኑ
(Independent Catholic News) - እ.ኤ.አ. በ1994 ዓ.ም. በሩዋንዳ 800,000 ሰዎችን ሰለባ ባደረገው የጅምላ ጭፍጨፋ ወቅት ሌሎችን ከሞት ለመታደግ ላደረጉት ትልቅ አስተዋፅኦ ባለፈው ሳምንት ታላቅ አክብሮት ከተቸራቸው አሥር ሰዎች መካከል አንድ ጣልያናዊ ሚሲዮናዊ አንዱ መሆናቸው ታውቋል።
ግብረ ጥንቆላን በመቃወሙ የተገደለው አስተማሪ ቅድስና
(Independent Catholic News) - ከዛሬ 19 ዓመታት በፊት የጥንቆላን ነገሮች በመቃወሙ የተገደለው ደቡብ አፍሪካዊ ካቶሊክ መምህር ቤኔዲክት ዳስዋ የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው ቅዱስ የመሆን ሂደት ላይ መሆኑ ተዘገበ።
ብፅዕናው ይታወጅ ዘንድ የሚያግዙ 850 ገጽ ያላቸው ሰነዶች ከአምስት ዓመት በላይ ሲዘጋጁ ቆይተው የተከናወኑ ሲሆን የቅድስና ጉዳይን ወደ ሚመለከተው የቫቲካን ክፍል መንበር ኃላፊ ሊቀ ጳጳሳት አንጀሎ አማቶ ተልከዋል። ቀጣዩ ርምጃ የሚሆነው የእግዚአብሔር አገልጋይ ቤኔዲክት ዳስዋ ምስል ማዘጋጀትና በአማላጅነቱም ጸጋን ለማግኘት ጸሎት ማሳተም ይሆናል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የደቡብ አፍሪካ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባዔ ታሪኩን፣ ሥራውንና ሕይወቱን ለማስፋፋት ያግዝ ዘንድ የእሱን አጭር የሕይወት ታሪክና ዲቪዲ እያዘጋጀ መሆኑም ታውቋል።
ቤኔዲክት ባህላዊ እምነት ከነበራቸው ቤተሰቦች ሌምባ ከሚባል አናሳ ጎሣ የተወለደና በዚያው ያደገ ሲሆን፣ ኋላም ባብዛኛው ቬንዳ በምትባል ከተማ ኖሯል። ከነበረው ባህላዊ እምነት ወደ ካቶሊክነት የተለወጠው ለመምህርነት በመማር ላይ ሳለ ነበር።
Last Updated (Wednesday, 22 July 2009 20:39)
አዲስ ሐዋርያዊ ወኪል በኢትዮጵያ - በነቀምት
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ የማኅበረ ልኡካን ማኅበር አባል አባ ቴኦደሩስ ፋን ሩቨን በኢትዮጵያ የነቀምት ሐዋርያዊ ወኪል እንዲሆኑ መሰየማቸውን የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀ።
አባ ቴኦዶሩስ ፋን ሩቨን በኔዘርላንድ የአምስተርዳም ሀገረ ስብከት ሪስቪክ በተባለ ቦታ ግንቦት ሀያ ሁለት ቀን 1938 እ.ኤ.አ. የተወለዱ ሲሆን በ1964 ፓኒንገን በተባለ ቦታ መዓርገ ክህነት የተቀበሉ መሆናቸውን መግለጫው አመልክቷል።
አባ ቴኦዶሩስ መዓረገ ክህነት ከተቀበሉ ከአንድ ዓመት በኋላ በማኅበራቸው አማካይነት ማለትም በማኅበረ ልኡካን (ላዛሪስት) ወደ ኢትዮጵያ የተላኩ እና በሀገሪቱ ውስጥ በተለያዩ የቤተክርስትያን ሐዋርያዊ አገልግሎት የተሰማሩ መሆናቸው መግለጫው በተጨማሪ ገልጧል። እስከ አሁን ድረስም የጂማ ቦንጋ ሐዋርያዊ አሰተዳዳሪ ሆነው መስራታቸው መግለጫው አክሎ ዘግቧል።
Last Updated (Sunday, 23 August 2009 20:42)
- ሥነ ሕይወት በክርስትያናዊ አመለካከት
- ር.ሊ.ጳ. ስለ ኢየሱስ አያቶች
- ር.ሊ.ጳ. የእጅ ስብራት ሕክምና አደረጉ
- በኢራቅ አብያተ ክርስትያናት የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ
- መንፈሳዊ ነገሮች የዓለም አቀፋዊ መቃወስ የመፍትሔ ክፍል
- ንጽሕና፣ ድንግልና ክብረ ንጽህና
- “ካሪታስ ኢን ቨሪታቴ - ፍቅርን በእውነት” - አዲሱ ዓዋዲ መልእክት
- ሰዎች ሕይወት ቅዱስ መሆኑን የሚያውቁት መች ይሆን?
- መሃይምነትን በማጥፋት ክርስቶሳዊ እውነትን መመስከር
- ዓመተ ሐዋርያ ጳውሎስ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የመዝግያ ሥርዓት ተፈጸመ፡
- ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንዲሰፍን በድጋሚ አሳሰቡ
- ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን ካህናት ያስፈልጓታል









