ንኡሳን ገጾች
Chaplet of Divine Mercy
Home (ቅድመ ገጽ)

በቅርብ የተጨመሩ ጽሑፎች

ር.ሊ.ጳ. የእጅ ስብራት ሕክምና አደረጉ

(ZENIT.ORG/Ewtn.com) - ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው ለዕረፍት በተጓዙበት በሰሜን ጣልያን በሚገኘው አኦስታ ሐምሌ 9 ቀን ምሽቱ ላይ በደረሰባቸው ቀላል የመውደቅ አደጋ የእጅ ስብራት ያጋጠማቸው ሲሆን እዚያው በሚገኘው ኡምቤርቶ ፓሪኒ በሚባል ሆስፒታል ቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው ከቫቲካን የወጣው ዘገባ ገለጸ።
የቫቲካን ማስታወቂያ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ኢየሱሳዊ አባ ፈዴሪኮ ሎምባርዲ ሁኔታውን ሲያስረዱ ር.ሊ.ጳ. ቀዶ ሕክምናውን ለማድረግ ወደ ሆስፒታል ከማምራታቸው በፊት በጠዋቱ ቅዳሴያቸውን ቀድሰውና ቁርስ አድርገው ነበር ካሉ በኋላ ለር.ሊ.ጳ. ቀላል የቀዶ ጥገና ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ የቀኝ እጃቸው መታሸጉን ገልጸዋል።

ከጠዋቱ 3:45 በሆስፒታሉ ሲደርሱ ር.ሊ.ጳ. ራጅ ለመነሣት ከርሳቸው ቀድመው የነበሩትን ሰዎች ተራ አክብረው መጠበቅን የመረጡ መሆኑንና በኋላም የቀዶ ጥገና ሕክምናው 20 ደቂቃ የፈጀ እንደነበር ታውቋል። የግል ሐኪማቸው ፓትሪሲዮ ፖሊስካ ር.ሊ.ጳ. በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም አሳውቀዋል።

ር.ሊ.ጳ. ቢኔዲክቶስ የ16 ቀን ዕረፍት ለማድረግ ወደ አኦስታ የተጓዙት ያለፈው ሐምሌ 6 ቀን መሆኑ ይታወሳል።


 

 

Last Updated (Sunday, 23 August 2009 20:45)

 

በኢራቅ አብያተ ክርስትያናት የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ

(ቫቲካን ራድዮ) ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ በቅርቡ በኢራቅ ክርስትያን የአምልኮ ሥፍራዎች ላይ የተፈጸመው የጥቃት ተግባር በእጅጉ እንዳሳዘናቸው ገልጠው፣ ይህ ዓይነቱ የአመጽ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም የኢራቅ መንግሥት ባለ ሥልጣናትን በአጽንኦት አሳሰቡ።

የአመጹ ተግባር ሆን ብሎ የተደረገ ወንጀል ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል። ቅዱስነታቸው በቅ. መንበሩ ዋና ጸሓፊ በብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ በኩል ወደ ከለዳዊት ባቢሎን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አማኑኤል ደሊ ሦስተኛ በላኩት መልእክት የአመጹ ጠንሳሾች ልብ እንዲለወጥ ጸሎት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጠው፣ በመንፈስም ከኢራቁ ካቶሊካዊ እና ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረ-ሰብ ጎን መቆማቸውን አረጋግጠዋል።

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በመልእክታቸው የኢራቅ መንግሥት ባለሥልጣናት ለሁሉም የኢራቅ ዜጎች አብሮ ተቻችሎ በሰላም መኖርን እና ፍትሕን እንዲያሰፍኑ የተቻላቸውን ሁሉ እንዲጥሩ መክረዋል። 

 

መንፈሳዊ ነገሮች የዓለም አቀፋዊ መቃወስ የመፍትሔ ክፍል

(Catholic News Service) --ዘርፈ ብዙ ለሆነው ለዓለም ችግር መፍትሔ ቁሳዊ ነገሮችን ማሟላት ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ የሰዎች ሰብአዊና መንፈሳዊ ፍላጎቶችንም መሟላት እንደሚያስፈልግ ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው አስገነዘቡ።

ሐምሌ 5 ቀን በቅ.ጴጥሮስ ባደረጉት የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አስተምህሮ ላይ "ለቴክኖሎጂ በጣም የሰፋ ቦታ መስጠቱ ትልቁ መገለጫ በአንዳንድ ተግባራት ላይ የሰውን ልጅ ሕይወት መቃወም መሆኑ ለወደፊቱ የሰብአዊ ሁኔታ ጥሩ ያልሆነ ገጽታን ፈጥሯል" ካሉ በኋላ በጣልያን ላኩይላ ተሰብስበው የነበሩትን በኢንደስትሪ የበለፀጉ የሚባሉትን ቡድን ስምንት መሪዎች በተመለከተም "የነፍስና አካል ባለቤት የሆነውን ሰው ግምት ውስጥ ካላስገባ በስተቀር ለወቅታዊው ሰብአዊ ችግሮች ቴክኖሎጂ ብቻውን መፍትሔ አይሆንም" ብለዋል። 

"በዓለም ያለው ማኅበረሰባዊ የበላይነትና የበታችነት እንዲሁም መዋቅራዊ ኢፍትሐዊነት በቸልታ ሊታለፍ የሚገባው ጉዳይ አይደለም፤ አስቸኳይና ተገቢ ርምጃ ያስፈልጋቸዋል ብቻም ሳይሆን ሁሉን አቀፍ መፍትሔን ለማምጣት የተቀነባበረ እቅድ ያሻቸዋል" በማለት አሳስበዋል።

Last Updated (Saturday, 18 July 2009 00:48)

 
የሳምንቱ መልእክት
"ለሰው ይኽን ያህል ታላቅ ክብር ለመስጠት ያነሳሳህ ምን ይሆን?...ወደር የሌለው ፍቅርህ እንደሆነ አይጠረጠርም! በፍቅሩ ተማርከሃል፤ በአውነትም በፍቅር ፈጥረኸዋል፤ በፍቅርም ዘላለማዊ መልካምነትህን የሚያጣጥም ስብእናን ለግሰኸዋል።" ቅድስት ካተሪና ዘሲየና
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ያን መዝሙሮች (ብዛት 110!)
ባለፉት 12 ሰዓታት የጎብኚዎች አገር
Top 5:
United States flag 36%United States (4)
Ethiopia flag 27%Ethiopia (3)
Russian Federation flag 18%Russian Federation (2)
Moldova, Republic of flag 9%Moldova, Republic of (1)
Switzerland flag 9%Switzerland (1)
11 visits from 5 countries