ንኡሳን ገጾች
Chaplet of Divine Mercy
Home (ቅድመ ገጽ)

በቅርብ የተጨመሩ ጽሑፎች

ንጽሕና፣ ድንግልና ክብረ ንጽህና

(ቫቲካን ሬድዮ) -2009-07-08- ከትላትና በስትያ በላቲን ሥርዓት የተከበረው የቅድስት ማሪያ ጎረቲ ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት ይህች ሰማዕት ቅድስት በተወለደችበት በኢጣሊያ በላቲና አውራጃ የምትገኘው የፈሪየረ ከተማ ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማሪያኖ ክሮቻታ ባሰሙት ስብከት “ንጽሕና ድንግልና ክብረ ንጽህና ጉዳይ በተመለከተ ይቅር ለመናገርና ለማሰቡም የማይፈቅድ፣ እነዚህን ነገሮች ማሰብ ኋላ ቀርነትን የሚገልጥ ማለት እንደሆነ በሚያስተምረው ባህል በተስፋፋበት በአሁኑ ዓለም፣ ምንም ትርጉም የሌላቸው ሆነው ከማኅበረሰብ ማኅበራዊ መዝገበ ቃላት ውጭ በመሆን፣ በዚህ የሐሰት ስድና ልቅ ነጻነት የሚሰበክበትና ሁሉም ይኸንን አመለካከት ተግባራዊ ለማድረግ መራወጥ ማለት በኃላፊነት ላይ ያልጸና ነጻነት-ባርነት መኖር ነው፣ የእኔ ሕይወት የግሌ ነው፣ ስለዚህ በግሌ የፈለግኩትን ባደረግ የራሴ ጉዳይ ነው እየተባለ ትሕትናና አወንታዊ አፍረት ተወግዶ ራስን በትክክል መውደድ ከዕለታዊው ኑሮ ውጭ እየሆነ ነው” ብለዋል።

Last Updated (Thursday, 09 July 2009 07:11)

 

“ካሪታስ ኢን ቨሪታቴ - ፍቅርን በእውነት” - አዲሱ ዓዋዲ መልእክት


ቅዱስ አባታችን ቤኔዲክቶስ 16ኛው

 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው በቤተክርስትያን፣ በሥነ ቁጠባ እና በሥነ ምግባር መካከል ያለውን ግኑኝነት የሚዳስስ “ካሪታስ ኢን ቨሪታቴ” ማለትም "ፍቅርን በእውነት"  በሚል ርዕስ የደረሱት ዓዋዲ መልእክት (encyclical letter) ነገ በይፋ ለንባብ እንደሚቀርብ ተገለጠ።

 

ቤተክርስትያን እና ሥነ ቁጠባ ለመጪው የዓለም ሥነ ቁጠባዊ ትስስር ያለው ኃላፊነትን በልዩ የሚያብራራ፣ ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ታህሳስ 23 ቀን 1985 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ሆነው ከመሾማቸው በፊት እዚህ ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ ኡርባኒያኑም መንበረ ጥበብ (የልኅቀት ማእከል - ዩኒቨርስቲ) ተገኝተው የሰጡት አስተምህሮ እ.ኤ.አ. በ1986 ዓ.ም. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ኮሙኒዮ ዩኤስኤ በተሰኘው መጽሔት ታትሞ በኢጣሊያ በ 2009 ዓ.ም. ዳግም የታተመውን የሚያንጸባርቅ ሥነ አመለካከት ዋቢ ያደረገ መሆኑም ተገልጧል።

ዓዋዲ መልእክቱም ቤተ ክርስትያን እና ሥነ ቁጠባ በሚል ርእስ ሥር ለዓለም ማኅበረሰብ እጅግ አስጊ የሆነው እና ለአደጋ የሚያጋልጠው በሰሜንና በደቡብ የዓለማችን ክፍል ያለው ያልተመጣጠነ የእድገት ልዩነት ምንኛ አደገኛና ህልውናን የሚቀናቀን መሆኑ በስፋት ተብራርቶ ለመፍትሔውም ተግባራዊ ለማድረግ አስቸጋሪ መስሎ የሚታየው ሥነ ምግባራዊ ተሃድሶ ወሳኝ መሆኑን ያበክራል። ምናልባት ቤተ ክርስትያን እና ሥነ ቁጠባ ምን ያገናኛቸዋል የሚል ተገቢ ጥያቄ ሊነሣ ይችላል፣ ሆኖም ግን ቤተ ክርስትያን በዚህ ምድር የምትጓዝ በማኅበራዊ፣ ሥነ ቁጠባዊና ፖለቲካዊ ተጨባጭ ጉዳዮች እውነትን መሠረት የሚያደርግ ግኑኝነት እንዳላት መገንዘቡ አስፈላጊ ነው።

 

Last Updated (Tuesday, 14 July 2009 20:34)

 

ሰዎች ሕይወት ቅዱስ መሆኑን የሚያውቁት መች ይሆን?

  ቫቲካን ራድዮ - (2009-07-07) - ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እሁድ ዕለት እኩለ ቀን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመምራታቸው በፊት እና በኋላ ባስተላለፉት መልእክት በዓለማችን በአመጽና በፍትሕ አልቦነት የሚፈሰው ደም ይቁም ሲሉ ተማጥነዋል።

የክርስቶስ ደም እግዚአብሔር ለሰው ዘር ያለው ታማኝ ፍቅር ዋስትና ነው። በምድራችን በተለያዩ ክፍሎች የሚፈሰው ደም ለሚያሰማው የጩኸት ድምፅ እግዚአብሔር መልስ የሚሰጠው በልጁ ደም ነው።

የመጨረሻ የስቃይ ጩኸት ድምፅ የሰማነው ዛሬ ጠዋት በፊሊፒንስ አገር በኮታባቶ ካተድራል በራፍ በፈነዳውና የብዙ ሰው ሕይወት ባጠፋው የግብረ ሽበራ የጥፋት ድርጊት ሰበብ የተፈጠርው ነው በማለት ስለ አደጋው የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገልጸው የሽበራ ድርጊት የችግር መፍትሔ አለመሆኑን በማረጋገጥ በአጽንኦት የአምጹን ተግባር ኮንነዋል።

Last Updated (Thursday, 09 July 2009 07:10)

 
የሳምንቱ መልእክት
"ለሰው ይኽን ያህል ታላቅ ክብር ለመስጠት ያነሳሳህ ምን ይሆን?...ወደር የሌለው ፍቅርህ እንደሆነ አይጠረጠርም! በፍቅሩ ተማርከሃል፤ በአውነትም በፍቅር ፈጥረኸዋል፤ በፍቅርም ዘላለማዊ መልካምነትህን የሚያጣጥም ስብእናን ለግሰኸዋል።" ቅድስት ካተሪና ዘሲየና
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ያን መዝሙሮች (ብዛት 110!)
ባለፉት 12 ሰዓታት የጎብኚዎች አገር
Top 6:
Ethiopia flag 27%Ethiopia (3)
United States flag 27%United States (3)
Russian Federation flag 18%Russian Federation (2)
Canada flag 9%Canada (1)
Moldova, Republic of flag 9%Moldova, Republic of (1)
Switzerland flag 9%Switzerland (1)
11 visits from 6 countries