ቱርክ ውስጥ አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲይን ጳጳስ ተገደሉ።
Independent Catholic News -Thursday, June 3, 2010 - እስከንደሩን በምትባለው አንዲት የቱርክ ከተማ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ሉዪጂ ፓዶቨዜ (63 ዓመት ዕድሜ) በትላንትናው ዕለት በስለት ተወግተው መገደላቸው ታወቀ። በሜዲትራንያን ወደብ አጠገብ በሚገኘው የበጋ መኖሪያ ቤታቸው ጓሮ ውስጥ በነበሩበት ወቅት ከአራት ዓመታት በላይ መኪና በማሽከርከር ያገለግላቸ በነበረው ሰው ጥቃቱ የተፈጸመባቸው መሆኑም ተገልጿል። የቱርክ ባለሥልጣናት ይህ ሁኔታ ጸረ ክርስቲያን ጥላቻዊ አቋምን ያለመ አይደለም ብለዋል። የቱርክ ፖሊስ ገዳዩን በእስር የያዙት ሲሆን ሰውየው ያልተረጋጋ አእምሮ ያለውና ከበድ ያለ ሥነ ልቦናዊ ችግር ውስጥ መሆኑን አሳውቀዋል።
ትውልደ ጣልያን የሆኑት አቡነ ፓዶቬዘ በአናቶሊያ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ እንደራሴና የቱርክ ጳጳሳት ጉባኤ ኀላፊ የነበሩ ሲሆን ከጥቃቱ በኋላ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል በመወሰድ ላይ ሳሉ ነበር ነፍሳቸው ያለፈችው። ር.ሊ.ጳ. በቆጵሮስ በሚያደርጉ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለአጃቢነት ወደዚያው ሊያመሩ በዝግጅት ላይ ነበሩ።
Last Updated (Friday, 04 June 2010 22:31)
"ምእመናን ሁሉ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ጸሎት እንዲያደርጉ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡" - አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን
መግቢያ
ከሁሉ አስቀድሜ ይህ ፕሮግራም በመዘጋጀቱ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ስም የተሰማኝን ደስታ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ "ከችግር መላቀቅ፤ የምግብ ዋስትና ማግኘት፤ ቋሚ ሥራ ማግኘት፤ ኃላፊነቶችን ያለ አድሎ መካፈል፤ ከጭቆና ሁሉ ነጻ መሆን፤ ሰብአዊ ክብሮችን ተከብሮ መኖር፤ የትምህርት ዕድል ማግኘት፤ የመኖር ዋስትናው ተጠብቆ መኖር፤ በአጠቃላይ የተሻለ ኑሮ መኖር" የኢትዮጵያ ሕዝቦች ምኞት ነው (የሕዝቦች እድገት 6)፡፡ "እያንዳንዱ ዜጋ መሪዎቹን መምረጥ የራሱ መብትና ኃላፊነት መሆኑን በማወቅ የመምረጥ መብቱን ተጠቅሞ ለሕዝቦች የጋር ጥቅም አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅበታል፤ ለሕዝብ አገልግሎት ራሳቸውን ለመሠዋት እጩ አድርገው የፖለቲካ ሸክም ለመሸከም የሚወዳደሩ ግለሰቦችን በአክብሮት እንመለከታለን" (ቤተክርስቲያን በዘመናችን 75)፡፡
1/ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት፡ በተቻለ መጠን በተለያዩ ፓርቲዎች መካከል ያሉ የምርጫ ልዩነቶችን ለማጥበብ የማያቋርጥ የመግባባት ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል ብለን እናምናለን፡፡
2/ የኃይል አጠቃቀምን ማስቀረት፡ በምርጫ ወቅትና በኋላም መራጮች ሆኑ ሥነ ሥርዓት አስከባሪዎች የኃይልና የአመጽ አጠቃቀምን ጨርሶ ማስቀረት፡፡ በአጠቃላይ የሰው ክቡርነት ከሀሳብ ልዩነታችን በላይ መሆኑን አውቀን ለሰላም የሚቻለውን ዋጋ መክፈል ተፈጥሮአዊ ግዴታችን ነው፡፡......
Last Updated (Friday, 04 June 2010 22:36)
እግዚአብሔርን በቍርጠኝነትና በታማኝነት ማገልግል ያስፈልጋል።
Last Updated (Saturday, 05 June 2010 19:45)
- የብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ቅብዓተ ጵጵስና ተከናወነ
- የሆሳዕና ሃገረስብከት ምስረታ በታላቅ ድምቀት ተከበረ - የሃገረስብከቱ አዲስ ጳጳስ ቅብዓተ ጵጵስና ተከናወነ
- የሰሙነ ሕማማት ትርጉም
- ፕሬዚዳንት ግርማ የካሪታስ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንትን አነጋገሩ
- ኃጢአትን መቋወም ኃጢአተኛን ግን መንከባከብ አለብን
- ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው የሱዳን ጳጳሳትን አመሰገኑ
- ቤተ ክርስቲያን የዘር አድልዎ እና ፍትሕ አልባነትን ትቃወማለች
- የገዛ ራስህን ድካም መገንዘብ
- ስቃይ መልስ የለውም ማለት ትርጉም የለውም ማለት አይደለም!
- ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ላይ የግድያ ሙከራ ያደረገው ቱርካዊ ከማረምያ ቤት ወጣ
- የልደተ ክርስቶስ ድባብ በቫቲካን መንበረ ጴጥሮስ
- ተስፋችን እግዚአብሔር ነው









