በሃማኖቶች መካከል በመደረግ ላይ ያለው ግኑኝነት
በካቶሊክ እና በሂንዱ ሃይማኖት መካከል ለሚካሄደው ግኑኝነት አንድ አዲስ ምዕራፍ መከፈቱ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚካሄደውን ግኑኝነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊ ቱራን በህንድ ሓዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው በተመለሱበት ወቅት ይፋ ማድረጋቸው ተገለጠ።
ብፁዕ ካርዲናል ቱራን በህንድ ኦሪሳ ክልል አክራሪያን የሂንዱ ሃይማኖት ምእመናን ጸረ ክርስትያን አመጽ ከማነሳሳታቸው ቀደም ብሎ እ.ኤ.አ. ባለፈው 2008 ዓ.ም. ሓዋርያዊ ጉብኝት አካሂደው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ የሂንዱ አክራሪያን ጸረ ክርስትያን አመጽ መሠረታዊው ምክንያት ለይቶ ለማወቅ ብፁዕ ካርዲናል ታውራን የሂንዱና የካቶሊክ ሃይማኖት ዓበይት መንፈሳዊ መሪዎች ጋር በመገናኘት ሀሳብ ለሀሳብ እንዲለዋወጡ ያቀረቡት ጥሪ እ.ኤ.አ. ባለፈው ሰኔ 12 ቀን 2009 ዓ.ም. በህንድ ቦምበይ ከተማ ዝግ በሆነ ጉባኤ እውን መሆኑ ተገልጠዋል።
Last Updated (Thursday, 09 July 2009 07:25)
ፍቅር “ይኖራል፣ በመኖሩም ነገሮችን ይለውጣል”

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትናንት እሁድ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመምራታቸው በፊት ዕለቱ በዛ ባሉት አገሮች ኮርፑስ ዶሚኒ በዓለ (ቅዱስ ቍርባን) ተከብሮ የሚውልበት ቀን መሆኑን አስታውሰው መላው ዓለም በረሃብ በመሰቃየት ላይ ያሉትን በሚሊዮናት የሚገመቱ ሕዝቦች ጉዳይ መረሳት እንደሌለበት አሳሰቡ።
ቅዱስነታቸው በፊታችን ሰኔ ሃያ አራትና ሃያ ስድስት በኒዮርክ ስለ ምጣኔ ሃብትና ገንዘብ መቃወስ ችግር መፍትሔ ለመሻት ሊካሄድ ታቅዶ ያለውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባኤ ጠቅሰው የረሃቡ ክስተት ጉዳይ ጨርሶ ተቀባይነት የሌለው ምክንያት አልባ ክስተት መሆኑን አስጠነቅቀዋል። በመጨረሻም ምእመናን በፊታችን ዓርብ ስለ ሚጀመረው የክነት ዓመት እንዲጸልዩ ጠይቀዋል።
Last Updated (Thursday, 09 July 2009 16:29)
ዓመተ ክህነት
የፊታችን ዓርብ እ.ኤ.አ. ሰኔ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓት የቅዱስ ልበ ኢየሱስ በዓል በሚከበርበት ዕለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ በሚመሩት ጸሎተ ሠርክ የክህነት ዓመት በይፋ ይከፍታሉ።
ይህ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሚያወጁት ዓመተ ክህነት፣ ካህናት የተጠሩበት ዓላማ ፍሪያማነቱና አጥጋቢነቱ ወደ ሚያጸናው መንፈሳዊው ፍጽምና ያቀኑ ዘንድ በማሰብ ባለፈው ዓመት የክህነት ዓመት ባወጁበት ዕለት መግለጣቸው የሚዘከር ነው። ስለዚሁ እፊታችን ዓርብ የሚጀመረው ዓመተ ክህነት በማስመልከት የቅድስት መንበር የዜናና የማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረድዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ሎምባርዲ፣ “ካህናት ጸላያን መሆን ይገባቸዋል፣ መጸለይ እንደሚገባቸው ማስታወስ ይኖርባቸዋል በማለት ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አበክረው ካህናትን በሚቀበሉበት ወቅት ቅዱስ መቍጠርያም በሚሰጡበት ወቅት የሚያቀርቡትን ጥሪ ለዚህ ዓመተ ክህነት መሠረት ነው” ብለዋል። “ዓመቱም የካህናት ጠባቂና አብነት የሆነው ቅዱስ ዮሓንስ ዘ ማርያም ቪያነይ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየበት 150ኛው ዓመት የሚዘከርበት ዓመት በመሆኑም ያስተላለፉትን አደራ ዓቢይና ጥልቅ ትርጉም የሚያሰጠው ነው” ብለዋል።
Last Updated (Thursday, 09 July 2009 07:26)
- የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የዕለተ ሮቡዕ አስተምህሮ (እ.አ.አ. ሰኔ 10 ቀን 2009)
- የብፁዕ አቡነ ኪዳነማርያም ጸሎተ ፍትሐት
- ከሁለት ሳምንታት በኋላ ዓመተ ክህነት መከበር ይጀመራል፡
- ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቼክ ሬፐብሊክን ይጐበኛሉ
- የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የዕለተ ሮቡዕ አስተምህሮ (እ.አ.አ. ሰኔ 3 ቀን 2009)
- የኢራቅ ማኅበረ ክርስትያን
- ረዳኢተ ክርስትያን
- ር.ሊ.ጳ የሞንተካሲኖን ገዳም ጐበኙ
- በሮማ አዲስ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን
- አዲሱ የዌስትሚኒስተር ሊቀ ጳጳሳት
- የቫቲካን አዲስ ድረ ገጽ
- የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስተምህሮ









