የሆሳዕና ሃገረስብከት ምስረታ በታላቅ ድምቀት ተከበረ - የሃገረስብከቱ አዲስ ጳጳስ ቅብዓተ ጵጵስና ተከናወነ
የአዲሱ ሆሳዕና ሀገረስብከት ምስረታ ሚያዝያ 3 ቀን 2002 ዓ.ም በሆሳዕና ካቴድራል በታላቅ ድመቀት ተከብሮ ውሏል፡፡ የሃገረስብከቱ የመጀመሪያ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ወልደጊዮርጊስ ቅብዓተ ጵጵስናም በብፁዕ አቡነ ብርሀነየሱስ ሊቀጳጳሳት ካቶሊካውያን ዘኢትዮጵያ እጅ ተከናውኗል፡፡
በዕለቱ ብፁዕ ለቀጳጳሳት ጆርጅ ፓኒኩለም የቫቲካን አምባሳደር በኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት፣ክቡር አባ ፓየስ የአሜሲያ (የምስራቅ አፍሪካ ጳጳሳት ጉባዔ ጠቅላይ ጸሃፊ፣ ክቡር አባ ሐጎስ ሐይሽ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት ጠቅላይ ጸሐፊ፣ የተለያዩ ሃይማኖቶች ተወካዮች፣ ክቡር ዶ/ር ሺፈራው ተ/ማርያም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር፣ ኩቡር አቶ መለሰ አለሙ የሃዲያ ዞን አስተዳዳሪ፣ አቶ ታደሰ ሮሞ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ኣስተዳዳሪ፣ ከመላዋ ኢትዮጵያ፣ ከሆሳዕናና አካባቢዋ የተውጣጡ፣ ካህናት፣ ደናግልና ምዕመናን እንዲሁም የብፁዕነታቸው ቤተሰቦች ተገኝተዋል፡፡
በበዓሉ ላይም በሆሳዕናና በኣካባቢዋ የስብከተ ወንጌል እንዴት እንደተጀመረና እንደተስፋፋ የሚያብራራ አጭር ታሪካዊ ዘገባ ቀርበዋል፡፡...
Last Updated (Wednesday, 19 May 2010 21:42)
የሰሙነ ሕማማት ትርጉም
|
ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ ቀይ ልብስም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ። ጲላጦስም:- እነሆ ሰውዬው አላቸው። ዮሐ.19:5-6 |
አንድ አፈ ታሪክ ስለ ሁለት ወንድማማቾች ይተርካል። አንደኛው ጥሩ ምግባር የነበረው ሲሆን ሌላኛው ግን ክፋትን ያዘወትር ነበር። አንድ ቀን ክፋትን ያዘወትር የነበረው ወንድም ወደ ቤት በሩጫ መጣ ካባውም በደም ነጠብጣብ ተጨማልቆ ነበር። ቤት እንደገባም እየተረበሸ "አሁን አንድ የዋህ ሰውን ገደልኩ" በማለት ለወንድሙ ነገረው። ባለ መልካም ምግባር ወንድሙም "እንካ፤ አንተ የኔን ነጭ ካባ ልበስ፤ እኔ ደግሞ ያንተን እለብሳለሁ። ከዚያም አንተ ከዚህ አካባቢ ተሰወር" አለው። ወንድሙ እንዳለው አደረገና ገዳዩ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ። ወዲያውም ወደዚያ ቤት ወንጀለኛውን ለማሰር የመጡት ሰዎች በደም የተጨማለቀ ካባ የለበሰውን ልጅ ወደ እስር ቤት ወሰዱት፤ ወዲያውም የሞት ፍርድ ተፈረደበት። ልክ ከመሞቱ በፊት ለገዳይ ወንድሙ መልእክት ላከለት፤ እንዲህም አለው "የሰጠሁህን ነጭ ካባ አስታውስ፤ እኔ አንተን ለማዳን ባንተ ምትክ መሞቴንም እንዳትረሳ"።
ባጭሩ ይህ ጌታችን ለኛ ያደረገውን ይነግረናል፦ የኛን የኃጢአት ካባ እሱ ለበሰው።
"በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፤ ሕመማችንንም ተሸክሟል። በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን"....
ፕሬዚዳንት ግርማ የካሪታስ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንትን አነጋገሩ
አዲስ አበባ, የካቲት 30 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) - ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የካሪታስ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ካርዲናል ኦስካር ሮድሪጌዝ ማራዲጋን በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
ካርዲናል ኦስካር ሮድሪገዝ ማራዲጋዝ ከውይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞች እንዳስታወቁት ውይይቱ በዋናነት ያተኮረው ካሪታስ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ እያከናወነ ባላቸው የልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ ነበር፡፡ በዚህም ድርጅታቸው ኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ያለችውን ልማት የማገዝ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል፡፡
በተለይም በትምህርት ዘርፍ ኢትዮጵያን ለማገዝ በሚያደርገው ጥረት በኢትዮጵያ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ለመገንባት በሂደት ላይ ይገኛል፡፡ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲን በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች የማስፋፋት ፍላጎት አለው ማለታቸውን የዘገበው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ብርሃነየሱስ በበኩላቸው ካሪታስ ኢንተርናሽናል በመላው ዓለም በ162 አገሮች የልማትና የበጎ አድርጎት ተግባራት ላይ እንደሚሳተፍ ገልጸዋል፡፡
- ኃጢአትን መቋወም ኃጢአተኛን ግን መንከባከብ አለብን
- ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው የሱዳን ጳጳሳትን አመሰገኑ
- ቤተ ክርስቲያን የዘር አድልዎ እና ፍትሕ አልባነትን ትቃወማለች
- የገዛ ራስህን ድካም መገንዘብ
- ስቃይ መልስ የለውም ማለት ትርጉም የለውም ማለት አይደለም!
- ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ላይ የግድያ ሙከራ ያደረገው ቱርካዊ ከማረምያ ቤት ወጣ
- የልደተ ክርስቶስ ድባብ በቫቲካን መንበረ ጴጥሮስ
- ተስፋችን እግዚአብሔር ነው
- ማንም ሰው ብቻውን እንዳይሆን፤ ማንም ሰው እንዳይነጠል፤ ማንም ሰው ተጥሎ እንዳይቀር
- በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ የመነኮሳውያት ቁጥር ዕድገት ሕንድ ትመራለች
- በኢራቅ የአናሳ ሃይማኖቶች ህልውና
- እርቅን፣ ፍትሕ እና ሰላምን ተግባራዊ ለማድረግ ንጹሕ ልብ፣ አዲስ አመለካከትና ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት












