የሰማይ ንግሥት ሆይ ለምኝልን!
ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚናገረው ይህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ ካቶሊካዎት ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ መገናኛ መምሪያ ቢሮ በየወሩ ከሚታተመው "ፍቅርና ሰላም" ከተሰኘው ጋዜጣ ግንቦት/ሰኔ 2001 ዓ.ም. እትም "የሰማይ ንግሥት ሆይ ለምኝልን!" ከሚል ርእስ በከፊል የተወሰደ ነው።
"የሰማይ ንግሥት ሆይ ለምኝልን!"
በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ላይ የተገለጸው የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ብሥራት የሚተርከው ማርያም የልዑል እግዚአብሔርን ልጅ እንደምትወልድና እርሱም በብሉይ ኪዳን ስለ መሲሑና ዘላለማዊ መንግሥቱ ተነግሮ የነበረው ተስፋ እንዲፈጸም እንደሚያደርግ ነው። (2ሳሙ.7:፤ መዝ.2:72፣89፤ ሉቃ.1:33)።

ጥንታዊ አይሁዳውያን አንዲት እናት ከዳዊት ዘር የሆነና ወደፊት በንጉሡ ዙፋን ላይ ሊቀመጥ የሚችል (አልጋ ወራሽን) የወለደች እንደሆነ ወዲያውኑ ንግሥት እንደሆነች አድርገው ይቀበሏታል። ማርያምም በብሥራቱ ጊዜ የተቀዳጀችው ይህንኑ አክሊል ነበር። እርሷ ባባቱ በዳዊት ዙፋን የሚቀምጥና ለመንግሥቱም ማለቂያ የሌለውን ኢየሱስን ጸንሳለችና።
የቅድስት ድንግል ማርያም የእናት ንግሥትነት ማዕረግ የበለጠ ጉልህ ሆኖ የሚታየው ደግሞ በ ሉቃ.1:43 ላይ ነው። ይህም ቅድስት ኤልሳቤጥ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ድምጽ በሰማች ጊዜ የመሰከረችው ነው። "የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል!"። ይህ የኤልሳቤጥ "የጌታዬ እናት" የሚለው አባባል የመነጨው በጥንት ጊዜ በንጉሡ ሸንጎ ፊት "ጌታዬ ሆይ!" ማለት "ንጉሥ ሆይ!" እንደማለት የነበረ በመሆኑ ነው። "የጌታዬ እናት" ማለቷ ኤልሳቤጥ የንጉሡ እናት ንግሥቲቱ ቤቷ ድረስ መምጣቷ አስገርሟትም አስደንግጧትም ጭምር ነው። በንግሥት መጎብኘት ያውም እቤት ድረስ መጥታ ያስደንግጣልና ነው። በመሆኑም ኤልሳቤጥ የማርያምን ልዕልና የተረዳችና የመሰከረች ሰው ናት።
ሌላው ቢዚህ የማርያም ንግሥትነት ላይ ብርሃን የሚፈነጥቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ደግሞ ራዕይ 12:1-2 ነው። "ታላቅ ምልክት በሰማይ ታየ ፤ ፀሐይን ተጎናጽፋ ጨረቃ ከእግሮቿ በታች ያላት በራስውም ላይ የአስራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርሷም ጸንሳ ነበር።"
ይህች ሴት ማናት? አንዳንዶች እስራኤልን ወይም ቤተ ክርስቲያንን የምትወክል ሴት ናት ይላሉ። ነገር ግን ይኸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በ12:5 ላይ ይህች ሴት የመሲሑ እናት እንደሆነች ይገልጻል። "አሕዛብን ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋን ተነጠቀ።" ስለዚህ ይህ "አሕዛብን ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለው" ተብሎ የተገለጸለት ንጉሥ ማነው? ንጉሡ ኢየሱስ ነው። ሴቲቱ ደግሞ እናት ንግሥቲቱ እምነ ማርያም ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም በዮሐንስ ራዕይ ላይ የተገጸችው በሰማያት እንደተቀመጠች ንግሥት ነው። በደፋችው ዘውድ ላይ 12 ከዋክብት ከ12ቱ የእስራኤል ንገዶች በተወለደችው በ12ቱ ሐዋርያት ላይ በታነጸችው ቤተ ክርስቲያን ላይ ያላትን የንግሥትነትን ማዕረግ ይገልጻሉ። ፀሐይን መልበሷ ደግሞ የእግዚአብሔር ክብር በርሷ እንደሚገለጽ ያስረዳል። ጨረቃን ከእግሮቿ በታች ማድረጓ የንግሥትነት ሥልጣኗን ይገልጻል (መዝ.8:6፤ 110:1)።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዛሬም በእግዚአብሔር መንግሥት የምእመናን ጠበቃ ሆና ታገለግላለች። በልጇ ዙፋን ፊትም የኛን ጸሎታና ለመና በማቅረብ ጎልህ ሚና የምትጫወት ጽኑ አማላጅ ናት። ጸሎታችንን ይዘን "አያሳፍርሽምና" በሚል መተማመን ወደ መንበሯ እንቅረብ። ኢየሱስም ሰሎሞን ለቤርሳቤህ እንደመለሰላት "እናቴ ሆይ! አላሳፍርሽምና ለምኚ" በሚል ማረጋገጫ ቃል ሰሎታችንን ከአንደበቷ ይቀበላል(1ነገ.2:20)።
Last Updated (Tuesday, 08 September 2009 23:00)
የሰማይ ንግሥት ሆይ! ለምኝልን











Comments
I found some unreadable character in the right side of the first page which is types of song. I cant read the title but I can see the year.
I am Very Very Happy To see this web. every time when i open I feel …
Thank You
God be with you Quote
and on this comment when i Press the bold button it display the script why? I Quote
ክቡር ደረጄ፦ የእግዚአብሔር ፍቅርና ሰላም ይበዛልዎ ዘንድ ምኞታችን ነው። ድረ ገጻችንን በመጎብኘት ለሰጡን አስተያየት፣ ጥቆማና ማበረታታት ሁሉ ምስጋናችን የላቀ ነው።
በድረ ገጻችን ላይ የምንጠቀመው የአማርኛ መልክዓ ፊደል (ፎንት) ኒያላ ዩኒኮድ ወይም ቪዡዋል ግእዝ ዩኒኮድ ሲሆን በዊንዶውስ ቪስታ ያለምንም ተጨማሪ የግእዝ መልክዓ ፊደል በሌሎች ዊንዶውስ ግን ማንኛውም ዓይነት ግእዝ ዩኒኮድ መልክዓ ፊደል የተጫነለት ኮምፒዩተር መነበብ ይችላልል።
በቋንቋችን ፊደላት ወጥ የሆነ ማለትም ለሁሉም በእኩል ሊሠራ የሚችል ዓይነት ዘዴ እስካሁን የለንም። በብዙ ኮምፒዩተሮች ቢነበብም በአንዳንድ ፕሮራሞች ውስጥ ይህ ያለመነበብ ችግር ይከሠታል። ስለዚህ ነጥብ በሙያው ውስጥ ያሉ ሰዎች የተሻለ ማብራርያ ሊሰጡ ይችላሉ። በዚሁ አጋጣሚም የመፍትሔ ሃሳብ ሊጠቁመን የሚችል ሰው ካለም በደስታ እንደምንቀበል መግለጽ እንወዳለን።
ስለ አስተያየት መጻፊያው ሂደትም ላነሡት ነጥብ፤ እርስዎ አስተያየትዎን ሲጽፉ የሚነኩት ትእዛዝና የሚታይዎ የተለያየ ቢሆንም ከጻፉ በኋላ "ላክ" ሲሉት ግን ባዘዙት መሠረት ስለሚወጣ በውጭ እንደፈለጉት ሳይሆን ስክሪፕት ቢያስይዎትም በውስጡ ተርጉሞ ስለሚያስተላልፈው ያለሃሳብ ይላኩት።
ለወደፊትም ይጎብኙን፣ ይጸልዩልን፣ አስተያየትና ጥቆማዎንም ይለግሱን።
(ለመልሳችን መዘግየት እዚህ ጋር ይቅርታ ጠይቀናል)
ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛልዎ።
www.ethiocist.org Quote
Monday, 03 August 2009 07:30 | Written by Administrator |
ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚናገረው ይህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ ካቶሊካዎት ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ መገናኛ መምሪያ ቢሮ በየወሩ ከሚታተመው "ፍቅርና ሰላም" ከተሰኘው ጋዜጣ ግንቦት/ሰኔ 2001 ዓ.ም. እትም "የሰማይ ንግሥት ሆይ ለምኝልን!" ከሚል ርእስ በከፊል የተወሰደ ነው።
"የሰማይ ንግሥት ሆይ ለምኝልን!"
በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ላይ የተገለጸው የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ብሥራት የሚተርከው ማርያም የልዑል እግዚአብሔርን ልጅ እንደምትወልድና እርሱም በብሉይ ኪዳን ስለ መሲሑና ዘላለማዊ መንግሥቱ ተነግሮ የነበረው ተስፋ እንዲፈጸም እንደሚያደርግ ነው። (2ሳሙ.7:፤ መዝ.2:72፣89፤ ሉቃ.1:33)።
እመቤታችን ቅ.ድንግል ማርያም ንግሥተ ሰማይ
ጥንታዊ አይሁዳውያን አንዲት እናት ከዳዊት ዘር የሆነና ወደፊት በንጉሡ ዙፋን ላይ ሊቀመጥ የሚችል (አልጋ ወራሽን) የወለደች እንደሆነ ወዲያውኑ ንግሥት እንደሆነች አድርገው ይቀበሏታል። ማርያምም በብሥራቱ ጊዜ የተቀዳጀችው ይህንኑ አክሊል ነበር። እርሷ ባባቱ በዳዊት ዙፋን የሚቀምጥና ለመንግሥቱም ማለቂያ የሌለውን ኢየሱስን ጸንሳለችና።
የቅድስት ድንግል ማርያም የእናት ንግሥትነት ማዕረግ የበለ Quote
RSS feed for comments to this post.