ንኡሳን ገጾች
Chaplet of Divine Mercy
Home (ቅድመ ገጽ) ዜናዎች የሰው ልጅ ሁሉ መመዘኛ ክርስቶስ ነው

የሰው ልጅ ሁሉ መመዘኛ ክርስቶስ ነው

ቫቲካን ሬድዮ - ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ.ቤኔዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ረፋድ እንደወትሮኣቸው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሱት በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ምእመናንና ነጋድያን (መንፈሳዊ ተጓዦች) የተለመደውን ሳምንታዊ የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ኣቅርበዋል። 

ጉባኤውን በጸሎት ከከፈቱ በኋላ የሚከተለው ቃለ እግዚአብሔር ከመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ አንድ ተነበበ።

1 በክፉ ሰዎች ምክር የማይሄድ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ የማይቆም፥ በፌዘኞች ወንበር የማይቀመጥ የተባረከ ነው። 2 እንዲህ ያለ ሰው፣ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም ቀንና በሌሊት ያሰላስለዋል። 3 ስለዚህም እርሱ፣ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ በፈሳሽ ውኃ ዳር እንደ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሥራ ሁሉ ይሳካለታል። 4 ክፉዎች ግን እንዲዚህ አይደሉም፥ እነርሱ ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው። 5 ስለዚህ ክፉ ሰዎች፣ በፍርድ ቀን ጸንተው አይቆሙም፥ ኃጢአተኞችም በጻድቃን መካከል አይገኙም። 6 ምክንያቱም እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች። 

በመቀጠልም ቅዱስነታቸው በዛሬ ትምህርታቸው ከነገ ወዲያ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 9 ቀን 2009 ዓ.ም. የሚታወሰው ቅዱስ ዮሓንስ ሌዮናርዲ ከሞተ አራት መቶ ዓመት መሙላቱን በማስታወስ በርሱ ሕይወት ዙሪያ አስተምህሮ አደረጉ። ከዚህ በታች በተለያዩ ቋንቋዎች ካቀረቧቸው ትምህሮቶች ለእንግሊዘኛ ተናገሪዎች የሰጡትን ትምህርት እናቀርብላችኋለን።

"ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፣ ይህ ሳምንት ቅዱስ ዮሐንስ ሌዮናርዲን ሞት 400ኛ ዓመት ያመለክታል። ቅዱሱ የእመ አምላክ ካህናት ማኅበር መሥራች ናቸው። የእነዚህ ካህናት የስብከተ ወንጌል መንፈሳዊ ቅናት የአሕዛብ ስብከተ ወንጌል ቅዱስ ማሕበር (ፕሮፓጋንዳ ፊዴ) መቋቋም ምክንያት ሆነዋል። ቅዱስ ዮሓንስ ሉካ በሚባል ከተማ አከባቢ ተወለደ። በፋርማሲ ትምህርት ከሠለጠነ በኋላ በጊዜው ለነበሩ ሰዎች የእግዚአብሔርን መድኃኒት ለመስጠት ማዕረገ ክህነትን ተቀብለው በትጋት አገለገሉ። በዚያን ጊዜ የቤተ ክርስትያንን ሕይወት ለመለወጥና ለማደስ ብርቱ ጥረት ይደረግ ስለነበር፣ ቅዱስ ዮሓንስ የስብከታቸው ማእከልና የሁሉ ነገር መመዘኛ ያደረጉት ነገር የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል ነበር። ቅዱሱ እውነተኛ የቤተ ክርስትያን ሕይወት ለውጥ የሚመነጨው በክርስቶስ ባለን እምነትና ለቤተ ክርስትያኑ ባለን ፍቅር መሆኑን በደንብ ተገንዝበው ነበር። ወጣቶችን ትምህርት ክርስቶስ ለማስተማር እንዲሁም የክርስትያን ሕይወትንና ኑሮን ለማደስ የስብከተ ወንጌል ሥራን ለማስፋፋትና ለማነቃቃት የገፋፋው የኢየሱስ ፍቅር ነበር።

ሌላው ቅዱስ ዮሐንስ በልበ ሙሉነት ያመነው ነገር ቢኖር የሰው ልጅ ሁሉ መመዘኛ ክርስቶስ መሆኑን ነው፣ ከዚህ የተነሣ የኅብረተሰብ ቅድስናንና ለውጥ ለማጐልበት በተጨባጭ እውነትና መንፈሳዊ ቅናት ይሠራ ነበር። በዚህ ዓመተ ክህነት፤ ክህነትን በምናስብበት ጊዜ የዚህ ታላቅ ስብከተ ወንጌላዊ ምስል ካህናትንና ምእመናንን እንደገና በአዲስ መንፈስ ከክርስቶስ ለመጀመር እንዲያበራላቸው፣ ጥሪያቸውን በጋለ ስሜትና ጉግት እንዲቀበሉ ይርዳቸው።" በማለት ስለቅዱስ ዮሐንስ ሌዮናርዲ ካሳሳሰቡ በኋላ፣ በመጨረሻ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ትምህርታቸውን ለመከታተል ለመጡ ምእመናንና ነጋድያን በተለያዩ ቋናቋዎች ሰላምታ አቅርበውና ኣመስግነው በመካሄድ ላይ ያለው የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ስኬታማ እንዲሆን በጸሎት እንዲተባበርዋቸው በማማጠን ሓዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት ምእመናንን አሰናብተዋል።

Last Updated (Thursday, 08 October 2009 05:44)

 

Add comment


የሳምንቱ መልእክት
"ለሰው ይኽን ያህል ታላቅ ክብር ለመስጠት ያነሳሳህ ምን ይሆን?...ወደር የሌለው ፍቅርህ እንደሆነ አይጠረጠርም! በፍቅሩ ተማርከሃል፤ በአውነትም በፍቅር ፈጥረኸዋል፤ በፍቅርም ዘላለማዊ መልካምነትህን የሚያጣጥም ስብእናን ለግሰኸዋል።" ቅድስት ካተሪና ዘሲየና
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ያን መዝሙሮች (ብዛት 110!)
ባለፉት 12 ሰዓታት የጎብኚዎች አገር
Top 6:
Ethiopia flag 27%Ethiopia (3)
United States flag 27%United States (3)
Russian Federation flag 18%Russian Federation (2)
Canada flag 9%Canada (1)
Moldova, Republic of flag 9%Moldova, Republic of (1)
Switzerland flag 9%Switzerland (1)
11 visits from 6 countries