ቤተ ክርስትያን የስብከተ ወንጌል ተልእኮ ቀንን አስታውሳ ዋለች
ራድዮ ቫቲካን - ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ትናንት እሑድ ከሐዋርያዊ አዳራሽ መስኮት በመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡት በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩት ምእመናን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመድገማቸው በፊት ዕለቱ የስብከተ ወንጌል ተልእኮ ቀን የሚዘከርበት እሁድ መሆኑን አስታውሰው፣ ቤተ ክርስትያን ለመላው ሰው ዘር ወንጌልን መስበክ እንደሚጠበቅባትና ቤተ ክርስትያን የምትኖረው የወንጌል የተስፋ መልእክትን ለማስተላለፈ መሆኑን አሳስበዋል። በቅርቡ በብራዚል የተገደሉት ልኡከ ወንጌል ኣባ ሩቮለቶ እና በፊሊፒንስ የታገቱት አባ ሲኖት በማስታወስም በጸሎት እና በመንፈስ እንደሚዘክሩዋቸው አረጋገጠዋል።










