ዐቢይ ጾምና ሌሎች አጽዋማት - መግቢያ
ዐቢይ ጾምና ሌሎች አጽዋማት
በክቡር አባ ተሾመ ፍቅሬ ከየካቲትና መጋቢት 2001 ዓ.ም. "ፍቅርና ሰላም" ካቶሊካዊት ወርኀዊ ጋዜጣ እትም የተወሰደ
መግቢያ
ያለንበት ወቅት በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የዐቢይ ጾም ጊዜ ነው። በመሆኑም አብዛኛውን ጊዜ “ጾም” ሲታሰብ ወደ አብዛኛዎቻችን አእምሮ በቅድሚያ ብልጭ የሚልልን ደግሞ ከምግብ መቆጠብ የሚለው አስተሳሰብ ነው። እናም ስልጾም በትንሹም ቢሆን ላካፍላችሁ ስነሣ በአንድ ወቅት የሰማሁት ቀልድ ትዝ አለኝና ላካፍላችሁ ወደድኩ፦ ሰውዬው ናቸው አሉ፤ ከመጠን ባለፈ ተመግበው ኖሮ በቁንጣን ሲሰቃዩ አይተው ለጥጋባቸው ያዘኑላቸው ወዳጆቻቸው የሚበትን ምናምን እንዲወስዱ ቢመክሯቸው “ለምን ሰበሰብኩና እንድበትን ትመክሩኛላችሁ” አሉ ይባላል። ይህንን ያነሣሁት ያለምክንያት ሳይሆን ስለጾም ስናስብ በመጠን (በልክ) መሆንን እንድለማመድ ሲባልና ራስን ለመግዛት ከምግብ መቆጠብን ብቻ የመጨረሻ ግብ አድርገን እንዳንወስድ ይልቁንም ከዚህ ባሻገር ያለውን መንፈሳዊ እንድምታ አብረን እንድናይ በማሰብ ጭምር ነው።
“ጾም” በጥሬ የመዝገበ ቃላት ትርጉአሜ ስንመለከተው ከላይ ካስቀመጥነው አገላለጽ ባለፈ አርቀን እንድናይ ብዙም የሚረዳን አይደለም። ትርጉሙንም ሲያስቀምጠው “ተወ፣ ተከለከለ፣ ታረመ፣ እርም ይሁንብኝ አለ” በማለት ነው።
Last Updated (Saturday, 06 March 2010 19:58)
ዐቢይ ጾምና ሌሎች አጽዋማት

