Font Size

Cpanel

Cistercians In Ethiopia - Ethiopian Catholic Church

You are here: Home ዜናዎች ዓመታዊ የቅዱስ ዮሴፍ ክብረ በዓል ተከበረ

ዓመታዊ የቅዱስ ዮሴፍ ክብረ በዓል ተከበረ

በየዓመቱ በወርኃ ግንቦት የሚከበረው አ.አ. የሚገኘው የሲታውያን ገዳም የጻድቁ ቅዱስ ዮሴፍ ክብረ በዓል ብፁዕ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ፣ ካህናት፣ ደናግላን እንዲሁም ቁጥራቸው እጅግ የበዛ ካቶሊካዊያን ምእመናንና ሌሎችም በተገኙበት ግንቦት 26/2004 ዓ.ም. በዕለተ ጰራቅሊጦስ በድምቀት ተከብሮ ዋለ፡፡ ከዋና ክብረ በዓሉ በፊት ማለትም ዋዜማው ብዙ ያሬዳውያን መዘምራን፣ ካህናት፣ የቅዱስ ሚካኤል ዘርአ ክህነት፣ የኮምቦኒ፣ የቅዱስ ኤፍሬም አቢይ ዘርአ ክህነት፣ የመንዲዳ ገዳመ ሲታውያን ተመካሪያንና ዘርአ ምንኩስና ተማሪዎች እንዲሁም የቀድሞ የገዳመ ሲታውያን ተማሪዎችና ሌሎች እንግዶችም በተገኙበት እጅግ ያማረ የዋዜማ ሥነ ስርአት ከቀኑ 9 ስዓት እሰከ 11፡30 ተከናውኖአል፡፡

ዕለቱ ድርብ በዓል (ጰራቅሊጦስ ና ቅዱስ ዮሴፍ) እንደመሆኑ መጠን ብፁዕ አባታችን አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን በስብከታቸው ስለ መንፈስ ቅዱስና ስለ ቤተሰብ በሰፊው ሰብከዋል፡፡ በተለይም ‹‹ወመንፈሰከ ቅዱሰ ኢታውፅእ እም ላዕሌየ...›› የሚለውን የዕለቱን ምስባክ ጠቅስው ህይወታችን በመንፈስ ቅዱስ ካልተመራ ትርጉም አልባ ነው፡፡ ስለዚህም ‹‹እባክህን መንፈስህን ከእኔ አትውሰድ ከወሰድክ ግን እሞታለሁ...›› ብለን እንማፀነው በማለት ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል ቤተሰብን አስመልክተው ሲሰብኩ ከሕዝበ ክርስቲያኑ መካከል የተወሰኑትን ቤተሰቦች (አባት፣ እናት፣ ልጅ) ወደፊት እንዲቀርቡ በጋበዙት መሰረት የተለያዩ ቤተሰቦች ወደ እርሳቸው ሲቀርቡ እርሳቸውም በበኩላቸው ከመካከላቸው አንዱን ሕፃን አንስተው በመታቀፍ ‹‹ቤተሰብ የቤተክርስቲያን እስትንፋስ ነው የሀገርም መሰረት ነው፡፡ ቤተሰብ ከሌለ ማህበረሰብ የለም፡፡ ስለዚህ በዛሬ ቀን በመላ ዓለም ቤተክርስቲያን ዘንድ ስለቤተሰብ የሚጸለይበት ቀን ስለሆነ ሁላችንም በመቆም ስለቤተሰብ እንጸልይ ፡፡ ›› በማለት የዕለቱን ቃለ እግዚአብሔር አጠቃለሉ፡፡

መሰዋዕተ ቅዳሴ ከተፈጸመ በኃላ ቅዱስ ቁርባንና የተለያዩ ቅዱሳን ስዕላት በመያዝ በወጣት መዘምራን፣ በያሬዳዊያን እንዲሁም በአባቶችና በእናቶች የተለያዩ ዝማሬዎችና ጸሎት የታጀበ የዑደት ስርዐት በማድረግ በብፁዕ አባታችን በተሰጠ የመጨረሻ የቅዱስ ቁርባን ቡራኬ የዕለቱ የቤተ ክርስቲያን መርኃ ግብር ተጠናቀቀ፡፡ በመጨረሻም ገዳሙንና የቁምስናው ምዕመናን ምክር ቤት በመተባበር ያዘጋጁትን የምሳ ግብዣ (ፀበል ፃዲቅ) ለሁሉም ምዕመናን በማዳረስ በጥሩ ሥነ-ሥርዓት የዕለቱ መርኃ ግብር ተፈጸመ፡፡

የመንዲዳ መድኃኔዓለም ቁምስና ምዕመናንና የደብረብርሃን ቁስቃም ማርያም ምዕመናን በሁለት ትላልቅ አውቶቡሶች በመሆን ያደረጉት የቅዱስ ዮሴፍ ንግሥ መንፈሳዊ ጉዞ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ በሌሎችም ዘንድ ቢለመድ ጥሩ ነው የሚል የግል አስተያየት አለኝ፡፡

ከመ በኩሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!!

አባ ተሻለ ንማኒ /ሲታውያን/

በዚህ ጽሑፍ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ጽሑፋት

Other articles in ዜናዎች

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ 50ኛው የዓለም የጥሪ ጸሎት ቀን መልእክት 23 May 2013

የብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ የ2005 ዓ.ም የጌታችን ትንሣኤ በዓል መልእክት 05 May 2013

የር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ስብከት ዘሆሳዕና 2005 ዓ.ም. 28 April 2013

ቤተ ክርስቲያን ልጆችን የምታስተኛ ሞግዚት መሆን የለባትም! 19 April 2013

ካቶሊኮች የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ደስታን በማሳየት ዓለምን አገልግሉ 11 April 2013

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ከቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው ጋር ተገናኙ 27 March 2013

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ማን ናቸው? 15 March 2013

"አዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አግኝተናል!" 13 March 2013

የቅዱስ አባታችን ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛውን ሕይወት የሚዳስስ ምርጥ ዝግጅት ያድምጡ 07 March 2013

ለር.ሊ.ጳ. ምርጫ ዝግጅት የመጀመሪያው የካርዲናሎች ጉባኤ ተካሄደ 05 March 2013

ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው የመንበረ ጴጥሮሳዊ አገልግሎታቸውን እንደሚያቋርጡ አስታወቁ። 11 February 2013

ሁላችን በጌታችን ፍቅር ልንሸነፍ ይገባናል! 07 January 2013

በሰባት ዓመቱ ሕፃን ጆሴፍ ራዚንገር /የአሁኑ ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው/ ለሕፃኑ ኢየሱስ የተጻፈ የገና ደብዳቤ 25 December 2012

ሢመተ ክህነት በገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን አዲስ አበባ 30 October 2012

መንፈሳዊ ምድረ በዳነት ባጠቃው ወቅታዊው ዓለም ዳግም ክርስቶስን ማወጅ 14 October 2012

የማይቃወመን እርሱ ከእኛ ጋር ነው! 05 October 2012

የእግዚአብሔር ሕዝብ በደም ትስስር በመሬትና በአገር ድንበር የቆመ አይደለም 01 October 2012

"ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች በአንድነት ቆመው አመፅ እንዲበቃ የሚያደርጉበት ጊዜው አሁን ነው!"፡ ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው በሊባኖስ 16 September 2012

ሊቀ ጳጳሳት ብ. አ. ብርሃነየሱስ የ2005 ዓ.ም ርእሰ ዐዉደ ዓመትን በማስመልከት ለምእመናን ያስተላለፉት መልእክት፡፡ 13 September 2012

ር.ሊ.ጳ. ቤኔዴክቶስ 16ኛው ለጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ህልፈት የኀዘን መግለጫ ላኩ። 22 August 2012

- Entire Category -

ተወራራሽ ርእሶች