Font Size

Cpanel

Cistercians In Ethiopia - Ethiopian Catholic Church

10. የተሰዋ ሕይወት

የተሰዋ-የምንኩስና- ሕይወት

በጌታ ክርስቶስ አርአያነቶችና በእርሱ ትምህርቶች ላይ በጥልቀት የተመሠረተው ይህ የተቀደሰ ሕይወት /ለተቀደሰ ዓላማ የተለየ ሕይወት/ በመንፈስ ቅድስ አማካይነት እግዚአብሔር አብ ለቤተክርስቲያን የለገሠው ስጦታ ነው፡፡ የኢየሱስ ሕይወት እውነተኛ ባሕርይ የሆኑት የወንጌል ምስክሮች፣ ማለትም ድንግልና፣ ድኽነትና ታዛዥነት በዓለም መካከል እውነተኛና ቋሚ "ጉልህ ገጽታን የሚያኙ ሲሆን አስቀድሞ በታሪክ ውስጥ በመሥራት ላይ ያለው ነገር ግን ሙሉ ግቡን በመንግሥተ ሰማያት እንደሆነ የሚጠባበቀው የምእመናን አስተሳሰብም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ምስጢር ተጠርቶአል፡፡ ከረጅም ዘመናት ጀምሮ ለአብ ጥሪና ለመንፈስ ቅዱስ ሥራ ትሑታን ታዛዦች የሆኑ፣ ክርስቶስን በመከተል ልዩ መንገድ፣ ሐሳባቸውን "ላይ ከፍ ብሎ" 1ቆሮ 7፡34 የመረጡ ወንዶችና ሴቶች ግለሰቦች ምንጊዜም አልታጡም፡፡ ለእግዚአብሔርና ለወንድሞቹ አገልግሎት እንደ ሐዋርያት እነርሱም ለእኛ ማንኛውንም ነገር አስተላልፈውልናል፡፡

በዚህም መሠረት መንፈስ ቅዱስ በሰጣቸው የመንፈሳዊነትና የሐዋርያት ሕይወት ተሰጥዎች የቤተክርስቲያንን ምስጢርና ተልእኮ ለማበልጸግ ከፍ ያለ አስተዋጽዎ አበርክተዋል፤ እንዲሁም ኅብረሰተብን በማደስ ተግባር ላይ ተባባሪዎቹ ሆነዋል፡፡

የተቀደሰ ሕይወት ለቤተክርስቲያን የተሰጠ ስለመሆኑ

የተቀደሰ ሕይወት ሁለንተናዊ ህላዌ የወንጌል ምስክርነት ባሕርይ በሙሉ ተጨባጭነት የሚያመለክቱት አስፈላጊ ከሆነ የተቀደሰ ሕይወት የተሸሸገ እውነታና ከማኅበረሰባዊ ሕይወት የተገለለ ሳይሆን ነገር ግን የመላዋን ቤተክርስቲያን የሚመለከት ነው፡፡ ይህንንም ጳጳሳት በሲኖዶሱ ጠቅላላ ጉባኤያቸው ላይ "እኛን የሚመለከት ነገር ነው" /nostra de re agitur/ ሲሉ ደጋግመው አረጋግጠዋል፡፡

በርግጥ የተቀደሰ ሕይወት "የክርስቲያናዊ ጥሪ ባሕርይን አብራርቶ በመግለጥ ያመለክናተል" በሚለው መሠረት ለዚህ ሕይወት ብቸኛ እጮኛ ከሆነው ከክርስቶስ ጋር በሚደረግ የኅብረት ጥረት ለመላዋ ቤተክርስቲያን ተልእኮ ተግባር እንደ ወሳኝ ነገር በመሆን በቤተክርስቲያን ልብ ውስጥ ይመሠረታለ ማለት ነው፡፡ የተቀደሰ ሕይወት ባለፉት ዘመናት ለቤተክርስቲያን የረዳትነትና የድጋፍ ሰጪነት ሚና ብቻ እንዳልነበረው በጳጳሳት ሲኖዶሳዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በርካታ ጊዜያት ተረጋግጧል፡፡ በመሆኑም የተቀደሰ ሕይወት ለሕዝበ እግዚአብሔር ለአሁኑና ለመጪው እጅግ ውድ የሆነ ስጦታ ነው፤ ምክንያቱም ከክርስቶስ ሕይወት ከቅድስናውና ከተልእኮው ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነውና፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአንዳንድ ዓለም ክልሎች መኖራቸው ቢታመንም የቤተክርስቲያን ሕይወት መሠታዊ አካል በሆኑት በወንጌል ምክሮች አማካኝነት የተቀደሰ ሕይወት ሁልጊዜ የላቀ የወንጌል አገልግሎቱን ማርካት እንዳለበት መጠራጠር አያሻም፡፡

ሕይወትን ለተቀደሰ ዓላማ በማዋል በኩል፣ በታሪካዊነት መልክ ሌላ አማራጭ ማግኘት ይቻላል፤ ሆኖም ለማንኛውም ሰብአዊ ቤተሰብ ስለ ኢየሱስ ፍቅር ሲባል የገዛ ራሱን አሳልፎ የመስጠትን ምርጫ የሚተካ ሌላ ስር ነቀል የሆነ ምርጫ እንደሌለ እሙን ነው፡፡

ስለዚህ ሕዝበ ክርስቲያን በዚህ እርግጠኝነት ማለትም ወደ መንግሥተ ሰማያት በሚያደርገው ጉዞ እጅግ በጣም ዋጋ ያለው ውድ ድጋፍ የሰጡ በክፍለ ዘመናችን ሂደት ውስጥ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎችን አስቆጥሮአል፡፡

ይህ የተቀደሰ ሕይወት ስጦታ በመንፈሳዊ ተሰጥዎቹና በተቋማት እውነት ለቤተክርስቲያን ማኅበረሰብ ያጠለለውን ብለጽግና ሁላችንም እንደምንገነዘብ አምናለሁ፡፡ ስለ ማዕረገ ክህነት፣ ስለ በጽሞና ጸሎት ላይ ብቻ ተመድበው ስለሚኖሩ የምንኩስና ማኅበራት፣ ስለ ሐዋርያዊ ሥራዎች፣ ስለ ሐዋርያዊ ሕይወት ማኅበረሰብና ስለ በገዳም ውስጥ የሚኖሩ የምንኩስና ማኅበራትና ስለ ሌሎችም የተቀደሰ አገልግሎት ሲሉ በተለይ የተቀደሰ ሕይወት ላይ ተለይተው ስለሚገኙ ማለትም እነዚህን ሁሉ እግዚአብሔር ስለሰጠን ለእርሱም ምስጋና ማቅረብ ይገባናል፡፡

በወንጌል ምስክሮች (የመሐላ ሕይወት) የቅድስት ሥላሴያዊ ሕይወት ነጸብራቅ

የወንጌል ምስክሮች (የመሐላ ሕይወት) ከቅድስት ሥላሴ ጋር ያላቸውን ግንኙነት መመስከር ማለትና የእነርሱን ጥልቅ ትርጉም መግለጽ ማለት ነው፡፡ በእርግጥም ኢየሱስ ከመንፈስ ቅዱስ አንድነት ጋር ለአብ የሚያቀርባቸው የፍቅር አነጋገሮች ናቸው፡፡ ሕይወቱን ለተቀደሰ ዓለማ የመደበ ሰው የወንጌል ምስክሮችን ተግባራዊ በማድረግ ክርስቲያናዊ ሕይወቱ የሚያጠቃልለውን የቅድስት ሥላሴያዊና ክርስቶሳዊ ባሕርይ በተለየ ሁኔታ ይኖራል፡፡

ንጽሕና፡- ትዳርን ያለመመሥረትና ድንግላውያን ንጽሕና ወይም ባልተከፈለ ልብ ለእግዚአብሔር ማደራቸውን የሚያሳይ እንደመሆኑ መጠን /1ቆሮ 7፡32-34/ ምስጢራዊ የሆነ የሦስቱ መለኮታዊ አካላት ፍቅር፤ ማለትም የገዛ ራሱን ሕይወት እስከመስጠት የደረሰውን ቃል ሥጋ የሆነውን ፍቅር ይመሰክራሉ፡፡ ይህም ፍቅር "በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ ለተሰጠ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለሞላ ተስፋው አያሳፍርም" ሮሜ 5፡5 እንደለው ለእግዚአብሔርና ለወንድሞች የሚሰጥ አጠቃላይ ምላሽ ነው፡፡

ድኽነት፡- ድኽነት እግዚአብሔር የሰው ብቸኛ እውተኛ ብልጽግና እንደሆነ ይመሰክራል፡፡ "እናንተ የጌታችን የኢሱስ ክርስቶስን ታላቅ ልግስና ታውቃላችሁ፤ እሱ ምንም እንኳን ሀብታም ቢሆንም ስለ እናንተ ብሎ ድኻ ሆነ" 2ቆሮ 8፡9 የሚለው አነጋገር ሦስቱ መለኮታዊ አካላት እርስ በርስ የሚሰጥበትን ጠቅላላ ራስን አሳልፎ የመስጠት ሁኔታ የሚያሳይ ነው፡፡ ይህም በእግዚአብሔር የመፈጠር ስራ ስጦታ ሲሆን፣ በቃል ሥጋ መሆንና አዳኝ በሆነው ሞቱ ሙሉ በሙሉ ይገለጻል፡፡

ታዛዥነት፡- ክርስቶስን ለመምሰል የሚደረግ ታዛዥነት ይህም ማለት ለእርሱ ግብ ያባቱን ፈቃድ መፈጸም ዮሐ 4፡34 በሚለው መሰረት የሚደረግ ታዛዥነት የሚያመለክተው የልጃዊነት እንጂ የአገልጋይነትን ሁኔታ አይደለም፤ ነገር ግን ታዛዥነት የኃላፊነት ስሜት የሞላበትና የእርስ በርስ መተማመን የዳበረበት የቅድስት ሥላሴ ፍቅር ነጸብራቅ ነው፡፡

ስለዚህ የተቀደሰ ዓላማ የተሰጠ ሕይወት የተጠራ ሰው የወንጌል ምስክሮችን (መሐላዎችን) ዘወትር በእውነተኛና በጠንካራ ቅድስት ሥላሴአዊ ፍቅር፤ ይህም ማለት ወደ ራሱ ለሚጠራ ለኢየሱስ ፍቅር፤ መንፈስ ቅዱስ ፍቅር ነፍስ የእሱን መቃተቶች እንድትቀበል ለሚያደርግ የተቀደሰ ሕይወት መሰረትና ምክንያት ለሆነው እግዚአብሔር አብ ፍቅር ዘወትር በእውነተኛና በጠንካራ መንፈስ የወንጌል ምስክሮችን በሥራ ላይ ማዋል፡፡ የተቀደሰ ሕይወት ወይም ለተቀደሰ ዓላማ የተሰጠ ሕይወት በዚህ ሁኔታ የእያንዳንዱ ክርስቲያናዊ ሕይወት እንደ አርአያና ምንጭ ተደርጐ ለቤተክርስቲያን የተሰጠ ይሆናል፡፡

ይህም የወንድማዊ ሕይወት "አንድ ልብና አንድ ሀሳብ" ሐ.ሥ 4፡32 በሚለው መሰረት ሕይወታቸውን ለተቀደሰ ዓላማ ያዋሉ ሰዎች በክርስቶስ ለመኖር ራሳቸውን የሚያስገድዱበት ሕይወት ነው፡፡ የተቀደሰ ሕይወት ሁሉን ሰዎች አንድ ቤተሰብ ለማድረግ ስለሚፈልገው ስለ አብ ይመሰክራል፤ ለተከፋፈሉና ለተበታተኑት ሰዎች በራሱ አብነት በጸሎቱ በቃላቱና ከሁሉም በላይ በሞቱ የእርቅ ምንጭ የሆነ መንገድን እያመለከታቸው የዳኑ ሰዎችን የሚቀበል ጸጋ ስለለበሰ ሰው አምላክ ይመሰክራል፤ እንዲሁም በቤተክርስቲያን የአንድነት መሰረት የሆነውን መንፈሳውያንን ቤተሰቦችንና የወንድማማች ማኅበረሰቦችን ያለ ማቋረጥ ስለሚደግፍ ስለ መንፈስ ቅዱስ ይመሰክራል፡፡

ምንጭ፡ የምንኩስና ሕይወት /vita consacrata/