Font Size

Cpanel

Cistercians In Ethiopia - Ethiopian Catholic Church

ሰማይና ምድር

ሰማይና ምድር

የሐዋርያት ጸሎተ ሃይማኖት እግዚአብሔር "የሰማይና የምድር ፈጣሪ" ነው በማለት ሲገልጽ፣ የኒቂያ ጸሎት ሃይማኖት ደግሞ፣ ይህ የእምነት መግለጫ "የሚታዩና የማይታዩትን ሁሉ" እንደሚያጠቃልል ያብራራል፡፡

"የሰማይና ምድር" የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ፣ የሚኖር ሁሉ፣ ፍጥረት በሙሉ ማለት ነው፡፡ በፍጥረት ውስጥ ያለውን ትስስር፣ ሰማይንና ምድርን አንድ የሚያደርጋቸውንና እንዲሁም አንዱ ከሌላው የሚለይበትን ሁኔታም ይጠቁመናል፡፡ "ምድር" የሰው ልጆች ዓለም ስትሆን፣ "ሰማይ" ወይም "ሰማያት" ጠፈርንና የራሱን የእግዚአብሔርን "መኖሪያ" "በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ" በሚለም ሐረግ የላቀ የክብር ቦታ የሆነውን "ሰማይ" ሊያመለክትም ይችላል፡፡ በመጨረሻም "ሰማይ" የሚለው ቃል ቅዱሳንና በእግዚአብሔር ዙሪያ የሚገኙ የመንፈሳዊ ፍጥረታትንና የመላእክትን "ቦታ" ያመለክታል፡፡

የአራተኛው ላተራን ጉባኤ /1215/ የእምነት መግለጫ፣ እግዚአብሔር "ከዘመን መጀመሪያ አንስቶ በአንድ ጊዜ ከምንም የስነ ፍጥረትን ሁለቱንም ሥርዓቶች፣ መንፈሳዊንና ምድራዊውን፣ ቀጥሎም ከመንፈስና ከአካል በመሠራቱ፣ የሁለቱም ሥርዓቶች ተካፋይ የሆነውን ሰው መፍጠሩን ያረጋግጣል፡፡

በዚህ ጽሑፍ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ጽሑፋት

Other articles in አንቀጽ ፭ - ሰማይና ምድር

የዓለም ውበት፣ ሥርዓትና ውኅደት 21 July 2012

የመላእክት ህላዌ 21 July 2012

ሰማይና ምድር 21 July 2012

- Entire Category -