Font Size

Cpanel

Cistercians In Ethiopia - Ethiopian Catholic Church

melkamEregna

ዘኖላዊ

በዚህ ስብከተ ገና ወቅት ይህ ሦስተኛው ሳምንት ዘኖላዊ ማለትም የእረኛው ኢየሱስ ሰንበት ተብሎ ሲጠራ እግዚአብሔር ምን ያህል እያንዳንዳችንን ፈልጎ ለማግኘትና ለመንከባከብ እንዲሁም የእርሱና ለእርሱ ከእርሱ እንዲሁም በእርሱ መሆናችንን እንገነዘብ ዘንድ በዚህ የእርሱ ልደት ዝግጅት ተጋብዘናል። በዚህም መሠረት ገና ማለትም የእርሱ ልደት ቀድሞ እርሱ እኛን እንዳገኘን የሚያሳስበን ሲሆን እኛም እናገኘው ዘንድ ራሳችንን እንድንመረምርና እንድናዘጋጅ ያግዘናል ብለን ስላመንን ስብከተ ገና በሚል ያገኘነውን ጽሑፍ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። ዘኖላዊ /ዘስብከት 3ኛ/ ዕብ 13፡ 16-21፣- 1ጴጥ 2፡19-25፣ ሐዋ 11፡19-26- ዮሐንስ 10፡ 1-6

የገና ሚስጢር እና አስደናቂነት እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያሳየው በአክብሮትና በንጽህና የተሞላ ፍቅር ዓመታዊ አስታዋሾች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ልጅ በዚያች የድሆች ከተማ በሆነችው ቤተልሔም ውስጥ መምጣት አስደናቂ እውነታ ለጥቂት ጊዜ ቆም ብለን በአትኩሮት ስናስብ ከራሳችን ማንነትና ዙሪያችንን ከከበቡን ጉዳዮቻችን ሁሉ ለመውጣት እንገደዳለን፡፡ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ለእግዚአብሔር አብ አዳኝ ፍቅርና መለኮታዊ ጥበቃ ምስጋና ወደ ማቅረብ አዲስ አድናቆት ወደ መቸር ከፍ ከፍ እንላለን፡፡

የስብከተ ገና ወራት የመታደሻ፣ አዲስ እምነት የመቀበያና የመለወጫ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ወቅት ለመንፈሳዊ እድገት እንቅፋት የሚሆኑትን በርካታ የችግር ሰንሰለቶች የመበጠሻ ጊዜ ነው፡፡ ወቅቱ ከእግዚአብሔር መለኮታዊ ኃይሉና ጥበቃው በሕይወታችን ላይ ካስቀመጣቸው ከወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋርም የአንድነት መተሳሰሪያ ገመዳችንን የምናጠብቅበት ጊዜ ነው፡፡ አንዱ የመጠቀሚያ ዘዴያችንም የእርቅና የፍቅር የሆነው የንስሐ ቅዱስ ሚስጥር ነው፣ ይህ ሚስጢር ኃጢአትን ይቅር ለማለት የሚደርስልንና እውነተኛውን ውስጣዊ መለወጥ ለማግኘት የሚያስችለንነ ፀጋ የያዘ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡

ጌታ በኛ ተፈልጐ መገኘት ያለበት ነው /በርሱ በኩል የሚቻለውን ያህል ቀርቧልና/፡፡ እርሱ እኛ ዘወትር ልንፈልገው የሚገባና እንደ ተገናኘንም ወዲያውኑ ሕይወታችንን ሊለውጠው ዘወተር ተዘጋጅቶ የሚጠብቀን ነው፡፡ እርሱን ፍለጋ እንድንሄድና ልባችንና ነፍሳችን አጥብቀው የሚሹትን አምላክ ፍለጋችንን ቀጥለን እስክናገኘው ድረስ እግዚአብሐር ይደበቅብናል፡፡ በዚህ ምድር ላይ የምናሳልፈው ሕይወታችን የማያቋርጥ ፍለጋ ያለበት፣ እግዚአብሔርን እስከምናገኘው ድረስ መሻታችንን የምንቀጥልበት፣ ካገኘነውም በኋላ ለሁል ጊዜውም ካጠገባችን ሳይለይ እንዲኖር የምናደርግበት ጊዜ ሊሆን ይገባል፡፡ በእርግጥ ከልብ የምንወደው ከሆነ እግዚአብሔርን ማግኘት ማለት ዘወተር አጥብቀን ይዘነው መቆየት ማለት ነውና፡፡

እርሱን ፍለጋ በምንሔድበት ጊዜ፤ፍለጋህ በሙሉ ልብህና ነፍስህ ከሆነ በእርግጥም ጌታን ታገኘዋለህ፡፡

እርሱን ለመፈለግ ታዲያ እንዴት ነው ልባችንንና ነፍሳችን የምናዘጋጀው? የርሱን ትእዛዛት ለመጠበቅ ለራሳችን ውሳኔ ባሳለፍንበት ቀን፣ የራሳችንን ማንነትና ውስጣችንን መርምረን ንስሐ ለመግባት ቁርጥ ውሳኔ ባደረግንበት ቀን የዚያን ጊዜ ስለርሱ መረዳት እንጀምራለን፣ ልናገኘው ተስፋ አድርገን ፍለጋውን የጀመርንለትን እርሱን ለማየት እንችል ዘንድ ዓይኖቻችን ይከፈታሉ፡፡ ምክንያቱም ልበ ንፁሃን እስካልሆንን ድረስ እርሱን ለማየትና ለማግኘትም አንችልምና ነው፡፡

እርሱን ለመፈለግና ለማግኘት መንገድ ከመጀመራችን በፊት ራሳችንን በጥንቃቄ መመርመርና በልባችን አዳራሽ ውስጥ የተቀመጠው ማን እንደሆነ ተገቢነት ለርሱ ለጌታችን መቀመጫ በሆነው የልባችን አዳራሽ ውስጥ ምን በመካሔድ ላይ እንደሆነ ማየትና ማወቅ አለብን፡፡ በሌላ አነጋገር እርሱን እንግዳችንን ይዘን የምንገባበትን ክፍል ማጽዳት አለብን፡፡ ጌታን ማግኘት ማለት እርሱን መያዝና በልባችን ውስጥ እንዲቀመጥ ወደ ውስጣችን መስገባት ማለት ነውና ጌታም ወደ እኛ ለመምጣትና ከኛ ጋር ለመኖር ይፈልጋል፡፡

እርሱን መፈለግ የሚገባን ያህል የማንፈልገው ከሆነ ምክንያቱ በንስሐ አገባባችን ላይ የሚጐድል ነገር መኖሩና እኛም ከኃጢአታችን ክብደት ለማዳን የተፈለገውን የሕማምና የሥቃይ መስዋዕትነት ልክ አለመገንዘባችን ነው፡፡ የኃጢአተ ይቅርታን ማግኘት አስፈላጊነት ስናውቅና ልምዱም ሲኖረን ብቻ እኛን ይቅር ለማለት ዘወትር ዝግጁ ሆኖ ወደማጠብቀን ጌታ ከልብ ተፀፅተን ፊታችንን ለማዞር የምንችለው ያኔ ብቻ ነው ከልብ በመነጨ ፍቅር እሱን መፈለግና መከተልም የምንጀምረው፣ ምክንያቱም ብዙ ኃጢአት ይቅር የተባለለት በፋንታው ደግሞ ብዙ ይወዳልና፡፡

"ስለዚህ ተስፋ የቆረጠውን ሁሉ በርታ አይዞህ አትፍራ እግዚአብሔር ሊታደግህ ይመጣል" ት. ኢሳያስ 35፡4

እግዚአብሔር ሁሉንም ነገሮች የሠራቸው ለራሳቸው ሲል አይደለም ነገር ግን ለታላቅ ፍጥረት ነው፡፡ ሁሉ ነገር ከተዘጋጀ በኋላ የዚህን ታላቅና ሰፊ ዓለም ንጉሥና ገዢ ሠራ ሰውን ፈጠረ፡፡ መለኮታዊ አስትንፋሱን በሰው ላይ ተነፈሰ፣ ልጁም አደረገው ከዚያም ገደብና ድንበር በሌለው በዘላለማዊ ደስታ ሰውን ተካፋይ እንዲሆንለት እጅግ ከፍተኛ ጉጉት አደረበት፡፡

ሆኖም ግን ሰው ታዛዥ ባለመሆኑ የተነሣ የእግዚአብሔርን እቅድ አበላሸ፡፡ ያም ሆኖ ግን እግዚአብሔር ጨርሶ አልተወውም፣ እራቀውም፡፡ ስለዚህ አዲስና እጅግ አስደናቂ የሆነ እቅድ አዘጋጀ በህልማችን እንኳን ጨርሶ ይሆናል ብለን ያላሰብነውን ዓይነት የሰውን ልጅ እርሱ ወዳዘጋጀለት ታላቅ ደስታ ለማምጣት ነው አዲሱን ዕቅድ የነደፈው፡፡ የሰው ልጅ ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፍ ዘንድ እግዚአብሔር ያለውን ታላቅ ጉጉት ለማሳየት በመለኮታዊ፣ ጥበብ፣ ሃይልና ፍቅር እስከ መናገር ደረጃ ደረሰ፡፡ አንድያና ብቸኛውን ልጁን የምስጢረ ሥላሴ ሁለተኛውን አካል የሆነውን ልጁን እጅግ አሳፋሪና አሰቃቂ የሆነውን የመስቀል ሞት እንዲሞትና በዚህም ሳቢያ የሰው ልጅ ፈጣሪው ለርሱ ያለውን ፍቅርና የዘላለምንም ደስታ እንዲያገኝ ያለውን ጉጉት እንዲገነዘብ ሁሉም ሰብዓዊ ፈጡር ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለስ ያንን ተወዳጅ ልጁን የሰው ልጆች ቤተሰብ አባል አድርጐ ወደ ምድር ላከው፡፡

እርሱ መለኮታዊ ሕይወት መልሶ ሰጥቶናል፣ በድጋሚ ልጆቹ አድርጐናል፣ የርሱ የሆነችው ቤተክርስቲያን አባል አድርጐናል በርሷ አማካይነትም እንደ እግዚአብሔር ልጅነታችን ይህንን ወደ ምድር የተላከውን አዳኝ ለነፍሳችን መጠበቂያ የምንወስደው ምግብና መጠጥ አድርጐ ሰጥቶናል፡፡ በሁሉም የሕይወት መከራዎችና ፈተናዎች ውስጥ ይጠብቀናል፣ ይመራናል፡፡

ምንጭ፡ የስብከተ ገና ወራትን መኖርና ማክበር

በሜሪ ሊዊስ

ትርጉም ሠብለወርቅ ጳውሎስ

  • Written by Super User
  • Hits: 1733
resurrection

ዘትንሣኤ 4ኛ

ኢየሱስ ተንሥቷልና ደስ ይበላችሁ!

ሉቃስ 24:33-44         ሐዋ. 11:1-8        1ጴጥ. 3:15-22            ቆላ. 3:1-25

ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በኋላ ደቀመዛሙርቱ እሱ ደጋግሞ ይነግራቸው የነበረውን ልብ ስላላሉት ተስፋ ቁርጠት ውጧቸው ነበር። ነገር ግን የትንሣኤ በኩር የሆነው ጌታችን ሞትን አሸንፎ ተነሥቶ በጽርኀ ጽዮን በፍርሃት ተንጠው በር ዘግተው ሞታቸውን ይጠብቁ በነበሩት መካከል ተገኝቶ ዓለም ሊሰጥም ሆነ ሊቀማ የማይችለውን ሰላሙን "ሰላም ለናንተ" በማለት አበሰራቸው። እኛም ዛሬ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ጌታ የሚያበስረን ሰላሙን ነውና በርሱ ትንሣኤ ዙርያ የነበሩትን ሰዎችና ሁኔታዎች እናስተንትን።

እስራኤልን ያድናል ብለን አስበን የነበረው ራሱ ሞተ፤ ወደ የመንደርና አገራችን መበታተን ካልሆነ ሌላ ምን ማለት እንችላለን ምንስ እናድርግ በማለት በተስፋ ቁርጠት ተሞልታችሁ የነበራችሁ እናንት የኤማሁስ ተጓዦች ሆይ! ጌታ ክርስቶስ እነሆ ሞትን አሸንፎ ተነሥቷልና ደስ ይበላችሁ፤ በኀዘን ውስጥ ሰምጣችሁ ባላችሁበት በአሁኑ ሰዓት በመካከላችሁ ተገኝቶ እየተናገራችሁ ነውና ልብ በሉት፤ ሳትሰሙት ከቀራችሁ ይጸጽታችኋል "በመንገድ ሲናገረንና መጽሐፍትን ሲያስረዳን ልባችን እንደ እሳት ይቃጠል አልነበረምን" ማለቱ አይጠቅምምና ድምጹን መስማቱንና መኖሩን ቻሉበት።

ሕያው የሆነውን እሱን ከሙታን መካከል በመፈለግ ላይ ያለሽውና በጌታሽ ፍቅር ተቃጥለሽ ባዶ መቃብር ላይ የምታለቅሺው ማርያም መግደላዊት ሆይ! ጌታ ከሞት ተነሥቶ አንቺንም ሊያነቃቃሽና የርሱን ትንሣኤ እንዳታስተውዪ የጋረደሽን ነገር ሊያስወግድልሽ ከኋላሽ ቆሟልና ዞር ብለሽ የፍቅርሽን ፍሬ ከእጁ ተቀበይ።

ኢየሱስ ተነሥቷል የሚል ብስራት እንደሰማችሁ ተጭኗችሁ የነበረው የፍርሃት ባርነት ከልባችሁ የተወገደና ጠላትን በመፍራት ሸጉራችሁ የነበራችሁትን በር ክፍታችሁ በድፍረት ወደ መቃብር የሮጣችሁ፤ ዓይነ ልቦናችሁ ተከፍቶ አስቀድሞ ስለራሱ የተናገረውን በማስታወስም ልባችሁ የተረጋጋ አሸናፊዎቹ ጴጥሮስና ዮሐንስ ሆይ! ኢየሱስ ተንሥቷልና ደስ ይበላችሁ።

ኢየሱስ ጌታችሁ ሞቶ ሲቀበር በተዘጋ ቤት ውስጥ በፍርሃት የተረበሻችሁ ደቀ መዛሙርት ሆይ! ሰላም በያንዳንዳችሁ ነፍስ ውስጥ ይነግሥ ዘንድና የዓለም ብርሃን ትሆኑ ዘንድ የቤታችሁ በር እንደተዘጋ ባላሰባችሁት ሁኔታ የሰላም ንጉሥ ተነሥቶ በመካከላችሁ ሰላምን እያበሰራችሁ ነውና ደስ ይበላችሁ። ንጉሥዋ ተነሥቶ በርስዋ ተገኝቷልና ጽርኀ ጽዮን በድጋሚ ዕልል ትበል ደስ ይበላት።

የዓለም ሕዝብ ሆይ! ኢየሱስ የባርነት ሰንሰለታችንን ሰባብሮ ሞትን በማሸነፍ ተነሥቷልና ዳግም ባርያ አይደለንም፤ ነጻ ወጥተናልና በያለንበት በኑሯችን እናመስግነው፤ ዕልል እንበልለት። "ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወስልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም፤ እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም" (ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ፤ ሞቶም ሞትን ረገጠ፤ ከእንግዲህ ወዲህስ ሐሴትና ሰላም ሆነ)።

የእግዚአብሔርና የእኛ እናት ለመሆን የተመረጥሽ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ! ሙሉ ዕድሜሽን ሳያቋርጥ ልብሽን በኀዘን ሰይፍ ይወጋው የነበረው የልጅሽ ስቃይ እስከ መጨረሻዋ ሰዓት ድረስ ከርሱ ሳትለዪ በኀዘን ባሕር ያሳጠመሽ ቢሆንም በተሰጠሽ የእግዚአብሔር ተስፋ ኪዳን መሠረት የጠላት ውድቀት የሆነውን የልጅሽ ድልና የነፍሳት ደኅንነትን ዋጋ በእጅሽ ይዘሽዋልና በኀዘን ሰይፍ የተወጋው ልብሽን የፈወሰ አምላክ ስሙ ይባረክ። አሜን።

አባ መስፍን ጸጋይ - ሲታዊ።

ከዚህ አስተንትኖ በመነሣት በእምነታችን አናኗር እይታ ራሳችንን ፈልገን ለማግኘት እንሞክር። የክርስቶስ ትንሥኤ ለዛሬ ማንነታችን ምን መልእክት እንዳለው የየግል ሕይወታችንንና ዙሪያገባችንን በመመርመር የእሱን ድል የየቀኑ ድል ለማድረግ እንወስን። እንደ ኤማሁስ ደቀ መዛሙርት "አዬ" የሚል የተስፋ ቁርጠት አዝማች ያለው ሕይወት ካለን ክርስቶስና ተስፋ ቁርጠት አብረው መኖር አይችሉምና ትንሣኤውን የኛ እናድርገው። ሕይወት ባዶ የመሆን መልእክትን የምታስተላልፍልን ሆኖ ከተሰማን በፊቱ ውድ የሆንንና ከነድካማችን ሊቀበለን የሚጠባበቀንን ሕያው ጌታ ጥሪ ለመቀበል አንዘገይ፤ ከሙታን የተነሣውን ክርስቶስ ለመገናኘት፣ ለመዳሰስና ለሌሎች ለማብሰር እንሩጥ። እርሱ በርግጥ ተነሥቷልና የጠወለገ ተስፋችን ያብብ ደስም ይበለን።

  • Written by Super User
  • Hits: 1176
Visit-of-Nicodemus

ዘኒቆዲሞስ

ከእኔነት ቅርፊታችን መውጣት - ዳግም መወለድ - ዘኒቆዲሞስ

ምስባክ ዘደብረ ዘይት፦ ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፤ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፤ ከመኢይንብብ አፉየ ግብረ ዕጓለ እመሕያው።

ልቤን ፈተንከው በሌሊትም ጎበኘኸኝ፤ ፈተንከኝ ምንም አላገኘህብኝም፤ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው።

መዝ.16:3-4 ንባባት፦- ዮሐ.3:1-11 - ሮሜ.7:1-18 - 1ዮሐ.4:18-21 - ሐዋ.5:34-42

ለሕማማት ሳምንት ብሎም ለብርሃነ ትንሣኤው በምንዘገጃጅበት በዚህ የጾም ወቅት ላይ የዛሬው ሰንበት ወንጌል የኒቆዲሞስንና የክርስቶስን ግላዊ ንግግር ያቀርብልናል። ኒቆዲሞስ አንድ ታሪካዊ ሰው መሆኑን ወንጌሉ አስረግጦ ቢነግረንም ግቡ ግን እንደወትሮው በኒቆዲሞስ ቦታ ራሳችንን አስቀምጠን ከኢየሱስ ጋር ግላዊ የነፍሳችንን ጉዳይ እንድንወያይ ለመጋበዝ ነውና ለዚህ ዓላማ የሚያግዙንን አንዳንድ ነጥቦች እንካፈል።

ኒቆዲሞስ በጊዜው በነበሩ የሰው መስፈርቶች በሙሉ "አንቱ" ሊያሰኙት የሚችሉ ነገሮችን ያሟላ ሰው እንደነበረ ወንጌል "ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ፣ የአይሁድ አለቃ፣ የእስራኤል መምህር መሆኑን" በማለት ያስረዳናል። በሰው እይታ አዋቂና የተከበረ ሰው እንደነበረ አያጠራጥርም፤ በክርስቶስም ዓይን የተከበረ መሆኑ ቢቀጥልም አዋቂነቱ ግን ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። ኢየሱስ "አንተ የእስራኤል መምህር ሆነህ ይህን አታውቅምን?" ሲለው ገና ማወቅ የሚገባው ብዙ ነገር እንዳለ ያሳየናል። ለኛ ይህ መነሻ ነጥብ ነው፤ በኢየሱስ ፊት ሁል ጊዜ ነገሮችን ለማወቅና ለማድረግ ዝግጁ መሆን አለብን።

ማንም ሰው በእግዚአብሔር ቃል ፊት ሁሉን ጠቅልሎ ሊያውቅ አይችልም። ስለ ደኅንነት ቢወራ ገና በየቀኑ ማወቅ የሚገባንና ማድረግ የሚጠበቅብን ነገር አለ፤ ስለ ማፍቀርና ይቅር ማለትም ቢነገር በየቀኑ የሚያጋጥሙንን ሰዎች ገና እንደ አዲስ ለማፍቀርና ይቅር ለማለት በየቀኑ ራሳችንን ማዘጋጀት አለብን እንጂ ባለፉት ጊዜያት አፍቅሪያለሁ፣ ይቅር ብያለሁ...ብለን የምንደመድመው ጉዳይ አይደለም። በሕይወት እስካለን ድረስ ዘወትር ለበለጠ ነገር መዘጋጀት አለብን። "እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሰው እንደገና ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም" የሚሉት የክርስቶስ ቃላት የሚያንጸባርቁትም እውነት ክርስትና አንዴና ለሁልጊዜ በአንድ ቀን ተአምራዊ ለውጥ ያከተመለት ሕይወት ሳይሆን ሁሌም ለማያልቀው የእግዚአብሔር ጸጋ ራስን ከፍቶ እንደ ሕጻን መሆንን የሚጠይቅ ጥሪ መሆኑን ነው። ድኛለሁ፣ አውቂያለሁ፣ ዳግም ተወልጃለሁ፣ በቃ... ብለን የቆምን ሰዎች እንዳንሆንና ሁለነገራችን በየቀኑ እያደገ ሲሄድ እምነታችንን በየቀኑ ሳናሳድገውና ሳንኖረው የሆነ ደረጃ ላይ ቆሞ እንዳይሆን ራሳችንን እንመርምር።

ኒቆዲሞስ የክርስቶስ ዳግም ተወልድ የሚለው ትእዛዝ ግራ ቢገባው "እንዴት ሊሆን ይችላል?" ይህ የአንዲት ነፍስ ቀጣይ ንግግር ነው። ነፍስ ስለማንነቷና ምንነቷን ከመጠየቅ መቼም ቢሆን አትቦዝንም። ሁሌም "እንዴት" ትላለች፤ እንዴትና ወዴት መጓዝ እንዳለባት ታስባለች። የሆነ ነገሮችን የምታውቅ ይመስላታል ሆኖም ግን ነገሮችን ጠንቅቃ አውቃ የመጨረስ ብቃት ስለሌላት በእግዚአብሔር ቃል ፊት ሁሌ "ምን፣ እንዴት ማድረግ አለብኝ" ማለቱ የግድ ነው። ምናልባት በሰው ፊት ስንቆምና ስንገኝ የፈለግነውን ስእላችንን ማስተላለፍ እንችል ይሆናል፤ በክርስቶስ ፊት ግን ገና ብዙ ማወቅ የሚገባን ነገር እንዳለ እንገነዘባለን። ለዚህም ነው በርሱ ቃል ፊት መምሰልና ማስመሰላችን ለማንነታችን ቦታቸውን የሚለቁት። በሰዎች ፊት መስለን የምንውለው ነገርና በክርስቶስ ፊት የሆንነው ነገር እንዲመሳሰል በጣርን መጠን ዳግም መወለድን እየተገበርነው እንሄዳለን።

መወለድ ማለት መለየት፣ ከአንድ ዓይነት አናኗር ወደሌላ ዓይነት መምጣት ማለት ነው። ልክ ሕጻን ሲወለድ ሕይወቱ ቢቀጥልም ከነበረበትና ራሱን ያኖርበት ከነበር ከእናቱ ማሕጽን መውጣት እንዳለበት በእምነትም ማደግ ካለብን እንዲሁ መላቀቅ የሚገባን ነገሮችን ማሰብ አለብን። ካለነርሱ ልንኖር የማንችል የሚመስለንን ነገር ለመተው መወሰን አለብን። ሕጻን ሲወለድ የምግብ ማስተላለፊያ የነበረው እትብቱ መቆረጥ የግድ ቢሆንም በሌላ መልኩ መመገቡን ይቀጥላል። እኛም መቆራረጥ ካለብን ሕይወት ክርስቶስ "ተወለድ/ጅ" ሲለን ህልውናችንን የሚፈትን ነገር መስሎን እንዴት ልንልና ልንሸሸው እንችል ይሆናል፤ እውነቱ ግን ያ ካልሆነ ማደግ አንችልም። ዛሬ በሕይወታችን ወደ ክርስቶስ ይበልጥ እናድግ ዘንድ መቆራረጥ ያለብን ነገር ምን ይሆን ብለን እናስተንትን።

ብዙ ጊዜ ራስ ወዳድነታችን ራስን ወደማየት ብቻ ያሳድገንና የእግዚአብሔርን ፈቃድና ሰዎችን ማሰቡ ይከብደናል። ነጋ መሸ "እኔ" ና ለኔ ብቻ በሚል ዓይነት መጓዝን እንመርጥ ይሆናል፤ ይህ ከሆነ ግን በክርስትና ማደጋችን አቁሟል ማለት ነው። ከእኔነት ቅርፊታችን ካልወጣን ከኛ ውጭ የሆነውን መገንዘብ አንችልም፤ ያልተፈልፈለ ማንነት ወይም ያላደገ እምነት ይዘን በሥጋ ወደፊት እንጓዛለን። በዚህ ዓይነት ስብእና የክርስቶስን ሕማማትና ትንሣኤ ማክበሩ ትርጉም አይኖረውምና የዛሬው ወንጌል ከማንነታች ወጥተን ለክርስቶስና ለሌሎች የመኖርን ሕይወት፣ በእምነታችን ከዕለት ዕለት ማደግን እንድንለማመድ ይጋብዘናል። ይህ ካልሆነ ክርስቶስ የከፈለውን ዋጋ ሁሉ እንዳልተከፈለልን እናደርገዋለንና ዳግም መወለድ የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ለእኔ በምን መልኩ ተግባራዊ አድርጌ ለዘንድሮው የክርስቶስ ትንሣኤ ብርሃን ራሴን ላዘጋጅ ብለን በቅዱስ ቃሉና በምስጢራቱ ፊት እናስተንትን።

  • Written by Super User
  • Hits: 903

  • Hits: 816

ዘመስቀል 2ኛ

መሸከም ያለመሸከም ሲሆን

የዛሬው ወንጌል ሲጀምር " ለብቻውም ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና። ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ብሎ ጠየቃቸው።" ይላል። ሰዎች ስለሆነ ነገር የሚሉትን መናገር አስቸጋሪ ሆኖ አይሰማንም። የሚሉት ነገር ይግባንም አይግባንም በመሰለንና በሚመቸን መልኩ አድርገን እንዲህ አሉ፣ ይላሉ...እንላለን። ለዚህም ነው ደቀ መዛሙርቱም "መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም። ኤልያስ፥ ሌሎችም። ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል ይላሉ" ያሉት። ክርስቶስ ይህን ሲጠይቃቸው ዋነኛ ነጥብ አድርጎ አይደለም፤ ይልቅስ ለሚቀጥለው ወሳኝ ጥያቄ መግቢያ እንዲሆን ነው።"እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው። " ደቀ መዛሙርቱ ይህን መመለስ ከቻሉ ብቻ ነው ሊለወጡ የሚችሉት፤ ስለዚህም ሕይወታቸው መለወጥ አለበትና ጠየቃቸው። ይህን ጥይቄ ለመመለስ ሐዋርያቱ እንደበፊቱ አልተሽቀዳደሙም፤ ብዙ አማራጭ ስም ለመደርደርም አልደፈሩም- ዝምታ ሆነ። የሌላን ማውራትና ማንጸባረቅ ቀላል ሲሆን የራስ የሆነ ምላሽ ለመስጠትና ለመወሰን ወደ ውስጣችን መግባት ግን ሁሌም ፈታኝ ነው።ቅዱስ ጴጥሮስ "ከእግዚአብሔር የተቀባህ ነህ" ብሎ ዝምታውን እስኪሰብረው ድረስ ምን ምን ብለው አስበው ይሆን? በርግጥ እነሱ ያሰቡትን ልንገምትና የሆነ ነገር ልንል እንችል ይሆናል፤ ግን አሁንም ለኛ ያ ምንም አይፈይድልንም።ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በሰሙትና በመሰላቸው ነገር ብቻ እንደሌሎቹ እየተጋፉ እንዲጓዙ አልፈለገም፤ ውስጣቸውን እንዲያዩና እንዲመረምሩ ጋበዛቸው። ለዘመናት ይህ እውነት አልተቀየረም። ክርስቶስ ስለኛ ክርስቲያኖች ያለው ሃሳብ በሱ ፊት የግላችን መልስ እንዲኖረን ነው። ዳር ዳር የሚል ክርስቲያን እንድንሆን አይፈልግም። በሕወታችን፣ በውሳኔያችንና በዕለታዊ ጉዟችን ከሌሎች የተለየ የእሱ እውቀት እንዲኖረን ይሻል። ስለዚህ ዕለታዊ ሕይወቴ ስለ ክርስቶስ ምን ይናገራል? ብለን እናስብ። ቆም ብለን ስለርሱ ማንነት እንድንወስን የዘወትር ክርስቲያናዊ ጥሪ ነው።ጴጥሮስ "ከእግዚአብሔር የተቀባህ (መሲሕ) ነህ" ሲለው ራሱ ክርስቶስ መሲሕ ነኝ ብሎ ከማወጁ በፊት ሕይወቱ ያንን ማወጅ ስላለበት ለሌላ አትናገሩ አላቸው። ይህ ለእኛ ያለው መልእክት ክርስትናችን ከውጫዊ ነገርና ከስም በላይ የሕይወት መሆን እንዳለበት ነው። ክርስቲያንነቴን አናኗሬ ቀድሞ መናገር አለበት። "ለማንም ይህን እንዳይነግሩ" ኢየሱስ አስጠነቀቃቸው የሚለው ሀሳብ የሚያስተላልፈው ሌላ መልእክት ሐዋርያቱ ገና መሲህ መሆን ምን ማለት እንደሆነ ስላልተረዱት ያልተረዱትን ነገር ማወጅ እንደሌለባቸው ለማሳሰብ ነው። እዚህም ላይ እምነታችንን ወይም ሃይማኖታችንን ብንጠየቅ ክርስቲያን፣ ካቶሊክ ማለታችን አይቀርም፤ ጥሩ በዚያ ማፈር የለብንም። ነገር ግን ምን ያህል ማወቅ የሚገባንንና የምንችለውን ያህል ስለ እምነታችንና ሃይማኖታችን እናውቃለን? ወይም ለማወቅ እንጥራለን? ክርስቶስ እሱን ሳናውቅ ስለርሱ እንድናወራ አይፈልግም።በዛሬው ወንጌል ቁ.23 ላይ የእርሱን መስቀል ተሸክመን እንድንከተለው ክርስቶስ ያዘናል። ሰው የሚከተለው ካለው ብቻውን አይደለም፤ መሪ አለው ማለት ነው። መንገድ የሚሳሳትና መድረሻው የሚያስጨንቀው ሰው በሕይወቱ መሪ የሌለውና የማይፈልግ ሰው ነው። ክርስቶስ ግን እኔ አለሁ እመራችኋለሁ ተከተሉኝ ይላል። ሕይወት በሆነ መልኩ ሸክም አላት፤ ሸክም ደግሞ ያለ መሪ እጥፍ ሸክም ነው። ስለዚህ እሱ መሪያችን ከሆነ መሸከማችን ያለመሸከም ይሆናል። እንዲሁም በተቃራኒው ክርስቶስን መሪያችን ካላደረግን ምንም ያልተሸከምንና ነጻ የሆንን ቢመስለንም ቅሉ ያለመሸከማችን ራሱ ሸክም ይሆንብናል።በሕይወታችን ያለንን ጓዝ ሁሉ ይዘን ከርሱ የሚያርቁንን አካሄዶቻችንን ሁሉ ለመካድ በመወሰን በቃሉና በመሥጢራት የሚጠብቀንን ጌታ አንተ መሪ ሁነን እንበለው።

መሸከም ያለመሸከም፤ ያለመሸከምም ሸክም ሲሆን።

የዛሬው ወንጌል ሲጀምር "ለብቻውም ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና። ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ብሎ ጠየቃቸው።" ይላል። ሰዎች ስለሆነ ነገር የሚሉትን መናገር አስቸጋሪ ሆኖ አይሰማንም። የሚሉት ነገር ይግባንም አይግባንም በመሰለንና በሚመቸን መልኩ አድርገን እንዲህ አሉ፣ ይላሉ...እንላለን። ለዚህም ነው ደቀ መዛሙርቱም "መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም። ኤልያስ፥ ሌሎችም። ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል ይላሉ" ያሉት። ክርስቶስ ይህን ሲጠይቃቸው ዋነኛ ነጥብ አድርጎ ስለሌሎችና ረብ ስለሌለው ነገር በመናገር የመጨዋወቻ ርእስ ለመክፈት ያህል አይደለም፤ ይልቅስ ለሚቀጥለው ወሳኝ ጥያቄ መግቢያ እንዲሆን ነው። ባብዛኛው ሰው ለሰው ግንኙነታችንን ልብ ካልነው ርእሶቻችን ነገን የማያዩ፣ ለዛሬ ምናልባትም ለተገናኘንባት ጊዜ ማሳለፊያ ብቻ የሚሆኑ ርእሶች ላይ የተመሠረቱ ንግግሮች እናዘወትር ይሆናል። ውስጣዊ ማንነትን የሚነካ ሀሳብ መካፈሉን እምብዛም አንደፍረውም፤ ስለ አየር ሁኔታ፣ ስለ አለባበስ፣ ስለ ምግብ፣ ስለ እገሌ/እገሊት...እናወጋለን፤ በርግጥ እነዚህ ርእሶች የዕለታዊ ሕይወታችን ክፍል ቢሆኑም በነርሱ ብቻ ሳንገደብ ክርስቶስ እኔ ሕይወት ነኝ ብሏልና ሕይወታችንን ርእስ ማድረጉ ተገቢ ነገር ነው። ለዚህም ምሳሌነት ነው ክርስቶስ ሐዋርያቱን ስለ ሌሎች ከጠየቀ ወደ ዋናውና ወደ ራሳቸው ያተኮረ ጥያቄ ያሻገራቸው።

"እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።" ደቀ መዛሙርቱ ይህን መመለስ ከቻሉ ብቻ ነው ሊለወጡ የሚችሉት፤ ስለዚህም ሕይወታቸው መለወጥ አለበትና ጠየቃቸው። ይህን ጥይቄ ለመመለስ ሐዋርያቱ እንደበፊቱ ማለትም "ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ?" ሲል በጠየቃቸው ጊዜ ሌሎች ስለርሱ የሚሉትን ለመንገር ፈጥነው አልተሽቀዳደሙም፤ ብዙ አማራጭ ስም ለመደርደርም አልደፈሩም- ዝምታ ሆነ። የሌላን ማውራትና ማንጸባረቅ ቀላል ሲሆን የራስ የሆነ ምላሽ ለመስጠትና ለመወሰን ወደ ውስጣችን መግባት ግን ሁሌም ፈታኝ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስ "ከእግዚአብሔር የተቀባህ ነህ" ብሎ ዝምታውን እስኪሰብረው ድረስ ምን ምን ብለው አስበው ይሆን? በርግጥ እነሱ ያሰቡትን ልንገምትና የሆነ ነገር ልንል እንችል ይሆናል፤ ግን አሁንም ለኛ ያ ምንም አይፈይድልንም።

ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በሰሙትና በመሰላቸው ነገር ብቻ እንደሌሎቹ እየተጋፉ እንዲጓዙ አልፈለገም፤ ውስጣቸውን እንዲያዩና እንዲመረምሩ ጋበዛቸው። ለዘመናት ይህ እውነት አልተቀየረም። ክርስቶስ ስለኛ ክርስቲያኖች ያለው ሃሳብ በሱ ፊት ስለርሱ የግላችን መልስ እንዲኖረን ነው። ዳር ዳር የሚል፣ ሌሎች የሚሉትንና የሚያደርጉትን ብቻ ለማስተጋባትና ለማስመሰል የታጠቀ ክርስቲያን እንድንሆን አይፈልግም። በሕይወታችን፣ በውሳኔያችንና በዕለታዊ ጉዟችን ከሌሎች የተለየ የእሱ እውቀት እንዲኖረን ይሻል። ይህም ግለ እውቀት ከርሱ ጋር ባለን ግንኙትነት ላይ ይመሠረታል። ስለዚህ ለኔ ክርስቶስ ዛሬ ማነው? እኔ ለእርሱ ምንድነኝ? ዕለታዊ ሕይወቴ ስለ ክርስቶስ ምን ይናገራል? ብለን እናስብ። ቆም ብለን ስለርሱ ማንነት እንድንወስን የዘወትር ክርስቲያናዊ ጥሪ ነው።

ጴጥሮስ "ከእግዚአብሔር የተቀባህ (መሲሕ) ነህ" ሲለው ራሱ ክርስቶስ መሲሕ ነኝ ብሎ ከማወጁ በፊት ሕይወቱ ያንን ማወጅ ስላለበት ለሌላ አትናገሩ አላቸው። ይህ ለእኛ ያለው መልእክት ክርስትናችን ከውጫዊ ነገርና ከስም በላይ የሕይወት መሆን እንዳለበት ነው። ክርስቲያንነቴን ከቃላቶቼ ይልቅ አናኗሬ ቀድሞ መናገር አለበት። "ለማንም ይህን እንዳይነግሩ" ኢየሱስ አስጠነቀቃቸው የሚለው ሀሳብ የሚያስተላልፈው ሌላ መልእክት፦ ሐዋርያቱ ገና መሲህ መሆን ምን ማለት እንደሆነ ስላልተረዱት ያልተረዱትን ነገር ማወጅ እንደሌለባቸው ለማሳሰብ ነው። እዚህም ላይ እምነታችንን ወይም ሃይማኖታችንን ብንጠየቅ ክርስቲያን፣ ካቶሊክ ማለታችን አይቀርም፤ ጥሩ በዚያ ማፈር የለብንም። ነገር ግን ምን ያህል ማወቅ የሚገባንንና የምንችለውን ያህል ስለ እምነታችንና ሃይማኖታችን እናውቃለን? ወይም ለማወቅ እንጥራለን? ክርስቶስ እሱን ሳናውቅ ስለርሱ እንድናወራ አይፈልግም።

በዛሬው ወንጌል ቁ.23 ላይ የእርሱን መስቀል ተሸክመን እንድንከተለው ክርስቶስ ያዘናል። ሰው የሚከተለው ካለው ብቻውን አይደለም፤ መሪ አለው ማለት ነው። መንገድ የሚሳሳትና መድረሻው የሚያስጨንቀው ሰው በሕይወቱ መሪ የሌለውና ምሪት የማይፈልግ ሰው ነው። ክርስቶስ ግን እኔ አለሁ እመራችኋለሁ ተከተሉኝ ይላል። ሕይወት በሆነ መልኩ ሸክም አላት፤ ሸክም ደግሞ ያለ መሪ እጥፍ ሸክም ነው። ስለዚህ እሱ መሪያችን ከሆነ መሸከማችን ያለመሸከም ይሆናል። እንዲሁም በተቃራኒው ክርስቶስን መሪያችን ካላደረግን ምንም ያልተሸከምንና ነጻ የሆንን ቢመስለንም ቅሉ ያለመሸከማችን ራሱ ሸክም ይሆንብናል። አንድ ክርስቲያን ክርስቶስን ተከተለ ማለት መስቀል መሸከም ዋነኛ መለያው ነው፤ መስቀል ለክርስቲያን ደግሞ በርሱ ድነናል፣ ከብረንማልና መርገም ሳይሆን ፍቅርና ክብር ነው።

በሕይወታችን ያለንን ጓዝ ሁሉ ይዘን፤ ከርሱ የሚያርቁንን አካሄዶቻችንን ሁሉ ለመካድ በመወሰን በቃሉና በመሥጢራት የሚጠብቀንን ጌታ አንተ መሪ ሁነን እንበለው።

  • Written by Super User
  • Hits: 815

Subcategories

በዚህ ጽሑፍ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ጽሑፋት

ተወራራሽ ርእሶች