ንኡሳን ገጾች
Chaplet of Divine Mercy
Home (ቅድመ ገጽ) ቅዱስ አውጎስጢኖስ ማነው

የቅዱስ አውጎስጢኖስ የሕይወት ታሪክ


ቅዱስ አውጎስጢኖስቅ. አውጎስጢኖስ ክክርስትና ደማቅ ከዋክብት አንዱ ነው። አፍሪካ ለዓለም ካበረከተቻቸው ድንቅዬ ልጆቿ ተጠቃሽ ሲሆን የዕድሜውን ማለትም ከኖራቸው 75 ዓመታት ውስጥ አራቱን ዓመታት ብቻ ነበር ከአፍሪካ አህጉር ውጭ ያሳለፈው።

በምዕራቡ ዓለም በፍልስፍናው ዘርፍ በተለይም የፕሌቶን ሃሳብ ከክርስትና እይታ ጋር በማተሳሰሩ በኩልና የራሱም አዳዲስ እይታዎችን በሚመለከት ሰፊ አበርክቶ ያለው ፈላስፋ፣ በነገረ መለኮት ረገድም የተከበረና ለዘመናት የዘለቀ አዎንታዊ ጫናን የፈጠረ ነገረ መለኮታዊ ሲሆን በክርስትና እምነት አናኗሩም በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ታላቅ ተብለው ከሚታወቁት ቅዱሳኖች አንዱ ነው።

ቅ. አውጎስጢኖስ ከልጅነቱ ጀምሮ መንፈሳዊ ፍላጎቱን የሚያረካ እውነትን ሐቅንና የሕይወት መመሪያን ለማግኘት በልዩ ልዩ የፍልስፍና ማዕበል ውስጥ ገብቶ ጭንቀትን ያተረፈ፤ በሕይወቱ እጅግ የበዛ ውጣ ውረድ የገጠመውና በመጨረሻም የክርስትና እምነትን በመቀበሉ ታላቅ የሕይወት ለውጥን ያሳየ የነፍስ ሰላም፣ የኅሊና እርጋታና የአእምሮ ብርሃን ያገኘ ሰው ነው። በዚህም ሁኔታ የሕይወት ትግል ሁሉ መፍትሔ ክርስትና መሆኑን አስመሰከረ።

የቅዱሳን ሕይወት የክርስቲያን አናኗር መመሪያ ነውና ዛሬም ቢሆን በማንነቱ እውነተኛ እፎይታን ለሚመኝ ሰው በተለይም የዘመኑ ወጣት እውነተኛ የማይለወጥ ማረፊያ ፍለጋ ላይ ስለሚገኝ የዚህ ቅዱስ ታሪክ መመሪያና መነቃቂያ ሊሆነው ይችላልና ክርስቲያን ከመሆኑ በፊትም ሆነ በኋላ፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለነፍሳት ደኅንነት፣ ለእግዚአብሔርም ክብር ያበረከተውን አገልግሎትና ያሳለፈውን ቅዱስ ሕይወትን በጣም አጠር ባሉ ተከታታይ ክፍሎች ልናቀርብላችሁ እንወዳለን።

(ከታች ያሉትን ርእሶች በመጫን ማንበብ ይችላሉ - ሙሉ ታሪኩ ተጠናቆ እስከሚቀርብ ገጹን በየጊዜው ይጎብኙት ቀጣይ አዳዲስ ክፍል ይኖረዋል)


Title Filter     Display # 
# Article Title Author Hits
1 ክፍል 9 - የቅዱስ አውጎስጢኖስ ሥነ ጽሑፋዊ አበርክቶ Administrator 195
2 ክፍል 8 - ቅዱስ አውጎስጢኖስና መናፍቃን Administrator 196
3 ክፍል 7- የአውጎስጢኖስ ጳጳስ መሆን Administrator 254
4 ክፍል 5 - የአውጎስጢኖስ ይበልጥ ወደ ክርስትና ማዘንበል Administrator 265
5 ክፍል 6 - የአውጎስጢኖስ እናት ሞኒካ መሞት Administrator 191
6 ክፍል 4 - ከሰሜን አፍሪካ ወደ አውሮጳ Administrator 258
7 ክፍል 2 - አእምሮ ወደ እውነት ልብም ወደ ደስታ ይመጥቃል! Administrator 220
8 ክፍል 3 - አውጎስጢኖስ የማኒ ትምህርትን ስለመቀበሉ Administrator 177
9 ክፍል 1 - አንተ ፈጠረኸዋልና ባንተ ዘንድ ካልሆነ በቀር ልባችን በሌላ አያርፍም Administrator 281
 
የሳምንቱ መልእክት
"ለሰው ይኽን ያህል ታላቅ ክብር ለመስጠት ያነሳሳህ ምን ይሆን?...ወደር የሌለው ፍቅርህ እንደሆነ አይጠረጠርም! በፍቅሩ ተማርከሃል፤ በአውነትም በፍቅር ፈጥረኸዋል፤ በፍቅርም ዘላለማዊ መልካምነትህን የሚያጣጥም ስብእናን ለግሰኸዋል።" ቅድስት ካተሪና ዘሲየና
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ያን መዝሙሮች (ብዛት 110!)
ባለፉት 12 ሰዓታት የጎብኚዎች አገር
Top 8:
Ethiopia flag 25%Ethiopia (4)
Netherlands flag 19%Netherlands (3)
Unknown flag 19%Unknown (3)
Moldova, Republic of flag 12%Moldova, Republic of (2)
Germany flag 6%Germany (1)
Russian Federation flag 6%Russian Federation (1)
Switzerland flag 6%Switzerland (1)
United States flag 6%United States (1)
16 visits from 8 countries