ንኡሳን ገጾች
Chaplet of Divine Mercy
Home (ቅድመ ገጽ) ዜናዎች

ከዓለም ዙሪያ የቤተ ክርስቲያን ዜናዎች

ፍልሠታ ለማርያም

ራድዮ ቫቲካን- ክርስትና የሚያበስረው ደኅንነት የምንወደውን ዘለዓለማዊ ሕይወት እንጂ የማይጨበጥ ደኅንነት ኣይደለም
ቅዱስ ኣባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ ትናንትና ረፋድ ላይ ለዕረፍት ከሚገኙበት ካስተል ጋንደልፎ ሓዋርያዊ አዳራሽ የመልኣከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ‘እመቤታችን ድንግል ማርያም እንደ ክርስቶስ ልጇ ሞትን አሸንፋ በነፍስዋና በሥጋዋ በሁለመናው ሰማያዊ ክብር እንደተጐናጸፈች እናምናለን’ ሲሉ በላቲኑ ሥርዓተ ኣምልኮ ከ5 ቀናት በፊት የተዘከረውን የፍልሠታ በዓል የተመለከተ ትምህርት ሰጥተዋል።
የፍልሠታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚከተለዉን ስብከት ሰብከዋል።

Last Updated (Friday, 20 August 2010 12:26)

 

“ካህን ለቤተ ክርስትያን እና ለዓለም ጸጋ ነው”

ራድዮ ቫቲካን - እሑድ እኩለ ቀን ላይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎትን ሲያሳርጉ ባሰሙት ስብከት፣ የእንተ ላእለ ኵሉ (ካቶሊካዊት) ቤተ ክርስያን ካህናት በሰው ልጅ ታሪክ ለመንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ኅዳሴ መረጋገጥ የደረሷቸው መጻሕፍት፣ የሰጡት አብነት እና አስተዋጽኦ የማይካድ ብቻ ሳይሆን የሚደነቅ መሆኑን   አመልክተዋል።

በመቀጠልም ለአንድ ዓመት በኵላዊት ቤተ ክርስትያን የተከበረውንና ባለፈው ሳምንት የተጠናቀቀውን የክህነት ዓመት መዝጊያ ምክንያት በማድረግ ከመላ ዓለም የተወጣጡ ከ15 ሺሕ በላይ የሚገመቱ ካህናት የተሳተፉበት በሮማ የተካሄደው ዓቢይ በዓል ፈጽሞ የማይረሳ የዘወትር ትውስታ እንደሚሆን ገልጠው፣ በዚህ የክህነት ዓመት ምክንያት እግዚአብሔር ለኵላዊት ቤተ ክርስትያን ለሰጠው ጸጋዎች ምስጋናን በማቅረብ፣ የታደሉት ጸጋዎች ማንም ሊለካው የማይቻል ቢሆንም ፍሬው በግልጽ የታየና ገና ተትረፍርፎ የሚታይ ነው ብለዋል።

ካህን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልብ ለቤተ ክርስትያን እና ለዓለም የሰጠው እና የሚሰጠው ጸጋ መሆኑም አስረድተው፣ ካህናትን የፍቅር ሥልጣኔ የመጀመሪያ አገልጋዮች በማለትም ገልጠዋቸዋል። ቅዱስ ዮሓንስ ማሪያ ቪያነይ እና ባለፈው ሳምንት ቅድስት ቤተ ክርስትያን በቫርሳቪያ ብፅእና ያወጀችለት የደም ሰማዕት የፖላንድ ተወላጅ ካህን ኣባ ጀርዝይ ፖፒየሉስዝኮን በመጥቀስ ለክህነት ሕይወት አብነት ናቸው ካሉ በኋላ፣ ቅዱስ አባታችን መላው ውሉደ ክህነትን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጥበቃ በማማጸን፣ ባለፉት ጥቂት ቀናት ቅድስት ቤተ ክርስትያን ብፅእና ያወጀችላቸውን በማሰብ፣ በተለይም ደግሞ ዓለማዊ ምእመን ጋዜጠኛ ማኑኤል ሎዛኖ ጋሪዶ፣ ሕመም እና ስቃይ ሳይበግረው፣ ሥራውን እና ክርስትያናዊ ኃላፊነቱን በመወጣት የመሰከረው እምነት በቅድሱ ቁርባን ላይ የነበረው ፍቅር የሕይወቱ ማእከል በማድረግ የኖረው ለሁሉም ጋዜጠኞች አብነት ነው ብለው፣ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰው በብዙ ሺሕ ለሚገመተው ምእመን ቡራኬ በመስጠት መልካም እሁድን ተመኝተው የዕለቱን አስተምህሮ አጠቃለዋል።

Last Updated (Tuesday, 15 June 2010 13:06)

 

የሰው ልጅ በክፋት ላይ ድልን ለመቀዳጀት የክርስቶስ መስቀል ያሰፈልገዋል

ራድዮ ቫቲካን -  ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛው ከትላንትና በስትያ ለቆጵሮስ ውሉደ ክህነት፣ ገዳማውያን እና ዲያቆናት በኒቆስያ በሚገኘው በቅዱስ መስቀል ቤተ ክርስትያን የቀረበውን መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት፦ ብዙዎች ክርስትያን የስቃይ የእስራት እና የግርፋት ምልክት የሆነውን መሣሪያ እንዴት ያመልካሉ በማለት ይጠይቁ ይሆናል፣ ለኛ ክርስትያኖች ይህ መሣሪያ ስለእኛ ብሎ ውርደታችንን የራሱን በማድረግ እኛን በማዳን በማያዳግም ተግባር የእግዚአብሔር ፍቅር በክፋት ላይ ድል የነሳውን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በመሆኑ፣ የድህነታችን ምልክት ነው።

መስቀል ተራ የግል የአምልኮ መግለጫ መሣሪያ እና የመለያ ምልክት ብቻ ሳይሆን ከተአምኖተ ኃይማኖት ወይም ካንድ የፍልስፍና አመለካከት አስገዳጅነት የሚሰጥ ምልክት ሳይሆን ስለ ተስፋ፣ ስለ ፍቅር፣ ሁከት በሰላም መሣሪያ ውድቅ እንደሚሆን የሚያበስር እግዚአብሔር ትሁታንን ከፍ ያደረገበት መለያየትን ውድቅ ያደረገበት ፍቅር በጥላቻ ላይ ድል የነሳበት የድህነት ታሪክ የሚያወሳ ምልክት ነው ብለዋል።

ስለዚህ የተሰቀለውን ኢየሱስን ስናበሥር እራሳችን ወይንም እኛነታችንን ሳይሆን የምናከብረው፣

Last Updated (Wednesday, 09 June 2010 10:28)

 

ቱርክ ውስጥ አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲይን ጳጳስ ተገደሉ።

bishop_pardovese_insideIndependent Catholic News -Thursday, June 3, 2010 - እስከንደሩን በምትባለው አንዲት የቱርክ ከተማ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ሉዪጂ ፓዶቨዜ (63 ዓመት ዕድሜ)  በትላንትናው ዕለት በስለት ተወግተው መገደላቸው ታወቀ። በሜዲትራንያን ወደብ አጠገብ በሚገኘው የበጋ መኖሪያ ቤታቸው ጓሮ ውስጥ በነበሩበት ወቅት ከአራት ዓመታት በላይ መኪና በማሽከርከር ያገለግላቸ በነበረው ሰው ጥቃቱ የተፈጸመባቸው መሆኑም ተገልጿል። የቱርክ ባለሥልጣናት ይህ ሁኔታ ጸረ ክርስቲያን ጥላቻዊ አቋምን ያለመ አይደለም ብለዋል። የቱርክ ፖሊስ ገዳዩን በእስር የያዙት ሲሆን ሰውየው ያልተረጋጋ አእምሮ ያለውና ከበድ ያለ ሥነ ልቦናዊ ችግር ውስጥ መሆኑን አሳውቀዋል።

ትውልደ ጣልያን የሆኑት አቡነ ፓዶቬዘ በአናቶሊያ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ እንደራሴና የቱርክ ጳጳሳት ጉባኤ ኀላፊ የነበሩ ሲሆን ከጥቃቱ በኋላ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል በመወሰድ ላይ ሳሉ ነበር ነፍሳቸው ያለፈችው። ር.ሊ.ጳ. በቆጵሮስ በሚያደርጉ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለአጃቢነት ወደዚያው ሊያመሩ በዝግጅት ላይ ነበሩ።

ይህ ግድያ ምንም እንኳ ሃይማኖታዊ ምክንያት የሌለው ቢመስልም በቱርክ ውስጥ በቅርብ ዓመታት በክርስቲያኖች ላይ የተወሰኑ ጥቃቶች ተሰንዝረዋል። እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም. በአገሪቱ ምዕራብ በምትገኘው ኢዝሚር በምትባል ከተማ ልክ ቅዳሴ እንደጨረሱ አንድ የካቶሊክ ካህንን የ19 ዓመት ወጣት ወግቶ ያቆሰላቸው ሲሆን፤ በዚያኑ ዓመት በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ አሳታሚ ድርጅት ውስጥ የሚሠሩ ሦስት ክርስቲያኖች መገደላቸው ሲታወቅ በ2006 ዓ.ም. ደግሞ 16 ዓመት እድሜ ያለው ልጅ አባ አንድሬያ ሳንቶሮ የተባሉትን ካቶሊካዊ ካህን በጸሎት ላይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሳሉ ከጀርባ በኩል ተኩሶ እንደገደላቸውም የሚታወቅ ነው።

Last Updated (Friday, 04 June 2010 22:31)

 

"ምእመናን ሁሉ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ጸሎት እንዲያደርጉ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡" - አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን

 

"በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፡ በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሣይሆን፤ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ
Abatachinበመመኘት ሣይሆን ጎብኙት" (1 ጴጥ. 5፡ 2)፡፡

 

መግቢያ

ከሁሉ አስቀድሜ ይህ ፕሮግራም በመዘጋጀቱ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ስም የተሰማኝን ደስታ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ "ከችግር መላቀቅ፤ የምግብ ዋስትና ማግኘት፤ ቋሚ ሥራ ማግኘት፤ ኃላፊነቶችን ያለ አድሎ መካፈል፤ ከጭቆና ሁሉ ነጻ መሆን፤ ሰብአዊ ክብሮችን ተከብሮ መኖር፤ የትምህርት ዕድል ማግኘት፤ የመኖር ዋስትናው ተጠብቆ መኖር፤ በአጠቃላይ የተሻለ ኑሮ መኖር" የኢትዮጵያ ሕዝቦች ምኞት ነው (የሕዝቦች እድገት 6)፡፡ "እያንዳንዱ ዜጋ መሪዎቹን መምረጥ የራሱ መብትና ኃላፊነት መሆኑን በማወቅ የመምረጥ መብቱን ተጠቅሞ ለሕዝቦች የጋር ጥቅም አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅበታል፤ ለሕዝብ አገልግሎት ራሳቸውን ለመሠዋት እጩ አድርገው የፖለቲካ ሸክም ለመሸከም የሚወዳደሩ ግለሰቦችን በአክብሮት እንመለከታለን" (ቤተክርስቲያን በዘመናችን 75)፡፡

1/ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት፡ በተቻለ መጠን በተለያዩ ፓርቲዎች መካከል ያሉ የምርጫ ልዩነቶችን ለማጥበብ የማያቋርጥ የመግባባት ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል ብለን እናምናለን፡፡

2/ የኃይል አጠቃቀምን ማስቀረት፡ በምርጫ ወቅትና በኋላም መራጮች ሆኑ ሥነ ሥርዓት አስከባሪዎች የኃይልና የአመጽ አጠቃቀምን ጨርሶ ማስቀረት፡፡ በአጠቃላይ የሰው ክቡርነት ከሀሳብ ልዩነታችን በላይ መሆኑን አውቀን ለሰላም የሚቻለውን ዋጋ መክፈል ተፈጥሮአዊ ግዴታችን ነው፡፡......

Last Updated (Friday, 04 June 2010 22:36)

 

እግዚአብሔርን በቍርጠኝነትና በታማኝነት ማገልግል ያስፈልጋል።

ቫቲካን ሬድዮ - ትናንትና እሁድ ረፋድ ላይ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይና በአከባቢው ያሉ ጐደናዎችን ያጥለቀለቀ ከሁለት መቶ ሺ በላይ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ የንግሥተ ሰላም ጉባኤ አስተምህሮ አቅርበዋል። ምእመናኑ ከመላው ጣልያን የተሰበሰቡ ሆነው፣ ምክንያቱም በዚሁ ፈታኝ ጊዜ ምእመናን ቅዱስነታቸውን በጸሎትና በአካል እጐናቸው መሆናቸውን በማሳወቅ ድጋፋቸና አጋርነታቸውን ለመግለጥ መሆኑን ከቅድስት መንበር የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።
ቅዱስነታቸው የንግሥተ ሰማያት ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ይህንን ትምህርት ሰጥተዋል፦

Last Updated (Saturday, 05 June 2010 19:45)

 

የብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ቅብዓተ ጵጵስና ተከናወነ

Abune_LissaneChristosየብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ የአዲስ አበባ ካቶሊካዊ ሰበካ ረዳት ጳጳስ ቅብዓተ ጵጵስና ዕሁድ ሚያዝያ 10 ቀን 2002 ዓ.ም አዲስ አበባ ካቶሊክ ካቴድራል በብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ካቶሊካውያን ዘኢትዮጵያ እጅ በደማቅ መንፈሳዊ ስነሥርዓት ተከናውኗል፡፡

ብፁዕነታቸው ከማለዳው በ1፡15 በብፁዓን ጳጳሳት፣ ቁጥራቸው በርካታ በሆነ ካህናት፣ መዘምራን፣ የብፁዕነታቸው ቤተሰብና ምዕመናን ታጅበው የዑደት ሥነስርዓት የተካሄደ ሲሆን በስነስርዓቱ ላይ ብፁዕ አቡነ ጢሞቲዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የቅድስት ስላሴ ኮሌጅ ጳጳስ/ዲን ክቡር አቶ ግርማ ብሩ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር፣የተለያዩ ሃይማኖቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ካቶሊካዊ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተው ነበር፡፡

ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ለቀጳጳሳት ካቶሊካውያን ዘኢትዮጵያ ቅብዓተ ጵጵስናውን በሰጡበት ወቅት ባሰሙት ቃለምዕዳን ለእግዚአብሄር ምስጋና ይድረሰው ካሉ በኋላ

Last Updated (Wednesday, 19 May 2010 21:39)

 

የሆሳዕና ሃገረስብከት ምስረታ በታላቅ ድምቀት ተከበረ - የሃገረስብከቱ አዲስ ጳጳስ ቅብዓተ ጵጵስና ተከናወነ

የአዲሱ ሆሳዕና ሀገረስብከት ምስረታ ሚያዝያ 3 ቀን 2002 ዓ.ም በሆሳዕና ካቴድራል በታላቅ ድመቀት ተከብሮ ውሏል፡፡ የሃገረስብከቱ የመጀመሪያ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ወልደጊዮርጊስ ቅብዓተ ጵጵስናም በብፁዕ አቡነ ብርሀነየሱስ ሊቀጳጳሳት ካቶሊካውያን ዘኢትዮጵያ እጅ ተከናውኗል፡፡

abune woldeghiorghisበዕለቱ ብፁዕ ለቀጳጳሳት ጆርጅ ፓኒኩለም የቫቲካን አምባሳደር በኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት፣ክቡር አባ ፓየስ የአሜሲያ (የምስራቅ አፍሪካ ጳጳሳት ጉባዔ ጠቅላይ ጸሃፊ፣ ክቡር አባ ሐጎስ ሐይሽ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት ጠቅላይ ጸሐፊ፣ የተለያዩ ሃይማኖቶች ተወካዮች፣ ክቡር ዶ/ር ሺፈራው ተ/ማርያም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር፣ ኩቡር አቶ መለሰ አለሙ የሃዲያ ዞን አስተዳዳሪ፣ አቶ ታደሰ ሮሞ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ኣስተዳዳሪ፣ ከመላዋ ኢትዮጵያ፣ ከሆሳዕናና አካባቢዋ የተውጣጡ፣ ካህናት፣ ደናግልና ምዕመናን እንዲሁም የብፁዕነታቸው ቤተሰቦች ተገኝተዋል፡፡

በበዓሉ ላይም በሆሳዕናና በኣካባቢዋ የስብከተ ወንጌል እንዴት እንደተጀመረና እንደተስፋፋ የሚያብራራ አጭር ታሪካዊ ዘገባ ቀርበዋል፡፡...

Last Updated (Wednesday, 19 May 2010 21:42)

 

ፕሬዚዳንት ግርማ የካሪታስ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንትን አነጋገሩ

አዲስ አበባ, የካቲት 30 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) - ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የካሪታስ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ካርዲናል ኦስካር ሮድሪጌዝ ማራዲጋን በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

ካርዲናል ኦስካር ሮድሪገዝ ማራዲጋዝ ከውይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞች እንዳስታወቁት ውይይቱ በዋናነት ያተኮረው ካሪታስ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ እያከናወነ ባላቸው የልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ ነበር፡፡ በዚህም ድርጅታቸው ኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ያለችውን ልማት የማገዝ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በተለይም በትምህርት ዘርፍ ኢትዮጵያን ለማገዝ በሚያደርገው ጥረት በኢትዮጵያ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ለመገንባት በሂደት ላይ ይገኛል፡፡ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲን በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች የማስፋፋት ፍላጎት አለው ማለታቸውን የዘገበው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ብርሃነየሱስ በበኩላቸው ካሪታስ ኢንተርናሽናል በመላው ዓለም በ162 አገሮች የልማትና የበጎ አድርጎት ተግባራት ላይ እንደሚሳተፍ ገልጸዋል፡፡

 

ኃጢአትን መቋወም ኃጢአተኛን ግን መንከባከብ አለብን

ቫቲካን ሬድዮ - ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛ አሑድ ዕለት ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ባቀረቡት ትምህርትነበር "ኃጢአትን መቋወም ኃጢአተኛን ግን መንከባከብ አለብን" ያሉት። ቅዱስነታቸው የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመመርኰስም የሚከተለውን ትምህርት ሰጥተዋል:- "ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ ዛሬ 5ኛ የዘመነ ጾም እሁድ ይዘናል፣ የዛሬው ቃለ ወንጌል ስለ በዝሙት የተገኘችውን ሴት ኢየሱስ ከሞት ቅጣት ሲያድናት እንመለከታለን፣ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 8:1-11 የተመለከትን እንደሆነ ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ተቀምጦ ሕዝቡን እያስተማረ ጸሐፊዎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ሕግ ተወግራ መሞት የነበረባትን በምንዝርና የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጥዋት። ኢየሱስ እንዲፈርዳት ፈልገው ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። ይህንን ያሉት ደግሞ የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ነው። ሁኔታው እጅግ ከባድ ነው።...

Last Updated (Thursday, 25 March 2010 21:28)

 

ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው የሱዳን ጳጳሳትን አመሰገኑ

MARCH 15, 2010 (Zenit.org) - ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው ቅዳሜ ዕለት በየአምስት ዓመቱ ለሚደረገው ጉብኝት እርሳቸው ጋር ለመጡት የሱዳን ጳጳሳት ለአሥርት ዓመታት አገሪቱን ያሰቃየው ግጭትን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ጳጳሳቱ በማበርከት ላይ ያሉትን ሚና ምክንያት በማድረግ ያላቸውን አድናቆትና ምስጋና ገለጡ።

ር.ሊ.ጳ. በሱዳን ውስጥ ሰላም ይጠናከር ዘንድ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ አንደኛው ነገር መከባበርንና መግባባትን የሚያሳድግ በሃይማኖቶች መካከል የሚደረግ ውይይት በተለይም ከእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር የሚደረገውን ንግግር ማሳደግ መሆኑን ጠቁመዋል።

ቀደም ብለውም ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ በሱዳን ዕርቅ ይወርድ ዘንድ ቤተክርስቲያን ከብዙ ዓመታት ጀምራ ለምታደርገውም ጥረት አድንቆታቸውን ገልጠዋል።

Last Updated (Tuesday, 16 March 2010 07:03)

 
More Articles...
የሳምንቱ መልእክት
"ለሰው ይኽን ያህል ታላቅ ክብር ለመስጠት ያነሳሳህ ምን ይሆን?...ወደር የሌለው ፍቅርህ እንደሆነ አይጠረጠርም! በፍቅሩ ተማርከሃል፤ በአውነትም በፍቅር ፈጥረኸዋል፤ በፍቅርም ዘላለማዊ መልካምነትህን የሚያጣጥም ስብእናን ለግሰኸዋል።" ቅድስት ካተሪና ዘሲየና
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ያን መዝሙሮች (ብዛት 110!)
ባለፉት 12 ሰዓታት የጎብኚዎች አገር
Top 8:
Ethiopia flag 25%Ethiopia (4)
Netherlands flag 19%Netherlands (3)
Unknown flag 19%Unknown (3)
Moldova, Republic of flag 12%Moldova, Republic of (2)
Germany flag 6%Germany (1)
Russian Federation flag 6%Russian Federation (1)
Switzerland flag 6%Switzerland (1)
United States flag 6%United States (1)
16 visits from 8 countries