Font Size

Cpanel

Cistercians In Ethiopia - Ethiopian Catholic Church

ብጹዕ ገብረሚካኤል ሰማዕት

የብፁዕ ገብረ ሚካኤል አጭር ሰማዕታዊ ገድል

የብፁዕ ገብረ ሚካኤል አጭር ሰማዕታዊ ገድል

ብጹዕ ገ/ሚካኤል በ 1788 በጎጃም ልዩ ስሙ ዲቦ በተባለ አውራጃ ተወለዱ። ከልጅነታቸው ጀምረው የአገራችንን ትምህርት ማለትም ዜማ፡ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ቅኔ ወዘተ. . . ለመማር ተሰማሩ። በትምህርት ትጋታቸውና በውጤታቸው መምህሮቻቸው በጣም አደነቁዋቸው። ይህን ሁሉ መንፈሳዊ እውቀት ካካበቱ በኋላ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር በሙሉ ልባቸው ሊሰጡ ፍላጎት ዕቅድ ስለነበራቸው በ25 ዓመታቸው በመርጡለ ማርያም ገዳም ገቡ። በጣም ጎበዝና ከፍተኛ የዕውቀትና የእውነት ጥማት ስለነበራቸው ከገዳም ወደ ገዳም ይዘዋወሩ ነበር። እንደዚህም እያሉ ሲታገሉ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ሕሊናቸውን ያስጨንቅ የነበረው የሃይማኖት ልዩነትና ጭቅጭቅ ገጠማቸው።

በዚህም ዕረፍት አጥተው ተጨንቀው "ጌታዬና መድኃኒቴ፡ ጽድቅ የት እንደምትገኝ ግለጥልኝ፡ አንተ ጻድቅ እንደሆንክ አምናለሁ። ጻድቅ ነኝ፤ ትክክለኛው የኔ ነው ወዘተ . . . የሚሉኝ ብዙዎች ናቸው፤ እኔ ግን ጽድቅን ሳትበላሽ ከምንጭዋ ላገኛት እፈለጋለሁ" እያሉ ጸለዩ። እግዚአብሔርም

Read more: የብፁዕ ገብረ ሚካኤል አጭር ሰማዕታዊ ገድል

  • Written by Super User
  • Hits: 539
justin de jacobis

የቅዱስ አቡነ ያቆዕብ ዩስጢኖስ ታሪክ

የቅዱስ አቡነ ያቆዕብ ዩስጢኖስ ታሪክ

ቅዱስ አቡነ ያዕቆብ ዩስጥኖስ በ1800 እ.ኤ.አ በኢጣልያ ሳምፍል በተባለ መንደር ተወለዱ። በ1818 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ወደ ላዛሪስት /ማኅበረ ልኡካን/ ገዳም ገቡ። እ.ኤ.አ. በ1824 ዓ.ም. ሢመተ ክህነት ተቀበሉ። በናፖሊ ከተማ ለድሆች ወንጌልን እያስተማሩም በመንፈስና በሥጋ እያገለገሉ ሳሉ በመስከረም ወር 1838 እ.ኤ.አ የፕሮፓጋንዳ ፊዴ (በቫቲካን የስብከተ ወንጌል ክፍል) ኃላፊ የነበሩ ሞሴኝር ቪቶ ጓሪኒ አቡነ ያዕቆብ ወደ ነበሩበት ገዳም በእንግድነት መጡ። አቡነ ያቆዕብ ከእንግዳው ጋር ስለ ስብከተ ወንጌል ሲነጋገሩ ቤተክርስቲያን ወደ ኢትዩጵያ የሚላኩ ሰባኪያን ትፈልጋለችና ኃላፊዎች ቢፈቅዱልዎት መሄድ ይፈቅዳሉን? ብለው ጠይቁኣቸው።አቡነ ያዕቆብም በልባችው ይመኙት የነበሩትን በግልጽ በጆሮቸው ሲሰሙ በደስታ ፈነደቁና "ኃላፊዎች ቢፈቅዱልኝ እኔ ዝግጁ ነኝ" ብለው መልስ ሰጧቸው።

ከዚህም በኋላ በደንቡ መሠረት ሂደቱ ከተሟላ በኋላ ሞንትዎ ሪ ከተባሉ ጓደኛቸው ጋር አብረው ከርኣሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጎርጎርዮስ 11ኛው ምርቃትና ቡራኬን ተቀብለው ግንቦት 24 ቀን 1839 ዓ.ም. እ.ኤ.አ ቺቪታ ቬኪያ ከተባለችው ሮም አጠገብ ከምትገኘው ወደብ ተነሥተው

Read more: የቅዱስ አቡነ ያቆዕብ ዩስጢኖስ ታሪክ

  • Written by Super User
  • Hits: 623

Subcategories

  • የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አዕማድ

    በዚህ ዓምድ ውስጥ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ጎላ ብሎ ሊታይ የሚገባው ሚና ያላቸውን ሰዎች ገድል እናካትታለን። እንደ አመቺነቱ ታሪኮቹን ለማሰባሰብ የምንሞክርበት ነውና አቀራረቡ የዘመናት ቅደም ተከተልን የተከተለ አይደለም ስለዚህም ከአንዱ ወደ ሌላው የሚሸጋገር ዓይነት ወጥ የሆነ አካሄድ ላይኖረው ይችላል።


     

በዚህ ጽሑፍ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ጽሑፋት

ተወራራሽ ርእሶች