እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

2 - የመጽሐፍ ቅዱስ ቅርጽ (አከፋፈል)

2 - የመጽሐፍ ቅዱስ ቅርጽ (አከፋፈል)

መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ መጽሐፍቶችን እንዳሰባሰብ አንድ ቤተ መጻሕፍት ነው። ስለዚህም በቀላሉ የተፈለገውን መጽሐፍ ለማግኘት አንድ ጥሩ ቤተ መጻሕፍት በሚገባ የተስተካከለና የተዋቀረ የመጻሕፍት አቀማመጥ ሊኖረው እንደሚገባ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲሁ ነው።


የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያና የመጨረሻ ዓረፍተ ነገሮች (ዘፍ.1:1… እና ራእይ 22:20-21) ከጊዜ መጀመሪያና መጨረሻ ጋር የተያያዘ አገላለጥ ስላላቸው በውስጡ የያዛቸው መጽሐፍቶች በዓመታት ቅደም ተከተል የተቀመጡ ናቸው ያስብል ይሆናል። ነገር ግን የመጽሐፍቱ አቀማመጥ እንደሚመስሉት በዘመናት ቅደም ተከተል ሳይሆን ይበልጥ ውስብስብና ትርጉም በሚሰጥ መልኩ የተቀመጡ ናቸው።


በመጀመሪያ የምናገኘው ዋነኛው የመጽሐፍ ቅዱስ አከፋፈል ብሉይ ኪዳንና አዲስ ኪዳን የሚለው ሁለት ክፍል ነው። የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ በፊት የተጻፉ መጻሕፍት ስብስብ ሲሆኑ፤ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ደግሞ ከኢየሱስ ልደት በኋላ የተጻፉ መጻሕፍት ስብስብ ናቸው።

ብሉይ (አሮጌ፣ የበፊት) እና አዲስ የሚሉት ሁለት ቅጽሎች ኪዳን የሚለውን ስም ስለሚገልጹ እዚህ ላይ መሠረታዊ ጥያቄ ሊሆን የሚችለው “ኪዳን” ማለት ምን ማለት ነው ሊሆን ይገባዋል። በጥንታዊው ዓለም ኪዳን ማለት ውል፣ ስምምነት፣ ቃል መገባባት…የሚያሰማ ሲሆን ተግባራዊነቱም በሁለት ወገኖች መካከል ቤተሰባዊ ትስስር ወይም ጥምረት ለመፍጠር የሚደረግ ወጋዊና ይፋ ውል ማለት ነው። በማደጎ መልክ ልጅ መውሰድ ወይም ጋብቻ የመተሳሰር ሂደት የዚህ ዓይነት ውል ዓይነተኛ ምሳሌ ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃቀም ብሉይና አዲስ ኪዳን ስንል እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያለውን የግንኙነት ደረጃ ያመለክታል።


በነዚህ ሁለት ዋነኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍፍል ውስጥ ሁሉም መጻሕፍት በይዘታቸው መሠረት በየጎራው ተለይተው እንደሚከተለው ይከፈላሉ።


የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ክፍፍል

ብሉይ ኪዳን አራት መሠረታዊ ክፍፍሎች አሉት፦ በብሉይ ኪዳን ውስጥ አራት ዓይነት ክፍሎች አሉ፦

  1. የሕግ መጻሕፍት ፦ እነዚህ መጻሕፍት የሌሎቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት መሠረት የሆኑት አምስቱ የሙሴ መጻሕፍት ናቸው። የእስራኤል ሕዝብ አጀማመር ታሪክንና የሕይወትና የአምልኮን መመሪያ የያዙ ናቸው።
  2. የታሪክ መጻሕፍት ፦ በነዚህ መጻሕፍት ውስጥ የእስራኤል ሕዝብ በተፋዪቱ ምድር ውስጥ ያሳለፉትን ታሪክ ይተርካሉ። በዚህም ውስጥ እንዴት የተስፋዪቱን ምድር እንደያዙ፣ ራሱን የቻለ መንግሥት መመሥረታቸው፣ ወደ ስደት በምርኮ መሄዳቸውና ስኬታማው የመቃብአውያን አብዮትን ያካትታሉ።
  3. የጥበብ መጻሕፍት ፦ ይኼኛው ጎራ ላይ የተካተቱት መጻሕፍት በሥነ ፍጥረት ላይ ልዩ እይታንና ጽብረቃን የሚያደርጉና በቤተሰባዊ ሕይወትና በአስተዳደራዊ ሂደት ሞራላዊ ማለትም ግብረ ገባዊ የአናኗር መመሪያዎችን፣ መልካም የሆኑ መስተጋብሮችንና ፈሪኀ እግዚአብሔርን የሚመለከቱ ጽሑፎችን ይዘዋል።
  4. የትንቢት መጻሕፍት ፦ በክፉዎች ላይ ፍርድን ለተጨቆኑት ደግሞ የተስፋ መጽናናትን የሚሰጥ የእግዚአብሔር ቃል ይገኝባቸዋል።

የአዲስ ኪዳን አራት መሠረታዊ ክፍፍሎች ፦

በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ከብሉይ ኪዳን ጋር ተመሳሳይ የሆነ የአራት አከፋፈል ሂደት እናገኛለን።

  1. ወንጌሎች (ሕግ) ፦ የተቀሩት የአዲስ ኪዳን ጽሑፋት መሠረት የሆኑት አራቱ ወንጌሎችን የያዘ ሲሆን ክርስቲያኖች ይኖሩበት ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ያመጣውን አዲስ ሕግ ይናገራሉ።
  2. የሐዋርያት ሥራ (ታሪክ) ፦ አዲስ መንግሥት የሆነችው የቤተ ክርስቲያንን መመሥረትና መስፋፋት ይዟል።
  3. መልእክቶች (ጥበብ) ፦ በክርስቲያናዊ ጥበብ ላይ የሚያስተነትኑንና ክርስቲያናዊ ሕይወትን እንዴት መኖር እንደሚገባ ተግባራው ምክሮችን የሚሰጡ ናቸው።
  4. መጽሐፈ ራእይ (ትንቢት) ፦ የመጨረሻው ፍርድ እንዴት በክፉዎች ላይ ፍርድን እና ለተጨቆኑት ደግሞ መጽናናትን እንደሚያመጣ ይገልጻል።

በሁለቱ ኪዳናት የምናገኛቸውን ከላይ የተመለከትናቸውን እነዚህን አራት ታላላቅ አከፋፈሎች ማስታወሱ ብቻ በራሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት ምን መሆኑን ለማወቅ ትልቅ ጠቀሜታ አለው። አንዴ ይህን ሰፊ አወቃቀር ማወቅ ስንጀምር እንዴት ባለ ፍጥነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምንፈልገውን ቶሎ እንደምናገኝ ያስገርመናል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት - ብሉይና አዲስ ኪዳናት 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት