4.1 - የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት

የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት

ኢየሱስ እና የእርሱ ሐዋርያት "መጽሐፍትን" ጠቀሱ ስንል ዛሬ እኛ ብሉይ ኪዳን ብለን የምንጠራውን፣ የአይሁዳውያንን መጽሐፍ ቅዱስ የገነባውን የተቀደሰ ጽሑፍ ስብስብ ማለታችን ነው፡፡ ነገር ግን የእሥራኤል ሕዝቦች የተቀደሰውን መጽሐፍ ካልተቀደሰው እንዴት ለይተው ሊወስኑት ቻሉ? በብሉይ ኪዳን ውስጥ መጽሐፍትን "ለይቶ መቀደስ" በተመለከተ አያሌ ምሥሌዎች እንደነበሩ በግልጽ ለማየት እንችላለን፤ እነዚህ ምልክቶች በአብዛኛው እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር አዲስ ቃልኪዳን የሚያጸናበትን ገጠመኝ የሚታከኩ ነበሩ፡፡

በኖህ አማካኝነት እግዚአብሔር ለሰው ዘር ሁሉ ይከተሉት ዘንድ ቀላልና ተራ የሆነ ሕግ ሠጣቸው፡፡ ሙሴም በተራው ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ሕግ በመጽሐፍ መልክ መዝግቦ በመያዙ የሕግ መጽሐፍትን "ቀኖና" ሊያበረክት ቻለ፡፡ /ዘጸ 24፡3-8/

መጽሐፈ ነገሥት ሁለተኛም ኢዮስያስ ለረዥም ዘመን ተትቶ እና ተረስቶ የነበረውን የሕጉን መጽሐፍ እንዳገኘ የተገድሶ መሪ አድርጎ ያቀርበዋል፤ እርሱም በሕዝቡ ፊት የሕጉን መጽሐፍ አነበበላቸው /2ነገ 23፡2/፡፡ በተመሣሣይ ከምርኮ ከተመለሱ በኋላ ካህኑ ዕዝራ በሕዝቡ ጉባኤ ፊት መጽሐፍን ከፍ ባለ ድምፅ በማንበብ ሕጉን በድጋሚ አስተዋውቋል /ነህ. 8፡3፣ 5-6/፡፡

በታሪካችን ሁሉ ውስጥ እሥራኤላውያን የልዱሳት ጽሑፎችን ሥብሥቦች ጠብቀው አቆይተዋል፡፡ ከክርስቶስ በፊት በነበሩት ሥስት ክፍለ ዘመናት አይሁዳውያን በግብፅ ሳሉ እነዚህን ጽሑፎች ወደ ግሪክ ቋንቋ ተርጉመው በሰባ ተርጓሚያን ስም ሰባወክልዔቱ የሚል ስያሜ ሰጥተው አዲስ እትም ሊያቀርቡ ችለዋል፡፡ ይህ ስያሜ አልፎ አልፎ LXX በሚለው የሮም ቁጥር በምህፃረ ቃል ይጠቀሳል፡፡ የዚህ ----- ይዘት በዓለም ዙርያ የግሪክ ቋንቋ ተናጋሪ በሆኑ አይሁዳውያን ዘንድ ተቀባይነት ያገኘውን አንድ ጥንታዊ ቀኖና ይዟል፡፡ በአዲስ ኪዳን ጸሑፍ ወቅት ሐዋርያት የቀድሞ የቤተ ክርስቲያን አባቶች እንዳደረጉት ይህንን ሰባወክልዔቱ ያጣቅሱ ነበር፡፡

ኢየሱስ በነበረበት ዘመን መጽሐፍ ቅዱሰ ውስጥ መካተት ያለባቸውን መጽሐፍ በተመለከተ እና የትኞቹ መጽሐፍት በሥርዓተ አምልኮ ውስጥ በቤተ መቅደስ ሊነበቡ እንደሚገባቸው የጋራ መግባባት ተደርሶ ነበር፡፡ ከእነዚህ መካከል በጣም በቅርብ የሆኑት ጥቂት መጽሐፍት ግን አሁንም አከራካሪ ናቸው፡፡ ለምሣሌ እንደ መጽሐፈ መቃብያን እና የተወሰኑት የጥበብ መጽሐፍ ክፍሎች በአይሁዳውያን ዘንድ ተቀባይነት በማግኘታቸው በሰባ ወክልዔቱ ውስጥ ሊጠቃለሉ ችለዋል፡፡ ነገር ግን ዘግይተው የተነሱ የአይሁድ መምህራን መልሰው መጽሐፎቹን ስላልተቀበሏቸው ዛሬ እነዚህ መጽሐፍት በአይሁድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና የመጽሐፍት ዝርዝር ውስጥ አይገኙም፡፡

ካቶሊካውያን ጥንታዊውን እምነት በመጠበቅ እነዚህን መጽሐፍት እንደ ብሉይ ኪዳን ሰባት ቀሪ መጽሐፍት አድርገው ይቀበሏቸዋል፡፡ አብዛኞቹ ኘሮቴስታንቶች የአይሁዳውያንን ተግባር ተከትለው መጽሐፍቱን አይቀበሏቸውም፡፡ እነዚህ አከራካሪ መጽሐፍት ዲዮትሮኖሚካል ይባላሉ፤ የግሪኩ ቃል ፍቺ "ዳግማዊ ቀኖና" ማለት ነው፡፡ ለካቶሊካውያን እነዚህ መጽሐፍት ከ"ቀዳማዊ ቀኖና" መጽሐፍ በምንም አያንሱም፡፡ ነገር ግን በአብዛኞቹ የኘሮቴስታንት ትርጉሞች ውስጥ እነዚህ መጽሐፍት አይገኙም፡፡ ስለዚህ ለአንድ ካቶሊክ የኘሮቴስታንት መጽሐፍ ቅዱስ ያልተሟላ ነው ማለት ነው፡፡