እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

5. የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍት

5. የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍት

ሀ - ብሉይ ኪዳን

የሕግ መጽሐፍት

የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያዎቹ አምስት መጽሐፍት በተለምዶ ለሙሴ የተሰጡ ናቸው፡፡ ስለ ዓለም ፍጥረት አጀማመር፣ ስለ እስራኤል ሕዝብ፣ እሥራኤል ለእግዚአብሔር እንደተለየ ሕዝብ ሊኖርባቸው ስለሚገቡ የተቀደሱ ትዕዛዛት ያቀርባል፡፡

ዘፍጥረት፡- በግሪክ “መጀመሪያ ወይም ጅማሮ” ማለት ነው፡፡ የሁሉንም ነገር አጀማመር ታሪክ ያቀርብልናል፡፡ በፍጥረት ታሪክ ጀምሮ የእስራኤል ሕዝብ አባቶች ወደ ግብፅ ሲወሰዱ ያልቃል፡፡፡ በዚህ መካከል የሰውን ልጅ ኃጢአት፣ የጥፋት ውኃ፣ የባቢሎን ግንብ፣ አብረሐም፣ ይስሃቅ፣ ያዕቆብ እና ዮሴፍ እንደሁም ሌሎች ብዙ ታሪኮችን እናገኛለን፡፡

ዘጸዓት፡- “መውጣት” ማለት ሲሆን የእሥራኤል ሕዝብ ከግብፅ ባርነት እንዴት እንደወጣ ብሎም በሲና ተራራ እንዴት ሕጉን እንደተቀበሉ ይተርክልናል፡፡ መሪያቸው የነበረው ሙሴ ሲሆን የእርሱም ታሪክ በመጽሐፉ የመጀመርያ ክፍሎች ይዳስሳል፡፡ የአይሁድ ፋሲካን ጨምሮ አሥሩ የግብፅ መቅሰፍቶች ታሪክ የሚገኘው በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ሲሆን የአሥርቱ ትዕዛዛትም መገኛ ነው፡፡

ዘሌዋውያን፡- ሁለቱን የእሥራኤል ቤት የሕዝብ ቆጠራ ይዟል፡፡ ይሕ የእንግሊዘኛው ፍቺ ሲሆን የግሪኩ ፍቺ ደግሞ “በምድረ በዳ ውስጥ” ማለት ነው፡፡ የተቀረውን የመጽሐፉን ክፍል ለመግለጽ ይህ አመቺ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከነዓንን አሳልፎ በእጃቸው እንደሚሰጣቸው ባለማመናቸው የእስራኤል ሕዝብ ለአርባ ዓመታት እንደ ቅጣት በበረሃ ውስጥ ያደረጉትን ጉዞ ይዳስሳል፡፡

ዘዳግም፡- በግሪኩ ፍቺ “ሁለተኛ ሕግ” ማለት ነው፡፡ እሥራኤላውያን የሞዓባውያንን ጣኦቶች በማምለክ በድጋሚ በእግዚአብሔር ላይ በማመፃቸው የተቀደሰ ሕዝብ ለመሆን ያለባቸውን ጥሪ እና ኃላፊነት ትተው ነበር፡፡ በዘዳግም ውስጥ የተሰጠው ሕግ ለሕዝቡ “የደነደነ ልብ” ምሕረት የሚያደርግ ነበር፡፡ ለምሳሌ ፍቺ /ዘዳ 24፡1 ተመልከት እና ኢየሱስ ያንን ሕግ በማቴዎስ 19፡3-9 እንዴት እንዳብራራው አነፃጽር/፡፡

የታሪክ መጽሐፍት

እነዚህ የእሥራኤልን ሕዝብ ታሪክ ተስፋይቱ ምድር ከተሰጠችበት እሥራኤል አንድ እስከሆነችበት ድረስ፣ እንዲሁም እሥራኤል እስከተከፋፈለችበት እና ሕዝቡ በምርኮ እስከተያዘበት፣ በመጨረሻም የእሥራኤል ሕዝብ የወደመችውን ኢየሩሣሌምን እንደገና ለመገንባት እስከተመለሰበት ያለውን የሕዝቡን ታሪክ የሚያትቱ መጽሐፍት ናቸው፡፡

ኢያሱ፡- የሙሴ ተተኪ በነበረው በኢያሱ ዘመን እሥራኤል የከነዓንን በርካታ ግዛቶች እንዴት ልትቆጣጠር እንደቻለች ያስረዳል፡፡ ድሉ እሥራኤል ለእግዚአብሔር መመርያዎች ታማኝ በሆነባቸው ጊዜያቶች ላይ የሚገኝ ነበር፡፡ አለመታዘዝ ምርኮን ያስከተላል፡፡ የኢያሪኮ ውድቀትን የሚያትተው ታዋቂው ታሪክ በመጽሐፍ ኢያሱ ውስጥ ነው፡፡

መሣፍንት፡- በእሥራኤል የነበረውን ያለመረጋጋት ረጅም ዘመን ይዳስሳል፤ ፍልስጤማውያን እና በእሥራኤል ሳይማረኩ የቀሩት ከነዓናውያን በቅጡ ባልተደራጁት የእሥራኤላውያን ግዛቶች ውስጥ ሰርገው በመግባት አደጋ የሚጥሉበት ዘመን ነበር፡፡ የመጽሐፉ ፍሰት ክህደትን፣ ጭቆናን እና መዳንን የሚያሳይ ነው፡፡ እሥራኤል እውነተኛውን አምላክ ከማምለክ ይቦዝናል፣ እግዚአብሔር እሥራኤልን በጠላቶቿ እጅ አሳልፎ ይሠጣታል፣ እሥራኤል ተጸጽታ ወደ እግዚአብሔር ረድኤት ሰትጮህ ከምርኮ የሚያድናትን ይልክላታል፡፡ በመጽሐፈ መሣፍንት አያሌ ታሪኮች ይገኛሉ፤ ለመጥቀሱ ያህል፡- የጌዲዮን አዋጅ፣ ሳምሶን እና ደሊላ፣ የዮፍታሔ ሴት ልጅ ወዘተ ይገኛሉ፡፡

ሩት፡- በዘመነ መሣፍንት የተከናወነ አስደሳች የፍቅር ታሪክ ነው፡፡ ባልዋን በሞት ያጣችው ሞዓባዊቷ ሩት ምራቷን ተከትላ ወደ እሥራኤል ትመለሳለች፡- “ሩትም። ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፥ በምታድሪበትም አድራለሁና እንድተውሽ ከአንቺም ዘንድ እንድመለስ አታስቸግሪኝ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል” ሩት1፡16፡፡  በዚህ ጊዜ በሀብቱ ወደር የማይገኝለትን እና በመልካም ነገር የተሸለመውን ንጉሥ ቦኤዝን በማግባቷ የንጉሥ ዳዊት ቅድመ አያት በመሆን በኢየሱስ ክርስቶስ የዘር ሐረግ ውስጥ አንዷ ለመሆን በቅታለች፡፡

ሳሙኤል፡- በሁለት ክፍል የተከፈለው መጽሐፍ በእሥራኤል ስለተጀመረው ግዛት ይናገራል፡፡ ሕዝቡ ንጉሥ በፈለገበት ዘመን ሳኦልን የእሥራኤል ንጉሥ አድርጐ ይቀባው ዘንድ እግዚአብሔር ሳሙኤልን ይልካል፡፡ ነገር ግን ሳኦል ባለመታዘዙ ምክኒያት ንግሥናውን ስላቆሸሸ በእርሱ ምትክ ዳዊትን ይቀባው ዘንድ ሳሙኤል ይላካል፡፡ አንደኛ ሳሙኤል በአብዛኛው የሚጠነጥነው እያደር አመጽ እና ትዕቢቱ እየጐላ በመጣው ሳኦል እና አጋጣሚውን ቢያገኝም እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን አላነሳም ባለው በዳዊት መካከል በነበረው ትግል ዙርያ ነው፡፡ የሁለተኛ ሳሙኤል አብዛኛው ክፍል ደግሞ የንጉሥ ዳዊትን ረዥም የንግሥና ዘመን ይዳስሳል፡፡ የዳዊት እና የጐልያድ ታሪክ በ1ኛ ሳሙ. 17 እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ማለትም የዳዊት ግዛት ማለቂያ የሌለው መሆኑን የገለጠለት በ2ኛ ሳሙ. 7 ላይ ይገኛል፡፡

ነገስት፡- ይህ በሁለት ክፍሎች የተዋቀረው መጽሐፍ የሚያነሳው በንጉሥ ዳዊት የመጨረሻ ዘመናት ሁለተኛ ሳሙኤል መተረክ ካቆመበት ሀሳብ ነው፡፡ የመጀመርያ ነገሠት የሚዳስሰው የንጉሥ ሰሎሞንን የንግሥና ዘመን እና የእርሱም ክህደት ከሞት በኋላ በእሥራኤል ቤት ያስከተለውን ክፍፍል ነው፡፡ ከአሥራ ሁለቱ ግዛቶች አሥሩ አመጽ ቀስቅሰው የእሥራኤል ሰሜናዊ ግዛት ሲመሰርቱ የይሁዳ እና የቢንያም ነገድ የዳዊትን ቤት ጠብቀው ቆይተዋል፡፡ የአመጽ እና የእድሳት ዑደት በእሥራኤልና በይሁዳ ግዛቶች መፈራረስ አብቅቷል፡፡ የሰሜን ነገድ ሳይመለሱ በየቦታው ሲበታተኑ ሁለት የደቡብ ነገዶች ደግሞ በምርኮ ወደ ባቢሎን ተወስደዋል፡፡

ዜና መዋዕል፡- ይህ በሁለት ክፍሎች የተዋቀረው መጽሐፍ እንደ ሳሙኤል እና ነገሥት አይነት ይዘት ያለውን ተመሳሳይ ታሪክ ይዳስሳል፡፡ በዜና መዋዕል ውስጥ አጽኖት የተሰጠው ይበልጥ ሥነ-መለኮታዊ ለሆነው ነገር ሲሆን ደራሲው ንጉሥ ዳዊትን የወደፊቱ እውነተኛ ንጉሥ መልክ አድርጐ ለማሳየት የተለየ ጥረት ያደርጋል፡፡

ዕዝራ፡- አንዳንድ የይሁዳ ሕዝቦች ከአሥርት ዓመታት የምርኮ ዘመን በኋላ እንዴት ወደራሳቸውው ምድር እንደተመለሱ ይተርካል፡፡ በካህኑ በዕዝራ መሪነት የኢየሩሳሌምን ቤተ መቅደስ በድጋሚ ለመገንባት እና ለሙሴ ሕግ በመታዘዝ ሕይወታቸውን ለመኖር እንደሞከሩ ያሳየናል፡፡

ነህምያ፡- የንጉሥ የግብዥ አሳላፊ የነበረው ነህምያ የኢየሩሳሌምን ቅጽሮች ዳግም ግንባታ ለመምራት እንዴት ወደ ኢየሩሳሌም እንደተመለሰ ይናገራል፡፡ አብዛኛው ክፍል ከራሱ ከነህምያ ትዝታዎች የተፃፈ ነው፡፡ ከግዞት በኋላ በኢየሩሳሌም የታየ የተለየ የመጀመርያ መደብ ተራኪ ይዘት ወይም ስልት የተከተለ አፃፃፍ ነው፡፡

ጦቢት፡- ይህ መጽሐፍ ቤተሰቦቹ በቀና መንገድ ለመምራት ስለሚፈልግ እና በምርኮ በተወሰደው የእስራኤል ሕዝብ ውስጥ ይኖር  ስለነበረው በጥረቱም ላይ ባልታወቀ ድብቅ መልአክ እርዳታ የተደረገለት ሰው ታሪክ ነው፡፡ /ጦቢት ከቀኖና መጽሐፍ አንድ ነው/

ዮዲት፡- ይህ ሕዝቦቿን በአሶራውያን ከመሸነፍ ስላዳነቻቸው አንዲት ጀግና እሥራኤላዊት ሴት የሚተርክ መጽሐፍ ነው፡፡ / ዮዲት ከቀኖና መጽሐፍት አንድ ነው/

አስቴር፡- በምርኮ ወደ ፐርሺያ የተወሰደች አንዲት ሴት የፐርሺያ ንግሥት ሆኖ ሕዝቧን እስራኤልን ከታወጀበት የጅምላ ጭፍጨፋ የታደገች እሥራኤላዊት ሴት ታሪክ ነው፡፡ /የአስቴር የተወሰነው ክፍል ከቀኖና መጽሐፍት የሚመደብ ሲሆን መጽሐፉ ከኘሮቴስታንት እና ከአዲሱ የአይሁድ መጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ በካቶሊክ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ረዘም ይላል፡፡

1ኛ መቃብያን፡- የአይሁድ ሕዝብ በጭቆና ቀንበር ሥር በሚገዙት አምባገነን ነገሥታት አማካኝነት የአልቦ እግዚአብሔርነትን እምነት እንደተቀበሉ በተገደዱ ጊዜ ስላነሱት የተቃውሞ አመጽ እና ከብዙ ፈተናዎች በኋላ ስለደረሱበት ስኬት ይተርካል /1ኛ መቃቢያን ከቀኖና መጽሐፍት አንዱ ነው/፡፡

2ኛ መቃብያን፡- ይህ መጽሐፍ በአንደኛ መቃብያን ውስጥ የሚገኙትን ተመሳሳይ ክስተቶች ይተርካል፤ ትኩረቱም በደም ምስክርነት ወይም በሰማዕትነት ላይ ነው፡፡ /ሁለተኛ መቃብያን ከቀኖና መጽሐፍት አንዱ ነው፡፡ አንዳንድ መጽሐፍት ቅዱሳት እዚህ እንደሆነው በታሪክ መጽሐፍ መዝጊያ ላይ ከመስቀመጥ ይልቅ የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው መጽሐፍ አድርገው ያስቀምጡታል፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት - ብሉይና አዲስ ኪዳናት 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት