Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የክርስቶስ ቅዱስ መስቀል መክበር - መስከረም 4

የክርስቶስ ቅዱስ መስቀል መክበር

Exaltaion of Cross 3መስከረም 4 - በመጀመሪያዎቹ የ4ኛው ክፍለ ዘመናት ላይ ቅድስት እሌኒ ማለትም የሮማው ንጉሥ ቁስጥንጢኖስ እናት ወደ ኢየሩሳሌም የክርስቶስን መስቀል ፍለጋ ሔዳ ነበር። እዚያም ስትደርስ በሁለተኛው ክፍለ ዘመን የተሰራ የጣዖት መቅደስ በክርስቶስ የመቃብር ቦታ ላይ ተገንብቶ አግኝታ አፈረሰችው። ልጇም ንጉሥ ቁስጥንጢኖስ የቅዱስ መስቀል ቤተ መቅደስ በዚያው ቦታ ላይ ገነባ ። አዲሱ ቤተ መቅደስ ለመገንባት በሚቆፈርበት ጊዜ በቦታው ሦስት መስቀሎች ተገኝተዋል። በአፈ ታሪክ መሠረት የክርስቶስ ትክክለኛ መስቀል የትኛው እንደሆነ ለማረጋገጥ በሞት ጣር ላይ ያለች አንዲት ሴትን አምጥተው መስቀሎን ሲያስነኳት ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ሲነካት እንደዳነች ይነገራል ።

           ከዚህ በኋላ ነው ግማደ መስቀሉ የአክብሮት ምልክት የሆነው። በዓይን እማኞች መሠረት በ4ኛ ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ይህ ግማደ መስቅሉ በስቅለተ አርብ ቀን፣ ከብር የተሰራ በላዩ ጲላጦስ ጽሕፈት ያለበት ማስቀመጫ ውስጥ ተደርጎ በጠረጴዛ ላይ ይቀመጥ ነበር። አማኞች በሙሉ አንድ በአንድ አጎንብሰው በግንባራቸው ነክተው፣ በዓይናቸው አይተው ከዚያም በመሳም (በመሳለም) ያልፉት ነበር ።

           እስካዛሬ ድረስ የምስራቅ አብያተ ክርስትያናት ካቶሊኮችና ኦርቶዶክሶች በመስከረም ወር ይህን የመስቀል በአል ያከብራሉ። በምዕራቡ ዓለም ይህ በዓል በ7ኛ ክፍለ ዘመን መከበር የጀመረው ንጉሥ ሕርቃል በ615 ዓ.ም. መስቀሉን ለ15 ዓመት ወስደውት ከነበሩት ፐርሺያኖች ካስመለሰ በኋላ ነበር። በታሪክ እንደሚነገረው ንጉሡ መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ኢየሩሳሌም ሊመልሰው ሞክሮ ሆኖም ግን ሊንቀሳቅስ አልቻለም። ንጉሡ ንጉሣዊ ልብሱን ካወለቀና ባዶ እግሩን ከሆነ በኋላ መንፈሳዊ ጉዞውን ለማድረግ ቻለ፣ ወደ ኢየሩሳሌም መጓዙ ተሳካለት።

ትርጉም፦ ዮሴፍ ወልደዮሐንስ

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።