የአዛኝቱ እመቤታችን ማርያም ታሪክ - መስከረም 5

የአዛኝቱ እመቤታችን ማርያም ታሪክ

Our Lady of Sorrow articleመስከረም 5 - የአዛኝቱ እናት ክብረ በዓል ለረጅም ጊዜ በዓመት ሁለት ጊዜ በ15ኛውና 17ኛው ክፍለ ዘመን በአለም አቀፋዊት ቤተ ክርስቲያን ከደብረ ዘይት በዓል በፊት ያለው አርብ ቀንና በመስከረም ወራት ይከበር ነበር ።

           ይህ የአዛኝቱ ማርያም ክብረ በዓል መሠረት የሆኑት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሉቃስ 2፡35 ስምዖን የማርያም ልብ በሰይፍ ይወጋል የሚለውና ዮሐ 19፡26-27 ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ ለቅድስት ማርያምና ለቅ. ዮሐንስ የተናገረው “እነሆ ልጅሽ” እና “እነሆ እናትህ” የሚሉት ናቸው።     

           ማርያም ያለፍርሃት መስቀል ሥር ሆና ልጇን በሃዘኔታ ትመለከተው ነበር ሌሎቹ ሐዋርያቶች ሰሸሹ። የኢየሱስን ቁስሎች ኀዘን በተሞላበት ዓይኖቿ ተመለከተች። ይሁንና በነዚህ ቁስሎች ለዓለም ደህንነት እንደሆነም አይታልች። ብዙ የቀደምት ዓመታት የቤ/ክ ጸሐፊዎች፣ ይህ ሰይፍ የተባለውን የማርያም ኀዘንና ስቃይ የሚያመለክት ነው ብለው ተርጉመውታል ።

ቅዱስ በርናርዶስ የእመቤታችንን ኀዘን ጥልቀት ሲገልጽ “ሌሎች ሰማዕታት በሥጋቸው ሲሰቃዩ የእርሷ ግን እስከ ነፍሷ ይዘልቃል፤ እሷ ለኢየሱስ ያላት ፍቅር ከማንም በላይ የላቀ፣ የእናትነት ስለሆነ በልጇ ስቃይና ሞት ከማንም የላቀ ኀዘን ተሰምቷታል” ይላል። ቅዱስ አምብሮስዮስ ቅድስት ማርያምን በልጇ መስቀል ሥር ሆና የኀዘን ምልክት መሆኗ ብቻ ሳይሆን እንደጠንካራ የጽናት ተምሳሌትም ሆና ይመለከት ነበር ።

ትርጉም፦ ዮሴፍ ወልደዮሐንስ