Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ቅዱስ ቀርኔሊዮስ - መስከረም 6

ቅዱስ ቀርኔሊዮስ

St.Cornelius 1መስከረም 6 - በ250 ዓ.ም. ንጉሥ ዲሲዮስ ባደረገው ሃይማኖታዊ ጭፍጨፋና ስደት በጊዜው የነበረው ር.ሊ.ጳጳሳት ቅዱስ ፋቢያን ሰማእት ሆኖ መሞቱ ይታወቃል። ከዚህ በኋላ ለ14 ወራት ያህል ቤተ ክርስትያኗ ር.ሊ.ጳጳሳት አልነበራትምና በዚህ ጊዜ በካህናት ስብስብ ትመራ ነበር። ቅዱስ ቆጵርያኖስ የጓደኛውን ቀርኔሊዮስን ር.ሊ. ጳጳስ አድርጎ ሲሾመው "በእግዚአብሔርና በክርስቶስ ፍርድ እንዲሁም በታላላቅ ካህናትና በሕዝብ ምርጫ ለር.ሊ.ጳጳስነት ተመርጧል " ብሎም ጻፈ።

           ቅ. ቀርኔሊዮስ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት በር.ሊ.ጳጳስነት በሚያገለግልበት ጊዜ ካጋጠመው ችግሮች አንደኛው ምስጢረ ንስሐን የሚመለከት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በክርስትያናዊ ስደት ጊዜ ሃይማኖታቸውን የከዱ ክርስትያኖች እንዴት ሆኖ እንደገና ወደ ቤተ ክርስቲያን የመቀበልን ሂደት በሚመለከት ነበር። ቀዳማዊ የሰሜን አፍሪካው ቆጵርያኖስ፣ አቤቱታውን ለር.ሊ. ጳጳሳቱ ካቀረበ በኋላ እነዚህ የሚመለሱ የቤተ ክርስቲያን አባላትነ በሚመለከት የጳጳስ ውሳኔ ብቻ መሆን አለበት በማለት አቋሙን ገልጿል ።

           ቀርኔሊዮስ ግን በሮም ተቃራኒ አመለካከቶች አጋጠመው። ር.ሊ.ጳ. ሆኖ ከተመረጠ በኋላ ኖቪሺያን የተባለ ካህን ራሱን ጳጳስ አድርጎ በመሾሙ፣ የር.ሊ.ጳ. ቀርኔሊዮስ ተፎካካሪ በመሆን ከመጀመሪያዎቹ ጸረ ጳጳስ ሊባል ችሏል ።

           ኖቪሺያ ቤተ ክርስቲያኗ ከሃዲዎችን ብቻ ሳይሆን ነፍሰ ገዳዮች፣ ዘማውያን፣ ድጋሚ ያገቡትንም የማስታረቅ ኃይል የላትም ብሎ ነበር የካደው። ቀርኔሊዮስ ግን አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አብያተ ክርስትያናትን ድጋፍ አግኝቶ ኖቪሺያን አውግዞታል።  ከውግዘት በኋላ ይህ የመናፍቃን (ከትክክለኛው የእምነት ትምህርት የሳቱ) አስተሳስብ ለጥቂት ዓመታት ጸንቶ ቆይቶ ነበር። በ251 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ቀርኔሊዮስ ሲኖድ አካሂዶ እነዚህ እንደገና የተመለሱትን አማኞች ከንስሐ በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲገቡ አዘዘ ።

           ከር.ሊ.ጳ. ቀርኔሊዮስ በተገኘው ሰነድ መሰረት የቤተክርስቲያኗ አደረጃጀት በዚያን ጊዜ የሮም ቤተ ክርስቲያን በመካከለኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ 46 ካህናት፣ 7 ዲያቆናትና፣ 7 ንዑሰ ዲያቆናት እንደነበራት ያመለክታል ። 50,000 ክርስትያን አማኞችም እንደነበራት ተገምቷል። ቀርኔሊዮስ በስደት ባላበት ጊዜ በደረሰበት ጉስቁልና በዛሬዋ ቺቪታ ቬኪያ በሚባል ቦታ በተወለደባት በሮም ከተማ በ2ኛ ክፍለ ዘመን የተመሠረተው የባሕር ወደብ አረፈ።

ትርጉም፦ ዮሴፍ ወልደዮሐንስ

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።