Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ቅዱስ ሮበርት ቤላርማይን - መስከረም 7

ቅዱስ ሮበርት ቤላርማይን

Robert Bellarmineመስከረም 7 - ሮበርት ቤላርማይን በ1570 ዓ.ም. ሢመተ ክህነትን በተቀበለበት ጊዜ የቤተ ክርስቲያን ታሪክና አበው በሚያሳዝን ሁኔታዎች ላይ ነበሩ። ተስፋ ያለው ምሁር፣ በተስካኒ የጣሊያን ክፍለ ግዛት የተወለደው ሮበርት፣ ከወጣትነቱ ኃይልና ፍላጎቱን በነዚህ ሁለት ርእሶችና እንዲሁም በቅዱስ መጽሐፍ ላይ በማተኮር የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሥርዓት ባለው ሁኔታ ከፕሮቴስታንት ተሃድሶች ጥቃት ለመቋቋም አግዟል። ሮበርት በሎቬን ከኢየሱሳውያን ማህበር (Jesuits) የመጀመሪያው መምህር ሆኗል።

           ከሥራዎቹ አንድ በጣም የታወቀው ባለ ሦስት መድብል መጽሐፍ "በክርስትና እምነት ላይ የተነሡ ውዝግቦችን መሞገት" (Disputations on the Controversies of the Christian Faith) የሚል ነው። ከዚህ መጽሐፍ አንዱ ክፍል ትኩረት ማድረግ የሚገባው "የር.ሊ.ጳ. ምድራዊ/ጊዜያዊ ኃይልና የምእመናን ሚና" የሚለው ላይ ነው። ቤላርማይን የእንግሊዝና የፈረንሣይ ነገሥታት የሚመኙትን የንጉሥ መለኮታዊ መብት የማያዋጣና የማይሳካ ንድፈ ሐሰብ መሆኑን በማሳየቱ ከንጉሣውያኑ ዘንድ በጥብቅ ቁጣን ቀስቅሶ ነበር። እንዱሁም የር.ሊ.ጳ. በጊዜያዊ/ምድራዊ ጉዳዮች በሚመለከት ንድፈ ሐሳብ በማዳበሩ ከር.ሊ.ጳ. ሲክስቶስ 5ኛ ቁጣን ተቀብሏል። ይሁንና ይህ ንድፈ ሐሳብ ር.ሊ.ጳ.ን ከስኮትላንዱ ፈላስፋ በርክሌይ ተቋውሞ ለመመከት ነበር።

           ቤላርማይን ባለው እውቀት ተወዳዳሪ ስላልተገኘለት፣ በር.ሊ.ጳ ቀሌሜንጦስ 8ኛው ካርዲናል እንዲሆን ተሾመ። በቫቲካን ውስጥ የመኖሪያ ቤት ቢሰጠውም የቆጣቢነት ፀባዩን አልተወም። የቤት ወጪውንም በመቀነስ ድሃዎች መግዛት የሚችሉትን ምግብ አይነት ብቻ ይመገብ ነበር። ከውትድርና ያመለጠ ወታደር በማስለቀቅም ቤዛነትን አድርጓል። እንዲሁም በክፍሉ የነበሩትም ልዩ ልዩ የግርግዳ ጌጦች በመሽጥ "ግርግዳዎች ጉንፋን አይዛቸውም/አይበርዳቸውም" እያለ ድሆችን ያለብስ ነበር።

           በቤላርማይን ሕይወት ከፍተኛ ውዝግብ ያጋጠመው በ1616 ዓም የሚያደንቀውን ጓደኛው ጋሊልዮን ሀሳብ መገሰጽ ነበር። ቅድስት ወንበርን በመወከልም ጋሊልዮ ምድራችንና የተቀሩት ዓለማት በፀሐይ ዙሪያ ይዞራሉ የሚለውን የኮፐርኒከስ ንድፈ ሐሳብ  (Heliocentric theory) ከመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከት ተቃራኒ ሆኖ በማቅረቡ ነው። የቤላርማይን ይህን ሀሳብ መመጎት ቅዱሳንም እንደማንም ሰው እንደሚሳሳቱ ያሳየናል።

           ሮበርት ቤላርማይን እ.አ.አ መስከረም 17. 1621 አርፏል። የሱም የቅድስና ሂደት 1627 ተጀምሮ በጻፋቸው ጽሕፋት  ምክንያት በጊዜው በነበረው ፖለቲካዊ ሁኔታ እስከ 1930 ድረስ ተራዝሟል። በ1930 ር.ሊ.ጳ ፓየስ 11ኛ የቅዱስና ማዕረግ ያወጁለት ሲሆን፣ በቀጣዩም ዓመት የቤተ ክርስቲያን አበው ከሚባሉት አንዱ ሆኖ ተሰይሟል ።

ትርጉም፦ ዮሴፍ ወልደዮሐንስ

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።