ቅዱስ ጄናሮ - መስከረም 9

ቅዱስ ጄናሮ

st januarius witness of the most precious blood of christመስከረም 9 - ስለቅዱስ ጄናሮ የሕይወት ታሪክ ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም። በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው እሱ በጣልያን ቤንቬነቶ የተወለደ ሲሆን፤ በንጉሥ ዳዩክሊሺያ የሃይማኖት ስደት ዘመን በ305 ዓም ጣልያን ናፖሊ ውስጥ ሰማዕት እንድሆነ ይታመናል።  ቅ. ጄናሮ ክርስቲያኖች ሲሰደዱ በእሱ ዘንድ ይሸሽግ ነበር፤ እንዲሁም እየሄደ ባሉበት ይጎበኝ ነበር። በዚህ ሂደት ውስጥ ሲጎበኝ በመገኘቱ፤ እሱና  ተከታዮቹ በፖዙሊዮ የትርኢት ማሳያ ቦታ (አምፊቲያትር) ውስጥ ለድብ ተወርውረው አውሬዎቹ ግን ሊያጠቋቸውም ሆነ ሊበሏቸው አልቻሉም። ከዚያም አንገታቸው እንዲቆረጥ ተደርጎ የጃኖሪያስ ደም እንደ ቅዱሱ ትሩፋት ሰዎች ይጸልዩና የደም ምስክርነቱን እንዲማልዱበት ወደ ናፖሊ ከተማ ተወሰዷል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮም በተለያዩ አጋጣሚዎች በተለይም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለጉብኝት ሲሄዱ እንደ አዲስ ወደ ፈሳሽነት የመለወጥ ተአምር እንደሚከሰትም ይነገራል፤ ለምሳሌም ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 9ኛው በ1848 ዓ.ም. እ.ኤ.አ እንዲሁም ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው በ2007 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. በናፖሊ የእሱ ደም በሚገኝበት ካቴድራል ጉብኝትን ሲያደርጉ ደሙ ወደ ፈሳሽነት ተለውጦ ነበር።

ትርጉም፦ ዮሴፍ ወልደዮሐንስ