Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ቅዱሳን እንድሪያስ ኪም ታኤጎን ፣ ጳውሎስ ቾንግ ሐሳንግና ተከታዮቻቸው - መስከረም 10

ቅዱሳን እንድሪያስ ኪም ታኤጎን ፣ ጳውሎስ ቾንግ ሐሳንግና ተከታዮቻቸው 

        Kimመስከረም 10 - እንድሪያስ ኪም የመጀመሪያው የኮሪያው ካህን የተወለደው ክርስትናን ከተቀበሉት ወላጆቹ ነበር ። በ15 ዓመቱ ከተጠመቀ በኋላ 1,300 ማይልስ ተጉዞ ማካኦ ቻይና ዘርአ ክህነት (ሴሚናሪ) ገባ። ከስድስት ዓመታት በኋላ በማቹሪያ በኩል አድርጎ ወደ አገሩ ተመልሷል። በተመሳሳይ ዓመት ቢጫ ወንዝ የሚባለውን አቋርጦ ሻንጋይ በገባበት አመት ክህነቱን ተቀበለ። አገሩም ከተመለሰ በኋላ ሚሲዮናውያን የማሰማራት ሐላፊነት ተሰጦት፣ እነዚህ ሚሲዮናውያን ወንዝን ተከትለው በድንበር ጠባቂዎች እንዳይያዙ ያደርግ ነበር። ሶል ከተማ አጠገብ በሚገኘው የሀን ወንዝ ተይዞ ታስሮና ተሰቃይቶ በመጨረሻም አንገቱን ተሰይፎ ስለ እምነቱ ተሰውቷል።

           የእንድሪያስ አባት ኢግኔሺየስ ኪም በሃይማኖታዊ ስደት በ1839 ሰማዕት የሆነ ነው። በ1925 ብፁዕ ተባለ ። እንዲሁም ጳውሎስ ቾንግ ሐሳንግ ተራ ሐዋርያዊና ያገባ ሰው በ45 ዓመቱ በ1839 ተሰውቷል ።

           በ1839 ሰማዕት ከሆኑት ውስጥ አንዱ ኮሉምባ ኪም የተባለችው የ26 ዓመቷ ሴት ናት። ታስራ እስር ቤት ከገባች በኋላ በጋሉ መሣሪያዎች ትበሳና በሚያቃጥል ከሰልም ያቅጥሏት ነበር። እሷና እህቷ አግነስ ልብሳቸውን ተገፈው ለሁለት ቀናት ከወንጀለኞች ቆይተዋል ። ግን ማንም ፆታዊ ጥቃት አልደረሰባቸውም። ኮሉምባ በደረሰባት ኢ ሰብአዊ ውርደት አቤቱታዋን ካቀረበች በኋላ ሴቶች እንዲይ አይነት ሁኔታ እንዳይደርስባቸው ተደርጓል። ይሁንና በመጨረሻም ሁለቱም እህታማማቾች አንገታቸው በመቆረት ተገድለዋል ። ጴጥሮስ ሪዮ የተባላ የ13 ዓመት ወጣት ሥጋውን በሚያሳዝን ሁኔታ ተቦጫጭቆ ሳለ አንዳንድ ቁራጩን በዳኛ ላይ መወርወር ይችል ነበር ። እሱም አንገቱን አንቀውት ተገድሏል። ፕሮስታስ ቾንግ የተባለው የ41 ዓመቱ መኳንንት ባሰቃዮት ጊዜ ሐይማኖቱን በመካድ ተለቀቀ። በኋላም ተመልሶ አማኝ መሆኑን ከተናዘዘ በኋላ ብዙ ተሰቃይቶ ሞቷል።

           ክርስትና ወደ ኮርያ የገባው በጃፓን 1592 ወረራ ነበር። በዚህ ጊዜ አንዳንድ ኮሪያኖች በጃፓን ክርስትያን ወታደሮች ተጠምቀው ነበር ይባላል ። ወንጌል መስበክ ከባድ ነበር። ምክንያቱም ኮርያ (ለቻይና ቤጅንግ አመታዊ ግብር ከመክፈል በስተቀር) ከውጩ አለም ጋር ግንኙነትን እምቢ ስላለች ነው። ከእነዚህ ሁኔታዎች አንዱ በ1777 አካባቢ በቻይና ውስጥ የሚገኝ አንድ ኢየሱሳዊ (Jesuit) የጻፈው ፅሕፈት የተማሩ ክርስትያን ኮሪያኖች ወደ ጥናት መርቶአቸዋል። የቤት ውስጥ መሰብሰብ ቤ/ክ ተጀመረ። ከጥቂት አመታት በኋላ አንድ ቻይናዊ ካህን በምስጢር ወደ ኮርያ ገብቶ ወደ 4,000 ካቶሊክ አማኞችን አግኝቷል። ከእነሱ አንዳቸውም ካህን በጭራሽ አይተው አያውቁም ነበር ። ከ7 አመት በኋላ 10,000 ካቶሊኮች ነበሩ። የሃይማኖት ነጻነትም በኮሪያ በ1883 መጣ ።

           ከእንድሪያስን ጳውሎስ ሌላ ቅዱስ ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛው ኮሪያን በ1984 በጎበኙበት ጊዜ 98 ኮሪያኖችን የቅድስናን ማእረግ ሰጥተዋል። ከእነዚህም መካከል ጳጳሳትና ካህናት ሆኖም አብዛኛዎቹ ኮሪያኖች ተራ አማኝ ግለሰቦች 47 ሴቶችና 45 ወንዶች ነበሩ። በተጨማሪም 3 ፈረንሣይ ሚስዮናውያን በ1839ና 1867 ሰማዕት ከሆኑት ይገኙባቸዋል።

ትርጉም፦ ዮሴፍ ወልደዮሐንስ

          

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።