Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የጾመ ፵ ዕለታዊ አስተንትኖ

በጾመ ፵ ወቅት ለአሰተንትኖ የሚያግዙ ጽሑፎች የሚቀርብበት ክፍል

ስቅለት!

ስቅለት!

እነሆ ሰውየው!

የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች መቀደዱ የስቅለተ ዓርብ አንዱ ቀለም ነው፤ ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ ይህ ክስተት የአሮጌዎቹ ሥርዐቶች መሻር ምልክት መሆኑን ያስረዳል፤ ማቴዎስ በበኩሉ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ የዘመናት መቁጠርያ ቀመሮችን ከዋክብት የያዘ በመሆኑ የቀደመው ዘመን፣ የቀደመው ዓለም፣ ዓመተ ፍዳ መሻሩን የሚያሳይ ምልክት እንደሆነ ያስነብባል፤ ሦስቱም ወንጌላት…

Read more: ስቅለት!

Write comment (0 Comments)

ሰሙነ ሕማማት

ሰሙነ ሕማማት

ማክሰኞ

ፈጣሪ ቃል! ሕያው እግዚአብሔር በታሪካችን ማዕከል የማንነታችን የልብ ምት ሆኖ ኃይሉን ባልተለመደ መልኩ በኃይል አልባነት በመግለጥ ወደ ራሱ ይስበን ዘንድ  በኢየሩሳሌም መካከል ይመላለሳል። ይህ ወሰን የሌለው ፍቅር እና በማንም ኃጢአት የማይዝል ምሕረት የክብር ተስፋ ወዳለው፣ ከፍጥረት ሁሉ ጋር፣ ሁሉን ወደሚያቅፍ ትንሳኤያዊ ነገ እንጓዝ ዘንድ ይጋብዘናል። ከዚህ ከማያልቀው መለኮታዊ…

Read more: ሰሙነ ሕማማት

Write comment (0 Comments)

የዐቢይ ጾም 35ኛ ቀን

የዐቢይ ጾም 35ኛ ቀን

ይቅር እንደምንል

ይቅርታ በጥልቅ ስብራት መካከል የሚያብብ የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጥ ነው። ጌታ “አባታችን ሆይ” የሚለውን ጸሎት ለደቀ መዛሙርቱ ሲያስተምር “እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በልልን” እያለ የእኛን እና የእግዚአብሔርን ይቅርታ ትይዩ መስመር ላይ ያስቀምጠዋል። በመሰረቱ ይህንን ጸሎት በልማድ፣ በቃል ስለምናውቀው እና ስለምንጸልየው እንጂ ቆም ብለን…

Read more: የዐቢይ ጾም 35ኛ ቀን

Write comment (0 Comments)

የዐቢይ ጾም 31ኛ ቀን

የዐቢይ ጾም 31ኛ ቀን

ለክርስቶስ ጥሪ ምላሽ መስጠት

ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ዋጋ ሊከፍል ይችላል? የሚለው የጌታ ጥያቄ ቆም ብለን እንድናስብ ግድ ይለናል። ይህ ጥያቄ ስለ ሕይወታችን ዕጣ ፈንታ፣ ስለ ኑሯችን ትርጉም እና ስለ መንገዳችን ዓላማ የሚጠይቀን ጠንካራ ድምጽ ነው። ነፍሳችን በሰማይም ይሁን በምድር በምንም ሊተካ የማይችል የእግዚአብሔር ሥጦታ…

Read more: የዐቢይ ጾም 31ኛ ቀን

Write comment (0 Comments)

ሰሙነ ሕማማት

ሰሙነ ሕማማት

ጸሎተ ሐሙስ

“ልባችን ይቃጠል አልነበረምን?” የሚለው በሉቃስ ወንጌል የምናነበው የሁለቱ የኤማሁስ መንገደኞች ጥያቄ የእያንዳንዱ ክርስትያን ጥያቄ ነው። ከጌታ ጋር የተገናኘ ክርስትያን ሁሉ የሚያስታውሰው ነገር ይህ ልቡ በውስጡ እንግዳ በሆነ መልኩ የመንቀሳቀሱን እውነታ ነው። ነገር ግን ይህንን ታሪክ በቃል ከማወቃችን የተነሳ በዚህ ጥያቄ ውስጥ ያለውን ጥልቅ ምሥጢር ሳናስተውለው እንቀራለን። በመጀመርያ የሁለቱ…

Read more: ሰሙነ ሕማማት

Write comment (1 Comment)

ሰሙነ ሕማማት

ሰሙነ ሕማማት

ሰኞ

ሆሳዕና ጌታ በምድር ላይ የቀሩት ስድስት ቀናት መጀመርያ ነው። ጊዜው ለቤተ መቅደስ መሥዋዕት የሚቀርብበት በዓል ሰሞን ነው። ሰዎች በታላቅ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም የሚገቡበት እና የመኸር ምሥጋና የሚያቀርቡበት የምሥጋና በዓል ሳምንት ነው። ከዚህ ጎን ለጎን ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት የማስነሳቱ ተዓምር ዜና በኢየሩሳሌም ሁሉ ተስፋፍቶ ነበር። ወንጌል እንደሚመሰክረው ብዙዎች ከሞት የተነሳውን…

Read more: ሰሙነ ሕማማት

Write comment (0 Comments)

የዐቢይ ጾም 33ኛ ቀን

የዐቢይ ጾም 33ኛ ቀን

በጊዜ - መዳን

በኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም ሞት እና ትንሳኤ መዳናችን ሰርክ አዲስ ኅያው የሆነ፣ ሁለንተናችንን ዘልቆ የሚያረሰርስ፣ ከእምነት በሚሆን የጸጋ ሥጦታ የሚገለጥ እውነታ ነው። መዳን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ነው! መዳን አሁን ክርስቶስ በእኔ ይኖራል እንጂ ከእንግዲህ ወዲያ እኔ አልኖርም፤ አሁን በሥጋ የምኖረው በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን…

Read more: የዐቢይ ጾም 33ኛ ቀን

Write comment (0 Comments)

ምክር

ሰሙነ ሕማማት

ረቡዕ

"የምክር መንፈስ" ኢሳያስ ከሚዘረዝራቸው የመንፈስ ቅዱስ መገለጦች አንዱ "ምክር" ነው። ምክር ነፍስን የሚመልስ፣ የልብን ድንግልና የሚጠብቅ የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ነው። ምክር በነፍስ ውስጥ ሕያው የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ጉልበት ነው። ስለዚህ ይህ መንፈስ በልቦና ማስተዋል እና በሕሊና እውነተኛነት በነገር ሁሉ ውስጥ ይመክራል፣ ይገስጻል፣ ያቀናል፣ ያስጨክናል። ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር መክፈቻ ስለለተባረከ ሰው…

Read more: ምክር

Write comment (0 Comments)

ዐቢይ ጾም 39ኛ ቀን 

ዐቢይ ጾም 39ኛ ቀን 

ኃጢአት፣ ንስሐ፣ ተጋድሎ (ክፍል 1) 

ዛሬ የምንኖርበት ዓለም ኃጢአት ለሚባለው ነገር ጆሮ የለውም፤ የሕይወት ዑደት እና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሁሉ ኃጢአት የሚባል ነገር አያውቅም፤ ሁሉም ነገር የግል ጉዳይ እና የምርጫ ጉዳይ ነው። ጊዜው ኃጢአት የሚባል ጽንሰ ሐሳብ ምን እንደሆነ ለመግለጽ ቋንቋ ያጣ፣ ኃጢአት የሚወገድበት ስፍራ በመካከሉ…

Read more: ዐቢይ ጾም 39ኛ ቀን 

Write comment (0 Comments)

የዐቢይ ጾም 32ኛ ቀን

የዐቢይ ጾም 32ኛ ቀን

ሔሴድ

የደጉ ሳምራዊ ምሳሌ እግዚአብሔር የልቡን እውነተኛ መልክ የገለጠበት፣ ምሕረት ሥጋ ለብሶ በሰው ልጆች መካከል የተመላለሰበት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትረካ ሁሉ ማሰርያ ውል ነው።  ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በሰራ አካላቱ የሚናገረው ይህ የእግዚአብሔር ምሕረት እንዴት ያለ ምሕረት ነው? መዝሙረኛው ዳዊት እንደዚያ የሚቀኝለት ይህ የእግዚአብሔር ምሕረት ምን አይነት ምሕረት…

Read more: የዐቢይ ጾም 32ኛ ቀን

Write comment (0 Comments)

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።