፬ - “የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን”
- Category: በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ ጸሎት ሰባት ልመናዎች
- Published: Thursday, 13 October 2011 19:12
- Written by Super User
- Hits: 4643
- 13 Oct
፬ - “የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን”
“ስጠን”፡- ሁሉንም ነገር ፍለጋ አባታቸውን የሚጠሥቁ ልጆች እምነት ውብ ነው፡፡ “እርሱ በክፉዎችና በበጐዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና፡፡” ማቴ 5፡45 ለሕያዋን ሁሉ “ምግባቸውን በየጊዜው” ይሰጣቸዋል፡፡ ኢየሱስ ይህንን ጸሎት ለእኛ የሚያስተምርበት ምክንያት ጸሎቱ አባታችንን ከማናቸውም በጐ ነገሮች እጅግ የላቀ መልካም እንደሆነ በመግለጽ ስለሚያከብረው ነው፡፡
“ስጠን” ቃል ኪዳንንም ይገልጻል፡፡ እኛ የእርሱን፤ እርሱም ለእኛ ሲል የእኛ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ “ለእኛ” የሚለው ቃል እርሱ የሰዎች ሁሉ አባት እንደሆነ ስለሚያስገነዝበን በመከራና በስቃይ ላይ ከሚገኙ ሰዎች ጋር ሕብረታችንን ለመግለጽ ስለእነርሱ አምላክን እንለምናለን፡፡
“እንጀራችንን”፡- ሕይወት የሚሰጠን አባት፣ ለሕይወት የሚያስፈልገንን ሁሉ ይልቁንም ቁሳዊና መንፈሳዊ የሆኑ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ቡራኬንም ጭምር ይሰጠናል እንጂ ከቶ ሊነሳን አይችልም፡፡ ኢየሱስ በተራራው ላይ ስብከት ከአባታችን መለኮታዊ ጥበቃ ጋር ስለሚተባበረው የልጅነት አመኔታ አበክሮ ተናግሮአል፡፡ ኢየሱስ ወደ ሥራ ፈትነት አይገፋፋንም፣ ነገር ግን ዕረፍት ከሚሱን ማናቸውም ጭንቀትና ትካዜ እንድንላቀቅ ይሻል፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ታዛዥነት ይህን የመሰለ ነው፡-
እግዚአብሔር የእርሱን መንግሥትና ጽድቅ ለሚሹ ሰዎች ሌላውን ሁሉ በተጨማሪ እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶአል፡፡ ነገር ግን ሁሉም ነገር በእርግጥ የእግዚአብሔር እንደመሆኑ መጠን እግዚአብሔርን ከማግኙቱ በፊት ሌላ ነገር የሚፈልግ ካልሆነ በስተቀር እግዚአብሔርን የእርሱ ያደረገ ሰው ምንም የሚጐድለት ነገር አይኖርም፡፡
ነገር ግን ምግብ በማጣት የሚራቡ ሰዎች መኖር ይህን ልመና ጠለቅ ያለ ትርጉም ይሰጠዋል፡፡ በዓለም ላይ የሚታየው ረሃብ ክርስቲያኖች በግል ጠባያቸውና ከሰብአዊው ቤተሰብ ጋር ባላቸው ትብብር ስለወንድሞቻቸው ያላቸውን ኃላፊነት ተግባር ላይ ያውሉ ዘንድ በእውነት ከልብ ለሚጸልዩ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ይህ የጌታ ጸሎት ልመና ከድኻው ከአልአዛርና ከመጨረሻው ፍርድ ምሳሌዎች ተለይቶ ሊታይ አይችልም፡፡
ለሊጥ እርሾ እንደሚያስፈልገው ሁሉ የእግዚአብሔር መንግሥት አዲስነት በክርስቶስ መንፈስ አማካይነት ምድርን “ኩፍ ማድረግ”፣ አለበት፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለው በግላዊ በማኀበራዊ በኢኮኖሚያዊና በዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶች ፍትሕ የተመሠረተ እንደሆነ ነው፡፡ በእውነት ፍትሕን የሚሹ ሰዎች በሌሉበት ፍትሐዊ መዋቅሮች ሊኖሩ የማይችሉ መሆናቸውም ከቶ መረሳት የለበትም፡፡
“የእኛ” እንጀራ “ለብዙኃን” የሚበቃ “አንድ” ቁራሽ እንጀራ ነው፡፡ በብፅዕናዎች ውስጥ የተነገረው “ድኽነት” የመካፈል ምግባር ነው፡፡ ይህ መንፈሳዊ ኃይል ቁሳዊና መንፈሳዊ ሀብቶቻችን በኃይል ሳይሆን በፍቅር ተገፋፍተን ከወንድሞቻችን ጋር እንድንከፋፈል ሀብት የሌሎችን ችግር ለማቃለል ይረዳ ዘንድ ነው፡፡
“ሥሩ፤ ጸልዩም፡፡” “ሁሉ ነገር በእግዚአብሔር እንደሚሆን ጸለዩ፤ ሁሉም ነገር በእናንተ እንደሚወሰን ሥሩ” ሥራችንን በሠራን ጊዜ እንኳ የምናገኘው ምግብ ከእግዚአብሔር የተሰጠን ስጦታ ነው፡፡ ከማዕድ በፊትና በኋላ፡- በክርስቲያናዊ ቤተሰቦች እንደተለመደው ሁሉ ከምሥጋና ጋር ይህንኑ ይሰጠን ዘንድ መለመን መልካም ነው፡፡
ይህ ልመና ከሚያስከትለው ኃላፊነት ጋር፣ ሰዎች እርሱን ባለማግኘታቸው የሚጠፋበትን ሌላውን ረሃብ ይመለከታል፡- “ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ፣ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት አይኖርም፡፡”ዘዳ 8፡31፤ ማቴ 4፡4 ይህም ማለት ሰው የሚኖረው በሚናገረው ቃልና እስትንፋሱ የሆነው መንፈስ ነው፡፡ ክርስቲያኖች “ለድኾች ለማሳወቅ ማንኛውንም ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡” በምድር ላይ ረሃብ፡፡ “እንጀራን መራብና ውሃን መጠማት አይደለም፤ የጌታን ቃል መስማት እንጂ፡፡”ዓሞ 8፡11 ስለዚህ የዚህ የአራተኛው ልመና ልዩ ክርስቲያናዊ ትርጉም የሚመለከት የሕይወት እንጀራን፣ በእምነት የምንቀበለው ቃል እግዚአብሔርንና፣ በቅዱስ ቁርባን የምንቀበለውን የክርስቶስን ሥጋና ደም ነው፡፡
“ዛሬ” የሚለውን ቃል እኛ ከቶ ልንፈጥረው የማንችለው ጌታ ያስተማረን የአመኔታ መግለጫ ነው፡፡ “ዛሬ” የሚለው ቃል ከሁሉ በላይ ቃሉንና የልጁን ሥጋ የሚጠቅስ እንደመሆኑ መጠን የሚያመለክተን የእኛን የሟቾቹን ጊዜ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርንም “ዛሬ” ጭምር ነው፡፡
በእያንዳንዱ ቀን እንጀራውን ብትቀበል፣ እያንዳንዱ ቀን ለአንተ ዛሬ ነው፡፡ ክርስቶስ ዛሬ የአንተ ከሆነ፣ እርሱ በየቀኑ ለአንተ ይነሣል፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? “አንተ ልጄ ነህ፣ እኔ ዛሬ ወለድሁህ፡፡” ስለዚህ “ዛሬ ክርስቶስ የሚነሳበት ነው፡፡” መዝ 2፡7
“በእየዕለቱ” የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጠ በየትም ቦታ አይገኝም፡፡ በዓለማዊ ትርጉሙ ቃሉ “ያላንዳች ገደብ” በእምነት የሚያጸናን የ “ዛሬ” ትምህርታዊ ድግግሞሽ ነው፡፡ ቃሉን በሚገልጸው ነገር አንጻር ካየነው ለሕይወት አስፈላጊ የሆነን ነገር ያመለክታል፡፡ ይበልጥ ሰፋ አድርጐ ሲታይ ደግሞ ለመኖር የሚበቃ ማናቸውንም መልካም ነገር ያመለክታል ማለት ነው፡፡ ቃል በቃል ሲወሰድ /እጅጉን አስፈላጊ/ የሚል ሲሆን ያ እርሱ ሕይወት የማይገኝበትን የሕይወት እንጀራን የክርስቶስን ሥጋና ደም እንዲሁም የ “ዘላለማዊነትን ፈውስ” ደግሞ በቀጥታ ያመለክታል፡፡ በመጨረሻም ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ሰማያዊ ትርጉሙ ግለጽ ነው፡- “ዛሬ” የጌታ ቀን፣ የመንግሥቱ ግብዣ፣ የቅዱስ ቁርባኑ የታየውና የመጭው መንግሥትም ቅምሻ ነው፡፡ ስለዚህም በየዕየቱ መስዋዕተ ቅዳሴን ማቅረብ ተገቢ ነው፡፡
ቅዱስ ቁርባን እለታዊ እንጀራችን ነው፡፡ የዚህ መለኮታዊ ምግብ ኃይል የአንድነት ማሠሪያ ያደርገዋል፤ ወደ ሥጋው በመሰባሰባችን የእርሱም ብልቶች በመሆናችን የምንቀበለውን እነሆን ዘንድ ውጤቱን የምንገነዘበው በአንድነቱ ነው፡፡…. ይህ በየቀኑ በቤተ ክርስቲያን የምትሰሙት ንባብና የምታዜሙት፣ የምትሰሙትም መዝሙር የዕለት እንጀራችን ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ለምናደርገው የእምነት ጉዞ የሚያስፈልጉ ምግቦች ናቸው፡፡
በሰማይ ያለው አባታችን፣ የመንግሥተ ሰማያት ልጆች እንደመሆናችን መጠን የሰማይ እንጀራን ለማግኘት እንድንለምነው ያበረታታናል፡፡ ክርስቶስ ራሱ በድንግል ውስጥ የተዘራ፣ በሥጋ ያደገ፣ በሕማማት የቦካ፣ በመቃብር እቶን /ምድጃ/ የተጋገረ፣ በቤተ ክርስቲያናት የተቀመጠ፣ በመሰዊያ ላይ የቀረበ ለምዕመናንም በየዕለቱ ሰማያዊ መብልን የሚያስገኝ ነው፡፡
/የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ከቁጥር 2828-2837/