ሰባቱ ልመናዎች
- Category: በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ ጸሎት ሰባት ልመናዎች
- Published: Thursday, 13 October 2011 19:06
- Written by Super User
- Hits: 5026
- 13 Oct
ሰባቱ ልመናዎች
/የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ከቁጥር 28ዐ3-28ዐ6/
እግዚአብሔርን ለማምለክ ለመውደድና ለመባረክ ራሳችንን ከእርሱ ፊት ካቀረብን በኋላ ልጅነትን ያስገኘልን መንፈስ ሰባት ልመናዎችና ሰባት ቡራኬዎችን በልባችን ውስጥ ያጭራል፡፡ ከሰባቱ መካከል በይበልጥ ነገረ መለኮታዊ የሆኑት የመጀመሪያዎቹ ልመናዎች ወደ አብ ክብር ይስበናል፤ የተቀሩት አራቱ ደግሞ ወደ እርሱ የሚወስዱ መንገዶች እንደመሆናቸው ጭንቀታችን ለጸጋው ያቀርባሉ፡፡ ‹‹በፏፏቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራታለች›› መዝ. 42፡7
የመጀመሪያዎቹ ልመናዎች “ስምህ፣ መንግስትህ፣ ፈቃድህ” ስለ እርሱ ወደ እርሱ ይመሩናል፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ ስለምንወደው ነገር ማሰብ የፍቅር ባሕሪ ነው፡፡ በሦስቱም ልመናዎች እኛን የሚመለከት አንዳችም ነገር አንጠቅስም፡፡ ተወዳጁ ልጅ ስለ አባቱ ክብር የለው የሚያንገበግብ ፍላጐት እንዲያም ሲል ጭንቀት ይመስጠናል፡፡ “ስምህ ይቀደስ፣ መንግስትህ ትምጣ … ፍቃድህ … ይሁን” እነዚህ ሦስቱ ልመናዎች በክርስቶስ የማዳን መስዋዕት ምላሽ አግኝተዋል፤ ሆኖም ከዚያ ወዲህ እግዚአብሔር ገና ሁሉ በሁሉ አልሆነምንና በተስፋ ወደ መጨረሻው ፍጻሜያቸው እያመሩ ነው፡፡
ሁለተኛዎቹ የልመና ዝርዝሮች እንደ አንዳንዶቹ ቁርባናዊ የምልጃ ጸሎቶች በተመሳሳይ እንቅስቃሴ ይገለፃሉ፡፡ የምሕረቶች አባት ዓይኖች አሽቆልቁለው ወደ እኛ እንዲያተኩሩ ለእርሱ የምናቀርበው የተስፋዎቻችን መባእ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ “ስጠን … ይቅርበለን … ወደ … አታግባን … አድነን…” የሚሉት ልመናዎች ከእኛ ወደ ላይ ይሄዳሉ፤ የእኛንም ከዚህ ጊዜ አንስቶ በአሁኑ ዓለማችን የሚመለከቱን ይሆናሉ፡፡ አራተኛውና አምስተኛው ልመናዎች ምግብ ማግኘታችንና ከኃጢአት መፈወሳችን … በጠቅላላ ሕይወታችንን የሚመለከቱ ናቸው፡፡ የመጨረሻዎቹ ሁለት ልመናዎች ለሕይወት ድል የምናደርገውን ፍልሚያ የጸሎት ውጊያ የሚመለከቱ ናቸው፡፡
በመጀመሪያዎቹ ሦስት ልመናዎች አማካይነት በእምነት እንጐለብታለን፤ በተስፋ እንሞላለን፣ በፍቅርም እንቃጠላለን፡፡ ፍጡራንና ኃጢአተኞች በመሆናችን ከዓለምና ከታሪክ ጋር ለተሳሰረውና ለወሰን የለሹ የእግዚአብሔር ፍቅር ለምናቀርበው በዚያ “ለእኛ” መለመን አለብን፤ ምክንያቱም አባታችን የማዳን እቅዱን ለእኛና ለመላው ዓለም ወደ ፍጻሜ የሚያደርሰው በክርስቶስ ስምና በመንፈሱ ኃይል ነውና፡፡