የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት
- Category: ፲ቱ ትእዛዛት
- Published: Saturday, 25 June 2011 08:53
- Written by Super User
- Hits: 2660
- 25 Jun
የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት
በዘመናዊ ኅብረተሰብ ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በመረጃ ሥርጭት፣ በባሕላዊ እድገትና ቀረጻ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ይህ ሚናቸውም በቴክኖሎጂ እድገት ሳቢያ፣ በሚሰራጨው ዜና ስፋትና ብዛት እንዲሁም በሕዝቡ አስተያየት ላይ ባለው ተጽእኖ የመገናኛ ብዙኃን ሚና እያደገ በመሄድ ላይ ነው፡፡
በመገናኛ ብዙኃን የሚተላለፍ መረጃ ለጋራ ጥቅም የሚውል ነው፡፡ ሕብረተሰብ በሐቅ፣ በነጻነት፣ በፍትሕና በትብብር ላይ የተመሠረተ መረጃን ማግኘት መብት አለው፡፡
“የዚህ መብት በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋል የሚተላለፈው መረጃ ይዘት እውነተኛነት እንዲኖረው ፍትሕንና ፍቅር በደነገጉአቸው ገደቦች መሠረትም የተሟላ እንዲሆን ይጠይቃል፡፡ ይህም ማለት ከዜና አሰባሰብና ሥርጭር አኳያ ምግባራዊው ሕግና ሕጋዊ መብቶች እንዲሁም ሰአብዊ ክብር መጠበቅ አለባቸው ማለት ነው፡፡”
“የሕብረተሰቡ አባሎች በሙሉ በዚህ ዘርፍ የፍትሕንና የፍቅርን ጥያቄዎች መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ጤናማ ሕዝባዊ አስተሳሰብ በመፍጠርና በማስረጽም ረገድ የበኩላቸውን ማበርከት አለባቸው፡፡” ሕብረት የእውነተኛና የትክክለኛ መረጃ ልውውጥ እንዲሁም እውቀትንና ለሌሎች የሚኖርን አክብሮትን የሚያዳብሩ ሃሳቦች በነጻ የሚንሸራሸሩበት የመገናኛ ብዙኃን ውጤት ነው፡፡
የመገናኛ አውታሮች በተለይም መገናኛ ብዙኃን ከተጠቃሚዎች መካከል አንዳንዶቹን ንቁ ተጠቃሚዎች ከማድረግ ይልቅ የሚሰሙትንና ወይም የሚያዩትን በዝምታ እንዲቀበሉ ተጽእኖ ሊያሳድርባቸው ይችላል፡፡ ሰዎች በዜና ማሰራጫ አጠቃቀም ቁጥብነትንና ሥነ ሥርዓትን ልምድ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ጤናማ ያልሆኑ ተጽእኖችን ይበልጥ በቀላሉ ለመቋቋም በሳልና ትክክለኛ ሕሊና እንደኖራቸው ይሻሉ፡፡
ጋዜጠኞች ከሥራቸው ባሕርይ በሚመነጭ ዜና ሲያሰራጩ እውነትን የማገልገልና ፍቅርን ያለማጉደል ግዴታ አለባቸው፡፡ ጋዜጠኞች የጉዳዮችን ውስጠ ነገር ሲያብራሩ አንደሁም ግለሰቦችን በተመለከተ ትችታዊ አስተያየቶችን ሲያቀርቡ በሁለቱም አቅጣጫ በኩል ጥንቃቄ ለማድረግ ከፍ ያለ ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡ የሌላውን ስም ከማያጐድፍ ማንኛውም ተግባር ለመራቅ ከፍ ያለ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ለጋራ ጥምም ሲባል ለመንግሥት ባለሥልጣናት በዚህ ልዩ ኃላፊነቶች አለባቸው፡፡ እውነተኛና ትክከለኛ የመረጃ ስርጭት ነጻነትን መጠበቅና ማስጠበቅ… የዚህ አካላት ፈንታ ነው፡፡ ሕጐችን በማውጣትና ገቢራዊ መሆናቸውን በመከታተል፣ በመገናኛ ብዙሃን ሕገወጥ አጠቃቀም፣ “ሕዝባዊ ሥነ ምግባርን ማኅበራዊ እድገት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንዳይወድቁ” ባለሥልጣናት ማረጋገጥ ይጠበቅባዋቸል፡፡ ግለሰቦች ክብራቸውንና የግል ሕይወታቸውን ለማስጠበቅ ያሏቸውን መበቶች የሚጥሱትን ሁሉ መቅጣት አለባቸው፡፡ የጋራ ጥቅምን በተመለከተ ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃዎች ማቅረብ ወይም ለሕዝቡ ትክክለኛ ጥያቄዎች ምለሽ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡ በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ሕዝባዊ አስተያየትን ለማዛባት አሳሳች መረጃ መጠቀምን በምንም መልኩ መደገፍ አይቻልም፡፡የሕዝባዊ ሥልጣን ጣልቃ መግባት የግለሰቦችንና የቡድኖችን ነጻነት የሚጐዳ መሆን የለበትም፡፡
እውነትን በዘዴ ወደ ሐሰት የሚለውጡትን፣ መገናኛ ብዙኃን አማካኝነት በአስተሳሰብ ላይ ፖለቲካዊ ቁጥጥር የሚደረጉትን፣ በችሎት ላይ ተከሳሾችንና ምስክሮችን የሚያሳስቱትን “የአስተሳሰብ ወንጀል” ነው ብለው የሚገምቱትን ማንኛውንም ነገር በማነቅና በማፈን አምባ ገነንነታቸውን ለማስጠበቀ እንደሚችሉ የሚያስቡ ፈላጭ ቆራጭ መንግሥታት የሚፈጽሙትን ሰቆቃ ሥነ-ምግባራዊ ፍርድ ሊኰንነው ይገባል፡፡