የልብ ንጽሕና
- Category: ፲ቱ ትእዛዛት
- Published: Monday, 25 July 2011 07:28
- Written by Super User
- Hits: 3195
- 25 Jul
የልብ ንጽሕና
ልብ የሥነ ምግባራዊ ስብዕና ማደሪያ ነው፡፡ “ከልብ ክፉ ሐሳብ፣ መግደል፣ ምንዝርነት፣ ዝሙት … ይወጣልና፡፡” ማቴ. 15፡19 ከሥጋዊ ፍላጐት ጋር የሚደረግ ትግል ልብን ማንጻትንና እራስን መቆጣጠርን ይጠይቃል፤
ቅኖችና የዋሆች ሁሉ፤ የሰውን ሕይወት የሚያጠፋውን ክፋት እንደማያውቁ ጨቅላ ሕፃናት ትሆናላችሁ፡፡
ስድስተኛ ብፅዕና፤ ልበ-ንፁሖች ብፁዓን ናቸው፡፡ እግዚአብሔርን ያዩታልና፡፡ “ልበ-ንጹሖች” የሚለው ቃል የሚወክለው አዕምሮዋቸውንና ፈቃዳቸውን በተለይ በሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ማለትም በፍቅር በንጽሐ ድንግልና ወይም በወሲባዊ ታማኝነት፣ ለእውነት በሚኖር ፍቅርና በቀና እምነት ከእግዚአብሔር ቅድስና ያስተሳሰሩ ሰዎችን ነው፡፡ በልብ፣ በስጋና በእምነት ንጽሕና መካከል ዝምድና አለ፡፡
ምእመናን አንቀጸ-ሃይማኖትን ማመን ይገባቸዋል፡፡ ይህም የሚሆነው “በማናቸውም ለእግዚአብሔር ይታዘዙ ዘንድ፣ በመታዘዛቸውም በደህና ይኖሩ ዘንድ፣ በደህና በመኖራቸው ልባቸውን ያነፁ ዘንድና በንጹሕ ልብም ከሚያምኑበትን እንዲገነዘቡ ነው፡፡
“ልበ-ንጽሖች” የእግዚአብሔርን ፊት ለፊት እንደሚያዩ እርሱንም እንደሚመስሉ የተስፋ ቃል ተሰጥቶአቸዋል፡፡ የልብ ንጽሕና እግዚአብሔርን ለማየት የሚያስፈልግ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ አሁንም እንኳን ቢሆን የልብ ንጽሕናን እግዚአብሔር በሚፈቅደው መንገድ ሌሎችን እንደ “ባልንጀሮቻችን” አድርገን ለመቀበል ያስችለናል፡፡ የልብ ንጽሕና የሰውን አካል የእኛንም ሆነ የባልንጀሮቻችንን፣ እንደ መንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ፣ እንደ መለኮታዊ ውበት መግለጫ አድርገን ለመገንዘብ ያስችለናል፡፡