እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የሌሎችን ሃብቶች ማክበር

የሌሎችን ሃብቶች ማክበር

ሰባተኛው ትእዛዝ ስርቆትን፤ ማለትም ያለ ባለቤቱ ፍቃድ ንብረቱን አላግባብ መውሰድና ማስቀረትን ይከለክላል፡፡ ስምምነት ይኖራል ተብሎ ከታሰበ ወይም እምቢታ ከቶውንም የማይጠበቅና ሀብት የሁሉም ከመሆኑ አንፃር ግምት ውስጥ የማይገባ ከሆነ ድርጊቱ ከስርቆት አይቆጠርም፡፡ ግልጽና አጣዳፊ ሁኔታ ሊያጋጥም አስቸኳይና አሰፈላጊ የሆኑ ነገሮችን /ምግብ፣ መጠለያ፣ ልብስ/ ማቅረብ ባስፈለገ ጊዜ የሌሎችን ንብረት መውሰድና መጠቀም የግድ ሲሆን የሚሆነውም ይህ ነው፡፡

የመንግስት ሕግ ድንጋጌዎችን የማይጥስ ቢሆንም እንኳ፣ የሌሎችን ንብረት ያለአግባብ መውሰድና ማስቀረት፣ እንዲሁም በውሸት የተሰጡ ወይም የጠፉ እቃዎችን ሆን ብሎ ማሰቀረት፣ በንግድ ሥራ ማጭበርበር፣ ተመጣጣኝ ያልሆነ ምንዳዕ መክፈል፣ የሌላውን አላዋቂነት ወይም ችግር ተንተርሶ ዋጋን ማናር፣ ሰባተኛውን ትእዛዝ ይፃረራል፡፡

ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ከሥነ ምግባር አኳያ ሲታዩ ሕገ-ወጥ ናቸው፡፡ ሌሎችን በመጉዳት የራስን ጥቅም ለማካበት ሲባል በሰው ሰራሽ ዘዴዎች ዋጋን ለማምታታት የሚደረግ ጥረት፣ ሕግ የሚፈቅደው  መሠረት ውሳኔዎችን የሚያስተላልፍ ሰዎችን በማግባባት ምግባረ ብልሹነትን ማስፋፋት የድርጅቶችን የጋራ ንብረት በግላዊ ጉዳይ ማዋልን መጠቀም፤ ጥራት የሌለው ሥራ፣ ግብርን አለመክፈል፣ ሕጋዊ ባልሆኑ ቼኮችና ፋክቱሮች መጠቀም፤ ወጪን ከመጠን በላይ ማብዛትና ማባከን ሆን ብሎ የግል ወይም የመንግሥትን ንብረት ማበላሸት የሥነ ምግባር ሕግን የሚቃረን ስለሆነ ካሳን ያስከፍላል፡፡

የተገባው ቃል ከሥነ ምግባር አኳያ ትክክለኛ እስከሆነ ድረስ ቃል ኪዳኖች መጠበቅና ውሎችን በጥብቅ ማክበር አለባቸው፡፡ አብዛኛውን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሕይወት በሁለት ሕጋዊ ሰውነት ባላቸው ወገኖች መካከል የሚደረጉ ውሎችን /የግዥንና የሽያጭ የንግድ ውሎች፣ የኪራይ ወይም የሰራተኛ ውሎች/ የማክበር ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ውሎች ሁሉ በሥምምነት የጸደቁና በቅን ልቦና የሚፈጸሙ መሆን አለባቸው፡፡

ውሎች መብቶቻቸው በሚገባ በሚከበሩበት ሁኔታ በሰዎች መካከል የሚደረግ ልውውጥን በሚቆጣጠር የውል ሕግ ይመራሉ፡፡ የውል ሥርዓተ ሕግ በጣም የጠበቀ ያስገዳጅነት ኃይል አለው፤ ይህ ማለት የባለቤትነት መብቶች፣ የእዳ ክፍያዎችና በሙሉ ፈቃደኝነት ቃል የተገቡ የውል ግዴታዎች መጠበቃቸውን ይጠይቃል፡፡ በዚህ ረገድ ከውል ሥርዓተ ሕግ ውጭ ሌላ ዓይነት የፍትሕ አስተዳደር ሊኖር አይችልም፡፡

ማንም ቢሆን የውል ሥርዓተ-ሕግ ዜጋው ለማሕበረሰብ በትክክለኛ መንገድ ሊያደርገው የሚገባው ነገር ከሚደነግገውና ማሕበረሰቡ ከፍላጐታቸውና ከአስተዋጾኦዋቸው አንጻር ለዜጐች ሊደረግላቸው የማገባውን ከሚዘረዝረው ሕግ ለይቶ ሊያውቅ ይገባል፡፡

የውል ሥረዓተ ሕግ በሚያዝዘው መሠረት ለደረሰ በደል ካሳ የተሠረቀ ንብረት ለባለቤቱ መመለስ እንዳለበት ይጠይቃል፡፡

ዘኬዎስ “ማንንም አታልዬ /አጭበርብሬ/ ከሆነ፣ አራት እጥፍ እመልሳለሁ” ሲል በመናገር ኢየሱስ ባረከው፡፡ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሌላውን ንብረት የወሰደ ስለ እነርሱ ሊካሱ ወይም አመጣጣኝ ዋጋ በገንዘብም ይሁን በዓይነት ሊተኩ፣ ንብረቶች ጠፍተው ከሆነ ደግሞ ባለቤቱ ከእነርሱ በሕጋዊ መንገድ ያገኝ የነበረውን ትርፍ ወይም ጥቅም ጭምር ሊሰጡት የግድ ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በሆነ መንገድ በሥርቆት የተሳተፉ ወይም እያወቁት ከእንደዚህ አይነት ድርጊት ያገኙ ለምሣሌ ያህል ድርጊቱ ይፈጸም ዘንድ ያዘዙ፣ የተባበሩ ወይም የተሰረቀውን ንብረት የተቀበሉ እንደ ኃላፊነታቸው መጠንና የተሰረቀው ነገር ባገኙት ድርሻ ልክ መመለስ አለባቸው፡፡

የቁማር ጨዋታዎች /የካርታ ጨዋታዎች፣ ወዘተ …/ ወይም ውርርዶች በራሳቸው ፍትሕን አይፃረሩም፡፡ ከሥነ ምግባር አንፃር ተቀባይነት የማይኖራቸው አንድ ሰው ለራሱና ለሌሎችም የሚያስፈልጉትን ነገሮች የማቅረብ አቅሙ ሲያሳጡት ነው፡፡ የቁማር ፍቅር የሱስ ቁራኛ የማድረግ ባሕርይ አለው፡፡ ተገቢ ያልሆኑ ውርርዶችና በጨዋታ ላይ ማጭበርበር ጉዳይ የደረሰበት ሰው ቀላልነቱን ካልተቀበለ በቀር ከባድ ነገር ነው፡፡

ሰባተኛው ትእዛዝ በማናቸውም ምክንያት ከራስ ወዳድነት ወይም ከፖለቲካዊ አመለካከት ከሚመነጭ፤ በንግድ መልክ ወይም በማን አለብኝነት አቋም የሰዎችን ግላዊ ክብር ችላ በማለት እንደ ሸቀጥ በመግዛት፣ በመሸጥና በመለወጥ ለባርነት የሚዳርጉ ተግባራትን ወይም ድርጅቶችን ይከለክላል፡፡ ሰዎችን በኃይል ወደ ምርት መሣሪያነት ወይም ወደ ትርፍ ማግኛነት ዝቅ በማድረግ ክብራቸውንና መሠረታዊ መብታቸውን የሚጻረር አመጽ በሰዎች ክብር ላይ የተቃጣ ኃጢአት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም “ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ባሪያ አይሆንህም፤ … በሥጋውም በጌታም ዘንድ ከባርያ የሚሻል የተወደደ ወንድም እንዴት አይሆንም” ፊሊሞና 1፡6 ሲል አንዱን ባለ ባሪያ ይመክራል፡፡

የፍጥረትን ሙላት ስለ ማክበር

ሰባተኛው ትእዛዝ የፍጥረት ሙላት እንዲከበር ያዝዛል፡፡ እንደ ተክሎችና እንደ ግዑዝ ነገሮች ሁሉ፣ እንስሳትም በተፈጥሮአቸው ላለፈው፣ ለወቅታዊና ለወደፊቱ የሰው ዘር የጋራ ጥቅም የተሰጡ ናቸው፡፡ በመላው ዓለም በሚገኙ ማዕድናት አትክልቶችና በእንስሳት ሀብቶች መጠቀም ከሥነ ምግባራዊ ግዴታዎች ተነጥሎ መታየት አይችልም፡፡ ፈጣሪ ሕይወት በሌላቸው ነገሮችና በሌሎች ሕይወት ባላቸው ነገሮች ላይ ለሰው የሰጠው የገዥነት ሥልጣን ፍጹም አይደለም፡፡ ለባልንጀራው ሕይወት የተሻለ መሆን እንዲሁም ለመጪዎቹ ትውልዶች ጭምር በማሰብ የተወሰነ ነው፤ የፍጥረት ምላት እንደተጠበቀ እንዲዘልቅ ሃይማኖታዊ አክብሮትንም ይጠይቃል፡፡

እንስሳት የእግዚአብሔር ፍጥረቶች ናቸው፡፡ እርሱ በመለኮታዊ ጥበቃው ይከልላቸዋል፡፡ እነሱ በሕልውናቸው ብቻ ያመሰግኑታል ያከብሩታልም፡፡ በዚህም ሰዎች ርኅራኄ በሰፈነበት መንፈስ ሊመለከቱአቸው ይገባል፡፡ እንደ እሲሲው ቅዱስ ፍራንሲስኮስ ወይም ቅዱስ ፊሊጵ ኔሪ ያሉ እንስሳትን እንዴት ባለ ፍቅር ይንከባከቡአቸው እንደነበር እናስታውስ፡፡

እግዚአብሔር በአምሳሉ ለፈጠራቸው ሰዎች እንስሳትን ይጠብቁአቸው ዘንድ በአደራ ሰጣቸው፡፡ በዚህም ምክንያት እንስሳት ለምግብነት ለልብስ መጠቀም ተገቢ ነው፡፡ ሰው እንስሳትን ለሥራና ለመዝናኛነት ሲል ለማዳ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ በእንስሳት ላይ የሚደረግ የሕክምናና የሣይንስ ጥናታዊ ሙከራ ተገቢ በሆነ መንገድ የሚከናወን እስከሆነ ድረስ እንዲሁም ሰብአዊ ሕይወትን የሚከባከብ ከሆነ ወይም እሱን ለማዳን አስተዋጽኦ የሚያበረክት ከሆነ በግብረገብነት በኩል ተቀባይነት አለው፡፡

እንስሳትን አለ አግባብ ማሰቃየት ወይም በግደየለሽነት እንዲሞቱ ማድረግ ሰብአዊ ክብር ይቃረናል፡፡ እንዲሁም የሰውን ችግር ለማቃለል ቅድሚያ መስጠት ሲገባ፣ ገንዘብን በእንስሳት ላይ ማዋል ተገቢ አይደለም ሰው እንስሳትን መውደድ ይችላል ሆኖም ለሰው ብቻ የሚገባን ፍቅር ለእንስሳት ሊሰጥ አይገባም፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት