ሁለተኛይቱ ትእዛዝ
- Category: ፲ቱ ትእዛዛት
- Published: Saturday, 05 March 2011 23:54
- Written by Super User
- Hits: 3132
- 05 Mar
ሁለተኛይቱ ትእዛዝ
የእግዚብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ
በቀድሞ ጊዜ ለነበሩ ሰዎች … “በውሸት አትማል” እንደተባለ ሰምታችኋል፡፡… “እኔ ግን እንዲህ እላችኋለሁ፣ ከቶ አትማሉ፡፡” ማቴ. 5 33-34
1. የጌታ ስም ቅዱስ ነው
ሁለተኛይቱ ትእዛዛ የጌታ ስም እንዲከበር ታዝዛለች፡፡ ይህች ትእዛዛ ልክ እንደ መጀመሪያይቱ ሁሉ በሃይማኖታዊ ምግባር ላይ የተመሠረተች ሲሆን በተለይ የተቀደሱ ነገሮችን በሚመለከት ጉዳይ የቋንቋ አጠቃቀማችን አግባብ ያለው መሆን እንዳለበት ታስገነዝባለች፡፡
በመገለጽ ውስጥ ከሰፈሩት ሁሉ አንድ ልዩ ቃል አለ፡- የተገለጠው የእግዚአብሔር ስም፡፡ እግዚአብሔር በእርሱ ለሚያምኑ ስሙን ይገልጥላቸዋል፣ እሱ ራሱን የሚገልጥላቸው በአካላዊው ምሥጢሩ ነው፡፡ ስምህን መስጠት የእምነትና የወዳጅነት ምልክት ነው፡፡ “የጌታ ስም ቅዱስ ነው”፡፡ በዚህ መሠረት ሰው የጌታን ስም አላግባብ ሊጠቀምበት አይገባውም፡፡ በሐሳቡ ሊያከብረው እንዲሁም አርምሞና ፍጹም ፍቅር በሰፈነበት መንፈስ ሊያመልከው ይገባል፡፡ ሊባርከው፤ ሊያከብረውና ሊቀድሰው ካልሆነም በቀር ከንግግሩ መሐል አያስገባውም፡፡
ለስም የሚሰጥ ክብር ለራሱ ለእግዚአብሔር ምሥጢርና እርሱ ለሚያጭረው የተቀደሰ እውነታ ሁሉ የሚሰጥ ክብር ነው፡፡ የተቀደሰውን ማክበር የሃይማኖታዊ ምግባር አካል ነው፡፡
ምእመናን ያላንዳች ፍርኃት እምነታቸውን በመግለጽ ስለአምላክ ስም መመስከር አለባቸው፡፡ የመስበክና ሃይማኖትን የማስተማር ተግባር ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሚቀርብ አምልኮና አክብሮት የዳበረ መሆን አለበት፡፡
ሁለተኛው ትእዛዛ የአምላክን ስም ማዋረድ ይከለክላል፤ ይህም ማለት የእግዚብሔርንና የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ብቻ ሳይሆን፣ የድንግል ማርያምን፣ የቅዱሳንንም ሁሉ ስሞች ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ እንዳይነሱ ይከለክላል፡፡
በእግዚአብሔር ስም ለሌሎች ቃል የተገባ ነገር መለኮታዊውን ክብር፤ ታማኝነትን፣ እውነተኛነትንና ሥልጣንን ሁሉ የሚመለከት ነው፡፡ በትክክልም መከበር አለበት፡፡ ለእነዚህ ቃል-ኪዳኖች ታማኝ አለመሆን በእግዚአብሔር ስም አለአግባብ እንደመጠቀም ይቆጠራል፡፡ በሌላ መንገድ ደግሞ እግዚአብሔርን ሐሰተኛ እንደማድረግ ነው፡፡
እግዚአብሔርን መስደብ በቀጥታ ሁለተኛውን ትእዛዛ ይቃወማል፡፡ የእግዚአብሔርን ስም ወይም ሥራን መንቀፍ ከሚንጸባረቅባቸው ሁኔታዎች ጥቂቶች ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት ናቸው፡፡
በውስጥህ ይሁን በውጭ በእግዚአብሔር ላይ የጥላቻ፣ የነቀፌታ ወይም የትዕቢት ቃላትን መሰንዘር፣ ስለ እግዚአብሔር መጥፎ ነገርን መናገር፣ በንግግር ውስጥ እርሱን አለማክበርና በስሙም አላግባብ መጠቀም፡፡ ይህ የጥላቻና የነቀፌታ ክልከላ በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በቅዱሳንና በቅዱሳን ነገሮች ላይ የሚነገረውን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ የእግዚአብሔርን ስም ሽፋን በማድረግ የወንጀል ሥራዎችን መፈጸም፣ ሕዝቦችን ወደ ባርነት ደረጃ ዝቅ ማድረግ፤ ሰዎችን ማሰቃየት ወይም መግደል እንዲሁም የእግዚአብሔርን ስም ከመስደብ ይቆጠራል፡፡ ወንጀልን ለመፈጸም በእግዚአብሔር ስም አለአግባብ መጠቀም ሌሎች ሰዎች ሃይማኖታቸውን እንዲክዱ ያነሳሳቸዋል፡፡ ይህ ነቀፌታ ለአምላክና ለተቀደሰው ስሙ የሚገባውን ክብር የሚቃረን ነው፡፡ ይህ ድርጊት በራሱ ከባድ ኃጢአት ነው፡፡
የእግዚአብሔር ስም አለአግባብ በመጠቀም የሚደረግ መሐላ ምንም እንኳ የመሳደብ ዓላማ ባይኖረውም ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አክብሮት ስለሚጐድለው ተገቢ አይደለም፡፡ ሁለተኛው ትእዛዝ የአምላክን ስም ለአስማት መጠቀም ይከለክላል፡፡
እግዚአብሔር ታላቅነቱንና ልዕልናውን ለማክበር ስሙ ከተጠራ “በእውነት” ስሙ ታላቅ ነው፡፡ እግዚአብሔር እሱን ላለማሳዘን በጥንቃቄና አክብሮት በሰፈነበት መንፈስ ከተጠራ ስሙ ቅድስ ነው፡፡
2. የአምላክን ስም በከንቱ ማንሳት /መጥራት/
ሁለተኛው ትእዛዝ በሐሰት መማልን ይከለክላል፡፡ ቃል የሚገባ ወይም የሚምል ሰው የሚለውን ወይም የሚፈጽመውን ነገር እውነት እንደሆነ ለማረጋገጥ ሲል ለምስክርነት የእግዚአብሔርን ስም ይጠራል፡፡ ማሐላ የአምላክን ስም በውስጡ ያካትታል፡፡ “አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፤ እርሱንም አምልክ፤ በስሙም ማል፡፡” ዘዳ. 6፡13
በሐሰት እንዲምል ሲጠየቅ አሉታዊ ምላሽ የሚሰጥ ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ የሚፈለግበትን ፈጸመ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ፈጣሪና ጌታ ስለሆነ የእውነት ሁሉ መለኪያ ነው፡፡ ከሰው አንደበት የሚወጣ ንግግር በባሕርይ እውነት ለሆነ እግዚአብሔር የሚስማማ ወይም የማይስማማ ሊሆን ይችላል፡፡ መሐላ እውነተኛና ሕጋዊ ከሆነ ሰብአዊ ንግግር ከእግዚአብሔር እውነት ጋር ያለውን ግንኙነት ያሳያል፡፡ በሐሰት የሚደረግ መሐላ የውሸት ምስክር ይሆንለት ዘንድ የእግዚአብሔርን ስም ይጠራል፡፡
ሰው በሐሰት የሚመሰክረው መሐላ ገብቶ የሚናገረውን ነገር እውነተነት የመጠበቅ አንዳች ሐሳብ ሳይኖረው ቃል ሲገባ ሣለ፣ ወይም ቃል ከገባ በኋላ መሐላውን ሲያፈርስ ነው፡፡ በሐሰት መመስከር ከሰው አንደበት ከሚወጣ ንግግር ሁሉ የእግዚብሔር አክብሮት የጐደለው ተግባር ነው፡፡ ክፉ ተግባር ለመፈጸም መሐላ መግባት የእግዚአብሔር ስም ቅድስና የሚቃረን ሥራ ነው፡፡
ኢየሱስ በተራራው ላይ ባደረገው ስብከት “… ደግሞ ለቀደሙት በውሸት አትማል፤ ነገር ግን መሐላዎችህን ለጌታ ስጥ፤ እንደተባለ ሰምታትኋል፡፡ እኔ ግን እንዲህ እላችኋለሁ፤ በጭራሽ አትማሉ፤ … ስለዚህ ቃላችሁ አዎ ወይም አይደለም ይሁን፡፡ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው፡፡” ማቴ. 5 33-34 በማለት ሁለተኛውን ትእዛዝ አብራርቶአል፡፡ ኢየሱስ ማናቸውም መሐላ እግዚአብሔርን የሚጠቅስ እንደሆነ በማመልከት የአምላክ ሕልውናና የእርሱ እውነት በንግግር መከበር እንዳለባቸው ያስተምራል፡፡ እግዚአብሔርን መጣራት አባባሎቻችን ሁሉ ከሚመሰክሩለት ወይም ከሚቀልዱበት ለሐልዎቱ ከሚኖር አክብሮት ያልተለየው ግንዛቤ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
የቤተክርስቲያን ትውፊት ከባድ እና ምክንያቶች በሚያጋጥሙበት ጊዜ /ለምሳሌ በፍርድ ቤት/ መሐላ ሊደረግ እንደሚችል ይህንንም ኢየሱስ በቃሉ እንዳልከለከለ ስለተገነዘበ የቅዱስ ጳውሎስን ፈለግ ይከተላል፡፡ እውነት፣ ፍርድና ጽድቅ በሚፈቅዱት መሠረት ካልሆነ በስተቀር መለኮታዊውን ስም ስለ እውነት ምሥክርነት መጥራት ማለትም መማል አይገባም፡፡
የመለኮታዊ ስም ቅድስና ለጥቃቅን ነገሮች ይሁን አልያም በእውነት ሳያስፈልገው ይህንን ለሚጠይቅ አንድ አካል እንደ ሁኔታው ማረጋገጫ እንደመስጠት ሊተረጐም የሚችል መሐላ እንዳንገባ አበክሮ ያሳስበናል፡፡
ከካቶሊክ ቤ/ያን ትምህርተ ክርስቶስ የተወሰደ