ልጅ የእግዚአብሔር ስጦታ ስለመሆኑ
- Category: ፲ቱ ትእዛዛት
- Published: Monday, 09 May 2011 22:25
- Written by Super User
- Hits: 4948
- 09 May
ልጅ የእግዚአብሔር ስጦታ ስለመሆኑ
ቅዱስ መጽሐፍና የቤተ ክርስቲያን ትውፊት በቤተሰብ ውስጥ የልጆች መበርከት የእግዚአብሔር ቡራኬና የወደጆች ለጋስነት ምልክት ነው ይላሉ፡፡
መሀን መሆናቸውን የተረዱ ባልና ሚስት እጅግ ይሳቀቃሉ፡፡ አብርሃምም “አቤት እግዚአብሔር ሆይ ምን ትሰጠኛለህ? እኔም ያለ ልጅ እሄዳለሁ” ዘፍ. 15፡2 ሲል ጠየቀው፡፡ ራሔልም ለባሏ ለያዕቆብ “ልጅ ስጠኝ፤ ይህስ ካልሆነ እሞታለሁ” ብላዋለች፡፡
ሰብአዊ መሀንነትን ለመቀነስ የሚከናወን የሳይንሳዊ ጥናት “ሰውን፣ የማይገሠሡ መብቶቹንና እንዲሁም በእግዚአብሔር ዕቅድና ፈቃድ መሠረት እውነተኛና ምሉዕ በጐነቱን የሚያገለግልና የሚያራምድ ከሆነ ተገቢ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል፡፡”
ከጥንዱ ውጭ ሌላን ሰው ጣልቃ በማስገባት /የወንድ ዘር ወይም ዕንቁላል፣ ሞግዚት ማህፀን/ የባልና የሚስትን መለያየት የሚያስከትሉ ቴክኒኮችን መጠቀም ሥነ ምግባር የጐደለው ሥራ ነው፡፡ እነዚህ ቴክኒኮች /ሰው ሰራሽ የማዳቀልና የጽንስ ሥራ/ ልጅ ከሚያውቃቸው በጋብቻ ኪዳን ከተጣመሩ አባትና እናት የመወለድ መብትን እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ እነዚህ ዘዴዎች ባልና ሚስት አንዱ በሌላው አማካይነት ብቻ “አባትና እናት የመሆን መብት” እንዳያገኙ ያደርጋል፡፡
ባልና ሚስቱን ብቻ የሚያሳትፉ ቴክኒኮች ምናልባት አለ መጠን አስከፊ ባይሆኑም በሥነ ምግባር በኩል ተቀባይነት የላቸውም፡፡ እነዚህ ዘዴዎች ሩካቤን ከማፍራት ሥራውን ይነጥሉታል፡፡ ልጁን ወደዚህ ዓለም የሚያመጣው ድርጊት ሁለት ሰዎች አርስ በእርስ በመሰጣጠት የሚያደርጉት መሆኑ ቀርቶ “የሽሉን ማንነትና ሕይወት ለሥነ-ሕይወት ጠበብትና ለሐኪሞች ኃላፊነት የሚተው በሰው ልጅ መገኛና ዕጣም ላይ የቴክኖሎጂን የበላይነት የሚያሰፍን ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት የበላይነት የሰፈነበት ግኑኝነት በራሱ ለወላጆችና ለልጆች ክብርና እኩልነት ተፃራሪ ነው፡፡” “በሥነ-ምግባራዊ ገጽታን አኳም ሲታይ ዘር ማፍራት የጋብቻዊው ፍቅር ውጤት ማለትም የጥንዶቹ አንድነት የተለየ እንቅስቃሴ ውጤት እንዲሆን ባልተፈለገ ጊዜ ፍጽምናውን ያጣል፡፡ ዘር ማፍራት ከሰው ክብር ጋር በተጣጣመ መልኩ እውን እንዲሆን ማድረግ የሚቻለው ለጋብቻዊ ሩካቤና ለሚሰጡት ትርጉሞች ትስስር በሚኖር አክብሮት ለሰው ልጅ አንድነት በሚሰጥ ክብር ብቻ ነው፡፡”
ልጅ አንድ ሰው ይገባኛል የሚለው ነገር ሳይሆን ስጦታ ነው፤ “የአንድ ጋብቻ የላቀ ስጦታ” ልጅ ነው፡፡ “የልጅ ባለቤትነት መብት” የሚለውን አባባል ሊጠቁም እንደሚችለው ልጅ እንደ ንብረት ሊቆጠር አይገባውም፡፡ በዚህ ዙሪያ ትክከለኛ መብቆች ያሉት ልጁ ብቻ ነው፤ ይህም “የወላጆቹ ልዩ የጋብቻዊ ሩካቤ ፍሬ” የመሆን መብትና “በተፀነሰበት ወቅት ጀምሮ እንደ ሰው የመከበር መብት” ነው፡፡
ሥጋዊ መሀንነት ፍጹም ክፋት አለመሆኑን ወንጌል ያመለክታል፡፡ ሕጋዊ የሕክምና አገልግሎቶችን ሁሉ ከሞከሩ በኋላም በመሐንነት የሚሰቃዩ ባልና ሚስት የመንፈሳዊ ልጆች ሁሉ ምንጭ ከሆነው ከጌታ መስቀል ጋር ራሳቸውን ማዋሐድ ይኖርባቸዋል፡፡ የተጣሉ ልጆችን በመሰብሰብ ወይም ለሌሎች አስፈላጊ አገልግሎቶችን በመስጠት ቸርነታቸውን መግለጽ ይችላል፡፡