ለሙታን ስለሚገባ ክብር
- Category: ፲ቱ ትእዛዛት
- Published: Saturday, 26 March 2011 23:49
- Written by Super User
- Hits: 4724
- 26 Mar
ለሙታን ስለሚገባ ክብር
በሞት አፋፍ ላይ የሚገኙ ሰዎች የመጨረሻ ሰዓት ሰብአዊ ክበርና ሰላም በሰፈነበት መንፈስ እንዲያሳልፉ ጥንቃቄና እንክብካቤ የሞላበት እርዳታ ሊደረግላቸው ይበገባል፡፡ ዘመዶቻቸውን በጸሎት ሊረዱአቸው ይገባል፡፡ እንዲሁም በተገቢው ጊዜ ከሕያው እግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት የሚያበቋቸውን ምሥጢራት እንዲቀበሉ ሕሙማንን ማዘጋጀት ይገባቸዋል፡፡
የሙታን አስከሬኖች በትንሣኤ ሙታን ላይ የተመሠረተ እምነትና ተስፋ በሰፈነበት መንፈስ በክበርና በፍቅር መያዝ ይገባቸዋል፡፡ የሙታን ቀብር ሥጋዊ የምሕረት ሥራ ነው፡፡ ይህ ሥራ የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደሶች የሆኑ የእግዚአብሔር ልጆችን ያከብራል፡፡
በአስክሬን ላይ የሚደረግ ምርመራ በሕግ ሲጠየቅና በሳይንሳዊ ጥናት ሲፈለግ ቢፈጸም በሥነ ምግባር ረገድ ይፈቀዳል፡፡ ከሞት በኋላ ያለ ክፍያ የሚለገስ የአካል ስጦታ ሕጋዊና አስመስጋኝ ሥራ ነው፡፡ የሙታን ትንሣኤ አለ የሚል እምነትን የመካድ መንፈስ ከሌለበት ቤተ ክርስቲያን የአስክሬን መቃጠልን አትቃወምም፡፡