ራስን ስለማጥፋትና በማይድን በሽታ ስለሚሰቃዩ ሰዎች ግድያ
- Category: ፲ቱ ትእዛዛት
- Published: Saturday, 26 March 2011 23:38
- Written by Super User
- Hits: 14487
- 26 Mar
የማይድን ሕማም የተያዙትን ሕልፈት ማቅለል (ዩቲኔዝያ)
የመኖር ተስፋቸው የመነመነ ወይም የተዳከሙ ልዩ ክብር ይገባቸዋል፡፡ ሕመምተኞች ወይም አካለ ሰንኩላን በተቻለ መጠን እንደሌሎች ሁሉ ሕይወታቸውን ይመሩ ዘንድ እርዳታ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡
ዓላማዎቹና የሚጠቀምባቸው ብልሃቆች የቱንም ዓይነት ይሁኑ ዩቲኔዝያ የታመመን፣ በሞት አፋፍ ላይ ያለንና አካለ ጐደሎ የሆነን ሰው ህይወት ለሕልፈት መዳረግ ነው፡፡ ይህ ድርጊት ከሥነ ምግባር አንፅር ተቀባይነት የለውም፡፡
ስለሆነም የሆነ ድርጊት ወይም ጥፋት በራሱ ወይም ይሁነኝ ተብሎ በታሰበ መንገድ ስቃይን ለማስቀረት ሲባል ሞትን የሚያስከትል ከሆነ ፍፃሜው ለሰብአዊዡ አካልና ለፈጣሪው ለሕያው አምላክ የተገባውን ክብር የሚፃረር አሰቃቂ ግድያ ነው፡፡ በቅንነት የተወሰደ ግድፈት ያለበት እርምጃም ቢሆን ባሕርዩን ስለማይለውጠው፣ ምንጊዜም ቢሆን ግድያው ሊከለከልና ሊቆም የሚገባው ድርጊት ነው፡፡
ከባድ፣ አደገኛ፣ ያልተለመደ ወይም ከሚጠበቀው ውጤት ተስፋ ጋር የማይጣጣም ሕክምናን ማቋረጥ ሕጋዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም “ከመጠን ያለፈ” ሕክምናን መቃወም ነው እዚህ ላይ ውጤቱ ሞት እንዲሆን የሚሻ የለም አርሱን ማገድ ያለመቻል የሚቀበሉት ሐቅ ነው፡፡ ሕመምተኛው ችሎታና ብቃት ያሉት ከሆነ እነዚህ ውሳኔዎች በእሱ መደረግ አለባቸው፤ ወይም እሱ ውሳኔዎችን ማድረግ የማይችል ከሆነ ደግሞ ሕግ በሚፈቀደው ደንብ ስለ ሕመምተኛው ለመናገር መብት ባላቸው፣ ከዚህም በላይ ሁልጊዜ በሕጋዊ መንገድ የሕመምተኛውን ፍላጐት በሚያከብሩ ሰዎች ውሳኔዎቹ መደረግ አለባቸው፡፡
ሞቱ የማይቀር መሆኑ ቢታወቅ እንኳ ለሕመምተኛው ሊደረግለት የሚገባው የተለመደ እንክብካቤ መቋረጥ ሕጋዊ ሊሆን አይችልም፡፡ ቀናቱ የሚያሳጥር እንኳ ቢሆንም በጣር ላይ ያለን ሰው ሕመም የሚያለሳልስ ማስታገሻ ሞት እንደፍፃሜም ይሁን እንደ ስልት ያልታሰበ ግና የሚታወቅና በአይቀሬነቱ የሚጠበቅ ተደርጐ በተወሰደበት አኳኋን ከተፈጸመ በሥነ-ምግባር ረገድ ሰብአዊ ክብርን የሚፃረር አይደለም፡፡
ራስን መግደል
ማንም ቢሆን ሕይወትን በሰጠው በእግዚአብሔር ፊት ለህይወቱ ተጠያቂነት አለበት፡፡ የህይወት ብቸኛው ባለቤትና ጌታ ሆኖ የሚኖረው እግዚአብሔር ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ክብርና ለነፍሳችን ድኅነት ብሐን ህይወትን በታላቅ ምስጋና የመቀበልበና በሚገባ የመጠበቅ ግዴታ አለብን፡፡ ለእግዚአብሔር በአደራ ለሰጠን ህይወት ጠባቂዎች እንጂ ባለቤቶች አይደለንም፡፡ ህይወትን ማጥፋት የእኛ ሥልጣን አይደለም፡፡
ራስን መግደል፤ ሰብአዊ ፍጡር ህይወቱን ለመጠበቅና ለማቆየት ያለውን ተፈጥሮአዊ ዝንባሌ ይቃረናል፡፡ ትክክለኛውን ራስን የማፍቀር ስሜትን ክፉኛ የሚቃረን ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩም የባልንጀራን ፍቅር ያደፈርሳል፤ ምክንያቱም ባለውለታችን ከሆኑት ከቤተሰብ፤ ከሕዝብና ከሌሎች ሰብአዊ ኅብረተሰቦች ጋር የሚኖረንን የአንድነት ትስስር ያለአግባብ ይበጥሳል፡፡ ራስን መግደል የሕያው እግዚአብሔርን ፍቅር ይቃረናል፡፡
ራስን መግደል፣ በተለይም ለወጣቶች አብነት ለመስጠት በሚል ሐሳብ የተደረገ ከሆነ እጅግ የከፋና አሳፋሪ ድርጊት ይሆናል፡፡ ራስን በመግደል ተግባር ላይ በሙሉ ፈቃደኝነት መተባበር ሥነ ምግባራዊ ሕግን የቃረናል፡፡ ከባድ የሥነ ልቦና ቀውሶች፣ ጭንቀት ወይም የመከራ ወይም የሥቃይ ፍራቻ ራስን የመግደል ኃላፊነትን ክብደት መቀነስ ይችላል፡፡
ራሳቸውን የገደሉ ሰዎች ዘላለማዊ ድኅነትን አያገኙም ብለን ተስፋ መቁረጠ የለብንም፡፡ ምክንያቱም አግዚአብሔር ለምሱ ብቻ በሚታወቁ ሁኔታዎች አማካየነት እነዚህ ሰዎች ደስ የሚሰኙበትን ንስሐ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሕይወታቸውን በገዛ እጃቸው ላሳለፉ ሰዎች ትጸልያለች፡፡