በጋብቻ ክብር ላይ የሚፈጸሙ በደሎች
- Category: ፲ቱ ትእዛዛት
- Published: Monday, 09 May 2011 22:27
- Written by Super User
- Hits: 4459
- 09 May
በጋብቻ ክብር ላይ የሚፈጸሙ በደሎች
ዝሙት ለጋብቻ ቃል ኪዳን አለመታመንን ያመለክታል፡፡ ከሁለቱ ተጋቢዎች ቢያንስ አንዱ ሌላ ካገባ ወይም ሩካቤ ሥጋ ከፈጸመ ለአጭር ጊዜም እንኳ ቢሆን እነርሱ ዝሙት ፈጽመዋል ማለት ነው፡፡ ዝሙት በምኞት የአፈጸመ ቢሆንም እንኳን በክርስቶስ ዘንድ የተወገዘ ነው፡፡ ከአሠርቱ ትዕዛዝ ስድስተኛ፣ እንደሁም አዲስ ኪዳን ዝሙትን በፍፁም ይከለክላል፡፡ ነቢያትም የዝሙትን እኩይነት ይናገራሉ፡፡
ዝሙት በደል ነው፡፡ ዝሙትን የሚፈጽም ግለሰብ በቃሉን ያፈርሳል፡፡ የቃል ኪዳኑ ምልክት የሆነውን የጋብቻ ትስስር ይጐዳል፤ የሌላኛውን ወገን መብቶት ይጥሳል፤ የተመሠረተበትን ውል በማፍረስ የጋብቻ ተቋምን ያዳክማል፡፡ የሰውን ልጅ መዋለድ በጐነትና የወላጆቻቸውን የጸና አንድነት የሚሻውን የልጆች ደህንነት ከአደጋ ላይ ይጥላል፡፡
ፍቺ
ጋብቻ የማይፈርስ እንዲሆን የፈቀደውን የፈጣሪን የመጀመሪያ ትልም ኢየሱስም አጸናው፡፡ እንዲሁም ቀስ በቀስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተብተው የነበሩ ማስተካከያዎችን ይሽራል፡፡ በተጠመቁት መካከል የተፈጸመ “ስምምነት የፀደቀና ፍጽምናን ያገኘ ጋብቻ በሞት ካልሆነ በስተቀር በማንኛውም ሰብአዊ ሥልጣን ወይም በሌላ ምክንያት አይፈርስም”
አንዳንድ ተገቢ ምክንያቶች ሲያጋጥሙ የቤተ ክረስቲያን ሕገ ቀኖና በሚበይነው መሠረት ባልና ሚስት የጋብቻን ኪዳን ሳያፈርሱ ተለያይተው መኖር ይችላሉ፡፡
በፍርድ ቤት መለያየት አንዳንድ ሕጋዊ መብቶች፣ የልጆችትም እንክብካቤ ወይም የውርስ ባለቤትነት የሚረጋግጡበት ብቸኛው አመቺ መንገድ እርሱ ብቻ ከሆነ፣ ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል፤ ሥነ ምግባራዊ ጥፋትም አይሆንም፡፡
ፍቺ በባሕርያአዊ ሕግ ላይ የሚፈጸም ከባድ በደል ነው፡፡ ፍቺ ባልና ሚስት ያላንዳች አስገዳጅ ሃይል እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ አብረው ለመኖር በስምምነት የገቡትን ውል ለማፍረሰ ይሞክራሉ፡፡ ፍቺ የጋብቻ ምስጢራታዊ ምልክት የሆነውን የደኀንነት ኪዳን ይጐዳል፡፡ አዲስ አንድነትን መዋዋል በሕግ ተቀባይነት ያለው እንኳ ቢሆን ስብራቱን ይበልጥ ያከብደዋል፡፡ በዚህ መሰረት ለሁለተኛ ጊዜ ያገባው ወገን ይፋ እና ዘለቄታዊነት ያለውን ዝሙት ይፈጽማል፡፡
“ከሕጋዊ ሚስቱ ተለይቶ ሌላ ሴት የሚያገባ ባል አመንዝራ ነው፤ ምክንያቱም ሌላ ሴት ከእርሱ ጋር ዝሙት እንድትፈጽም አድርጓልና፤ ከእርሱ ጋር የምትኖር ሴትም ዘማዊት ናት፣ ምክንያቱም የሌላን ባል ለራሷ አድርጋለችና፡፡”
ፍቺ ኢግብረገባዊ ነው፤ ምክንያቱም በቤተሰብና በኀብረተሰብ ውስጥ ቀውስን ያስከትላልና ነው፡፡ ይህ ቀውስ በተፈታው ወገን፣ በወላጆቻቸው መለያየት ምክንያት ሰቆቃ በደረሰባቸውና አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ በሚበታተኑት ልጆች ላይ በሚደርሰው ከፍተኛ ጉዳት እንዲሁም ተላላፊነት ባለው ውጤት የተነሳ ሕብረሰተቡን የሚያጠቃ ወረርሽኝ በመሆኑ አስከፊነቱ የጐላ ነው፡፡
ከመንግስት ሕግ አኳያ በሚተላለፍ ውሳኔ መሠረት ከተጋቢዎቹ አንዱ ወገን ንጹሕ ሆኖ ሳለ ስለፍቺ በሚበየነው ፍርድ ሊበደል ይችላል፡፡ ለቃል ኪዳናዊ ምስጢር በመታመን በቅን ልብ እየታለገ ሳለ ያለ አግባብ በተገለለ ተጋቢና በገዛ ከባድ ጥፋቱ በቤተ ክርስቲያን ቀኖና ሕጋዊነቱ የታወቀለትን ጋብቻ በሚያፈርስ ተጋቢ መካከል ከፍ ያለ ልዩነት አለ፡፡
በጋብቻዊ ክብር ላይ የሚፈጸሙ ሌሎች በደሎች
ወንጌልን ለመቀበል ባለው ፍላጐት አንድ ወይም ከዚያ በላይ ቁጥር ያላቸውንና የቀደመ የጋብቻ ሕይወቱን አብሯቸው ያሳለፈውን ሚስቶቹን ለመተው የማገደድ ሰው የሚያልፍበትን አስጨግቂ ሁኔታ መገንዘብ አይገድም፡፡ ነገር ግን ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ከሥነ ምግባራዊ ሕግ የሚስማማ አይደለም፡፡ “ጋብቻዊ ሱታፌ ብዙ ሚስቶችን ከማግባት ልማድ ጋር ፍጹም ተፃራሪ ነው፤ እንዲያውም ይህ ልማድ ከጥንት ጀምሮ በእግዚአብሔር የተገለጠውን ዕቅድ በቀጥታ ስለሚጥስ በጋብቻቸው ዘመን ልዩና የእነርሱ ብቻ በሆነ እርስ በርስ መሰጣጠት የሚኖር ባልና ሚስት ሰብአዊ ክብር ይቃረናል፡፡” ከዚህ በፊት ከብዙ ሚስቶቹ ጋር ይኖር የነበረ ባል አሁን ከእርሱ ተለይተው የሚገኙ ሚስቶቹንና ልጆቹን በሚመለከት ጉዳይ በሕግ ፊት ቃል የገባባቸውን ውሎች የማክበር ግዴታ አለበት፡፡
በሕግ የተከለከለ ሩካቤ /ኢንሴስት/ በሥጋ ዝምድና ያላቸው ወይም ከጋብቻ ዘመዶች የሆኑ ሰዎች፣ በሕግ የተከለከለውን በመጣስ በመካከላቸው የሚፈጽሙት የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ያመለክታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ይህን የተጠላ ሥራ ከባድ በደል እንደሆነ ያሳስባል፡፡ “በመካከላችሁ ዝሙት እንዳለ ይወራል፤ … ያባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና፤ … በጌታ በኢየሱስ ስም እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንደሰጥ ፍርዴ ነው፡፡” 1ቆሮ 5፡1፤4-5 ሲልም ያወግዛል፡፡ በሥጋ ዘመዶች መካከል የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ የቤተሰብ ግንኙነትን ያበላሻል፤ ሰውንም ወደ እንስሳነት ደረጃ ዝቅ ያደርጋል፡፡
ጐልማሶች በሞግዚትነት እንደጠብቋቸው በአደራ ከተሰጡአቸው ልጆች ወይም ከወጣቶች ጋር ያለአግባብ የሚፈጽሙት የግብር ሥጋ ግንኙነት በሥጋ ዘመዳሞች መካከል ከሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ይህ አስነዋሪ ድርጊት በወጣቶቹ አካልና ሥነ ምግባራዊ ማንነት ላይ የማይሽር በጠሳ ስለሚተው በደሉ እጥፍ ድርብ ይሆናል፡፡ እነዚህን ወጣቶች በአስተዳደግ የበደሉ ሰዎች በኃላፊነት መቀየቅ ይኖርባቸዋል፡፡
“ነፃ ሕብረት” እየተባለ በሚታወቀው ግኑኝነት አንድ ወንድና አንዲት ሴት ወሲብ ያለበትን ቅርበታቸውን ሕጋዊም ይሁን ማኀበራዊ ቅርፅ ሊሰጡት አይፈቅዱም፡፡
“ነፃ ሕብረት” የሚለው አባባል ስሕተት ነው፡፡ ጥንዱ አንዱ ለሌላው ቃል የማይገቡ ከሆነ፣ አንዱ በሌላው ላይ እምነት ካልኖረው፣ በራሱ ወይም በወደፊቱ ሕይወት ካልተማመነ ሕብረት የተሰኘው ቃል ምን ትርጉም ይሰጣል?
አባባሉ በርከት ያሉ ሁኔታዎች ያመለክታል፤ ዕቁባት ማስቀመጥን ሕጋዊ ጋብቻን አለመቀበልን፣ ወይም ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ኪዳንን ለመፈጸም አለመቻልን ይቀቁማል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ሁሉ በጋብቻ ክብር ላይ የሚፈጽሙ አመፃዎች ናቸው፡፡ የ”በተሰብን ምንነትም መርሶ ያጠፋሉ፡፡ የታማኝነትንም ስሜት ያዳክማሉ፡፡ ለሥነ ምግባራዊ ሕግ ተቃራኒ ናቸው፣ ሩካቤ ሥጋ ከጋብቻ ውጪ መፈጸም የለበትም፡፡ ከጋብቻ ውጭ የሚፈጸም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከባድ ኃጢአት ከመሆኑም በላይ ከምሥጢራታዊ ሱታፌም መከልከልን ያስከትላል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በደንብ ከመጋባታቸው በፊት “የሙከራ ጋብቻን የማድረግ መብት” ይገባል የሚሉ አንዳንድ ሰዎች ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ያለጊዜው የግብረ ሥጋን ግንኙነት በመፈጸም ላይ የሚገኙ ሰዎች ዓላማ የቱንም ያህል ጽኑ ቢሆን “በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ለሚኖረው የጋራ ቅንነትና መተማመን እንደዚህ ዓይነቱ ግንኙነት እምብዛም ዋስትና ሊሰጠው አይችልም፤ እንደያውም በየጊዜው ከሚለዋወጥ ምኞት ወይም ከድንገት ደራሽ ፍላጐት ሊጠብቀው አይችልም፡፡” ሥጋዊ ኀብረት ሕጋዊ የሚሆነው የሥነ ምግባር ደንብ በሚፈቅደው መሠረት በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ግልጽ የሆነ ሕይወት ሲመሠረት ብቻ ነው፡፡ ሰብአዊ ፍቅር የሙከራ ጋብቻን አይቀበልም፡፡ እርሱ የሚጠይቀው ሰዎች እርስ በእርስ የሚሰጣጡት ሁለንተናዊና የመጨረሻ ስጦታን ነው፡፡