በእውነት ላይ የሚቃጡ በደሎች
- Category: ፲ቱ ትእዛዛት
- Published: Saturday, 25 June 2011 08:51
- Written by Super User
- Hits: 2799
- 25 Jun
በእውነት ላይ የሚቃጡ በደሎች
የክርስቶስ ደቀ መዛሙሮች “ለእውነትም ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ለብሰዋል፡፡” “ውሸትን በማስወገድ” “ክፋትን ሁሉ፣ ተንኮልንም ሁሉ፣ ግብዝነትንም ቅንአትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግደዋል፡፡” ኤፌ. 4፡25፤ 1ጴጥ2፡1
በሐሰት መመስከርና ሐሰተኛ ምስክርነት፡- በአደባባይ በተነገረ ጊዜ እውነቱን የሚፃረር መግለጫ ልዩ ክብደት ይኖረዋል፡፡ ድርጊቱ በዳኛ ፊት ከተፈጸመ በሐሰት መመስከር ይሆናል፡፡ ሐሰት በመሐላ ከተፈጸመ ሐሰተኛ ምስክርነት ነው፡፡ እንደዚህ ያሉ ድርጊቶች ንጹሑን ለማስኮነን፣ ወንጀለኛን ንጹሕ ለማድረግ ወይም የተከሳሽን ቅጣት ለማክበድ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ፍትሐዊ አሰራርንና በዳኞች የሚተላለፉ ውሳኔዎችን ሚዛናዊነት ያዛባል፡፡
የሰዎችን መልካም ስም ማክበር በሰዎች ላይ ያለ አግባብ ጉዳትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ማናቸውም አስተያየቶችን መስጠትን ወይም መሰል ቃላት መጠቀምን ይከላከላል፡፡ አንድ ሰው በልቡም እንኳ ቢሆን የባልንጀራውን ሥነ-ምግባራዊ ስሕተት ያለ በቂ መረጃ እውነት ነው ብሎ በመቀበል በችኮላ ከፈረደ
ü በተጨባጭ ተቀባይነት ያለው ምክንያት ሳይኖረው የሌላውን ስሕተቶችና ድክመቶች ለማያውቅ ሰው በማሳወቅ ያንን ሰው ካሳነሰና፣
ü ከእውነት ተፃራሪ በሆኑ አስተያየቶች የሌሎችን ክብር ካጐደፈና እነርሱን በሚመለከት የተሳሳተ ግምት ይኖር ዘንድ ስም ለማጥፋት አስተዋጽኦ ካደረገ በደለኛ ነው፡፡
የችኮላ ፍርድን ለማስወገድ ማናቸውም ሰው የባልንጀራውን ሐሳቦች ቃላትና ሥራዎች በተቻለ መጠን በቀና መንገድ በመተርጐም ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፡፡
ማናቸውም መልካም ክርስቲያን የሌላን ሰው አባባል ከማውገዝ ይልቅ ተገቢ ትርጉም ለመስጠት ይበልጥ ፈቃደኛ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ሌላ ሰው አባባሉን እንዴት እንደሚገነዘበው ይጠይቃል፡፡ የኋለኛው አመለካከት መጥፎ ከሆነ ፊተኛው በፍቅር ያርመው፡፡ ይህም በቂ ካልሆነ፣ ለመዳን ይረዳው ዘንድ ሌላውን ሰው ወደ ትክክለኛው ትርጉም ለማምጣት ክርስቲያን ተስማሚ መንገዶችን ለማግኘት በተቻለው ሁሉ ጥረት ያድርግ፡፡
አሉባልታና ሐሜት የባልንጀራን ስምና ክብር ያጐድፋሉ፡፡ አክብሮት ለሰብአዊ ክብር የሚሰጥ ማሕበራዊ ምሥክርነት ነው፡፡ በዚህም መሰረት ማንኛውም ሰው ስሙና መልካም ዝናው የሚከበርበት ባሕርይአዊ መብት አለው፡፡ ስለዚህ አሉባልታና ሐሜት ለፍትሕና ለፍቅር ተቃራኒ ናቸው ማለት ነው፡፡
ሌሎች ሰዎች በክፉ ሥራዎችና በብልሹ ጠባይ ጸንተው እንዲኖሩ በሽንገላ ወይም ከመጠን በላይ በማሞገስ ወይም ከጠን በላይ በማስደሰት በቃላት ወይም በመንፈስ እነርሱን ማበረታታት ወይም ማጠግከር የተከለከለ ነው፡፡ ከመጠን በላይ በማሞገስ አንድን ሰው ለሌላው መጥፎ ምግባሮች ወይም ኃጢአቶች ግብረ አበር እንዲሆን መገፋፋት ከባድ ጥፋት ነው፡፡ ለሌላው ድጋፍ ለመስጠት ወየም ወዳጅ ለማፍራት መቀላመድ ተገቢ አይደለም፡፡ ማሞካሸት ለመግባባት፣ ክፋትን ለማራቅ፣ ፍላጐትን ለማርካት ወይም ተገቢ ጥቅምን ለማግኘት የሚደረግ ከሆነ፣ ቀላል ኃጢአት ነው፡፡
ፉከራ ወይም ጉራ መንዛት እውነትን የሚቃረን በደል ነው፡፡ በተንኮል መንፈስ የአንድ ሰውን ባሕርይ በአሰቂኝ መልክ በማሳየት ሰውን ለማንኳሰስ የሚደረግ ምጸትም እውትን ስለሚቃረን ከበደል ይቆጠራል፡፡
“ውሸት ሆን ተብሎ የማታለል የሚነገር ቅጥፈት ነው፡፡” ጌታ መዋሸት የዲያቢሎስ ሥራ መሆኑን ሲገልጽ፤ “እናንተ የአባታችሁ ከዲያቢሎስ ናቸው፤… በእርሱ እውነት የለም፡፡ ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፤ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና፡፡
መዋሸት በቀጥታ በእውነት ላይ የሚፈጸም የከፋ በደል ነው፡፡ መዋሸት ማለት እውነትን የማወቅ መብት ያለውን ሰው ለማሳሳት እውነትን ተቃርኖ መናገር ወይም የሆነ ድርጊት መፈጸም ነው፡፡ ውሸት ሰው ከእውነትና ከእውነትና ከባልንጀራው ጋር ያለውን ግንኙነት በመጉዳት ሰውና ቃሉ ከጌታ ጋር ያላቸውን መሠረታዊ ግኑኝነት በመጻረር ይበድላል፡፡
የውሸት ክብደት የሚለካው ባጣመመው የእውነት ባሕርይ መጠን በሁኔታዎቹ፣ በዋሺው አላማና ተበዳዮቹ በሚደርስባቸው ጉዳት መጠን ነው፡፡ ውሸት በራሱ ሲታይ ሳለ ቀላል ኃጢአት ቢሆንም ፍትሕንና ፍቅርን በጣሙን በጐዳ ጊዜ ከባድ ኃጢአት ይሆናል፡፡
ውሸት በባሕሪው ውጉዝ ነው፡፡ የንግግር ዋና አላማ የታወቀ እውነትን ለሌሎች በመናገር ሆን ብሎ ባልንጀራን ለማሳሳት የሚፈጸም ድርጊት ፍትሕና ፍቅርን ማዳከም ነው፡፡ የማታለሉ አላማ በነገሩ ተሳስተው መጥፎ መንገድን በተከተሉ ሰዎች ላይ እስከ ሞት አደጋ የሚደርስ ውጤቶችን የሚያስከትል ከሆነ የተጠያቂነቱ ደረጃ በይበልጥ ከፍ ያለ ይሆናል፡፡
እውነተኛነትን ስለሚቀናቀን ውሸት በግለሰብ ላይ የሚፈጸም አመጻ ነው፡፡ መዋሸት ለያንዳንዱ ፍርድና ውሳኔ አስፈላጊ የሆነውን የግለሰቡን የማወቅ ችሎታ ያናጋል፡፡ ውሸት በውስጡ ያለመግባባትንና የሚያስከትላቸውን ክፋቶች ዘር የያዘ ነው፡፡ መዋሸት ሕብረተሰብን ይጐዳል፡፡ መዋሸት በሰዎች መካከል የመተማመንን መንፈስ ያዳክማል፤ ማሕበራዊ ግንኙነቶችንም ይበጣጥሳል፡፡
ለጥፋተኛው ምህረት ቢደረግለትም እንኳን በፍትሕና በእውነት ላይ የተፈጸመ ማንኛውም በደል ካሳን በይፋ መክፈል የማያማች በሆነ በስውር መደረግ አለበት፡፡ አንድ ግለሰብ ስለተፈጸመበት በደል በቀጥታ ሊካስ ባይችል በልግሥና ስም ሥነ-ምግባራዊ እርካታን እንዲያገኝ መደረግ አለበት፡፡ ይህ ካሳን የመክፈል ግዴታ የሌላን ሰው መልካም ስም ማጉደፍንም ይመለከታል፡፡ ይህ ሥነ ምግባራዊ አንዳንዴም ቁሳዊ የሆነ ካሣ በደረሰው ጉዳት አንፃር ሊተመን ይገባዋል፡፡ ጉዳዩ የሕሊናም አስገዳጅነት አለበት፡፡