ሲቶ የመጽሐፍትና ንዋያተ ቅዱሳት መደብር ተመረቀ

1የሲታውያን ወንድሞች ገዳም የሆነው “ሲቶ የመጽሐፍትና ንዋየ ቅዱሳት መደብር” ዛሬ ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም. ተመረቀ።
በአዲስ አበባ ጉርድ ሾላ በሚገኘው በሲታውያን ወንድሞች ቅጥር ግቢ ውስጥ የመጽሐፍትና ንዋየ ቅዱሳት መደብር” ተመረቀ። በመርኃ ግብሩም መነኮሳት፣ ገዳማውያን እና ገዳማውያት፣ ወጣቶች እና ምእመናን በተገኙበት በቡራኬ ዛሬ ታህሳስ 20/2016 በይፋ ተከፍቷል። ክቡር አባ ጴጥሮስ በርጋ የአዲስ አበባ ካቶሊካዊ ሰበካ ሐዋርያዊ ጽ/ቤት ኃላፊ ከገዳሙ ኃላፊ አባ ዳንኤል ጌታቸው ጋር በመሆን በጋራ በቡራኬ እና በጸሎት መርቀው፤ ክቡር አባ ጴጥሮስም ይህ የመጽሐፍት መደብር ለብዙዎች በረከት እንደሚሆን ተናግረዋል።
እንዲሁም አባ ዳንኤል ጌታቸው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕት ካስተላለፉ በኋላ የረዳቸውን እግዚአብሔርን አመስግነው። የመጽሐፍት ቤቱን አላማ እና የአመሰራረቱን ሂደት አስመልክተው ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም የመጽሐፍት ቤቱን ስያሜ እንዲህ ብለው አብራርተዋል “ሲቶ” በፈረንሳይ ሀገር የሚገኝ የመጅመሪያ ሶስቱ የሲታውያን መስራች ቅዱሳን አባቶች ጫካውን መንጥረው የመጅመሪያውን ገዳም የመሰረቱበት ቦታ ሲሆን እንዲሁም ሲታውያን የሚለው የገዳማውያኑ መጠሪያ ከዚያ እንደተገኝ ገልጠዋል። ሲቶ ከተገደመበት ከ11ኛው ክ.ዘ. ጀምሮም የሲታውያን ገዳማት የጽሑፍ ሥራ መከናወኛ ዋነኛ ቦታ ሆነው እንደቀጠሉ አስረድተዋል። 
በመርኃ ግብሩ ላይ የህትመትን ጅማሬ በተመለከት ጥናታዊ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን በኢትዮጵያ ከመጀመሪያዎቹ የህትመት ተቋማት አንዱ የድሬዳዋው ቅዱስ አላዛር ካቶሊክ ማተሚያ ቤት መሆኑ ተገልጧል። በተጨማሪም የጥሞና ቅጥር እና ኑዛዜ የሚሉት መጽሐፎች በጥቂቱ ለታዳሚው በንባብ የቀረቡ ሲሆን፣ ስለመጽሐፍት ቤቱ ጠቃሚነት የተሳተፉት ካህናት፣ ደናግላን እና ምእመናኖች አስተያየታችውን እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ የመክፍቻ ፕሮግራም በመዝጊያ ጸሎት እና በመጽሐፍት መደብሩ ጉብኝት ተጠናቋል።
 311564108