Map St Joseph Cistercians

Top Panel

“ቅዱስ አባታችን፥ እንኳን ወደ ሐዋርያዊ መንበርዎ በጤና ተመለሱ!”

“ቅዱስ አባታችን፥ እንኳን ወደ ሐዋርያዊ መንበርዎ በጤና ተመለሱ!”

Pope to Vaticanርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሮም ከተማ ውስጥ በሚገኝ ጄሜሊ ሆስፒታል ለ38 ቀናት ሲታከሙ ከቆዩ በኋላ እሁድ መጋቢት 14/2017 ዓ. ም. ወደ ሐዋርያዊ መንበራቸው ተመልሰዋል። የቫቲካን መገናኛዎች ርዕሠ አንቀጽ ዝግጅት ክፍል ዳይሬክተር አቶ አንድሬያ ቶርኔሊ ቅዱስነታቸው ወደ ወደ ሐዋርያዊ መንበራቸው መመለሳቸውን በማስመልከት “ቅዱስ አባታችን፥ እንኳን ወደ ሐዋርያዊ መንበርዎ ተመለሱ!” በማለት የሚከተለውን ርዕሠ አንቀጽ አዘጋጅቷል።
 “የ 88 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ ለሆኑት እና በሳንባ ምች ሕመም ለሚሰቃዩት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሕክምና ያሳለፏቸው አምስት ሳምንታት ፈታኝ ጊዜያት ነበሩ። የሕክምና ውጤት ዘገባዎችም የሕመሙን ክብደት፣ ያጋጠሙትን ችግሮች ወይም የሕክምናውን ሂደት ውስብስብነት እንደ ቀላል አልተመለከቱትም።

ሆኖም በእነዚህ ሳምንታት ሁሉ ቅዱስነታቸው ከሕመማቸው እንዲያገግሙ በማለት ከዓለም ዙሪያ የሚቀርብ የጸሎት ድጋፎች አልተለያቸውም ነበር። የግል ጸሎቶች፣ ማኅበረሰቦች የሚቀርቧቸው ጸሎቶች፣ የመቁጠሪያ እና የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎቶች ይጠቀሳሉ። ከካቶሊካዊ ምዕመናን ብቻ ሳይሆኑ የሌሎች እምነቶች ተከታዮች እና ከማያምኑ ሰዎችም ጭምር መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸውል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት እሑድ መጋቢት 14/2017 ዓ. ም. በጄሜሊ ሆስፒታል ዙሪያ ለተገኙ ወደ ሶስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ያቀረቡት አጭር ሰላምታ እና ቡራኬ ለእነዚህ ሰዎች በሙሉ ነበር።

በእነዚህ ረጅም የመከራ ቀናት ውስጥ የሮም ሀገረ ስብከት ጳጳስ እና የመላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ከሆኑት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በመንፈስ በመተባበር በጸሎት አግዘናቸዋል። እሑድ መጋቢት 14/2017 ዓ. ም. እኩለ ቀን ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በደከመ ድምፃቸው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ምእመናን እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ሆነው በማኅበራዊ ሚዲያ አማካይነት የተገናኙትን ሕዝቦች ለጸሎታቸው አመስግነዋቸዋል። እሑድ መጋቢት 7/2017 ዓ. ም. ምሽት ለመጀመሪያ ጊዜ በሆስፒታሉ አሥረኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ጸሎት ቤት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መስዋዕተ ቅዳሴን ሲያሳርጉም ተመልክተናል።

ከሳምንታት ጭንቀት በኋላ ሕይወትን ለሚሰጥ እና በማንኛውም ጊዜ ወደ እራሱ ሊጠራን ለሚችል እግዚአብሔር በመገዛት ቅዱስነታቸው ዛሬ ተሽሎአቸው እንደገና በመካከላችን ሆነው ልናያቸው በቅተናል። ወደ ቫቲካን ሐዋርያዊ መንበራቸው በተመለሱባት ቀን ም ቡራኬያቸው በድጋሚ የቀብለናል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሆስፒታል ውስጥ ሆነው እያንዳንዱ የሕይወት ጊዜ ውድ እንደሆነ እና በማንኛውም ጊዜ ከእኛ ሊጠየቅ እንደሚችል አስታውሰውናል። ስቃይ እና ድካም ወንጌልን ለመመስከር  ዕድሎች ሊሆኑ እንደሚችሉ አሳይተውናል። ይህም ሰው ለሆነው አምላክ፣ ከእኛ ጋር መከራን ለተቀበለው እና በመስቀል ላይ ስቃይን የተቀበለው አምላክ ምስክርነት ነው።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከሆስፒታል ክፍላቸው ሆነው ይህን እውነት ስላካፈሉን እና ጦርነት ሞኝነት መሆኑን ስላሳሰቡን እናመሰግናለን። በተጨማሪም አዳዲስ ገዳይ መሣሪያዎችን ዓለምን ከማስታጠቅ ይልቅ ትጥቅ ማስፈታት እንደሚያስፈልግ እና በአስጊ ደረጃ ላይ ለሚገኝ ሰላም መጸለይ እንደሚገባ በማሳሰባቸው እናመሰግናቸዋለን።

ቅዱስ አባታችን እንኳን ወደ ሐዋርያዊ መንበርዎ ተመለሱ!”

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን 

https://www.vaticannews.va/am/pope/news/2025-03/pope-francis-discharged-from-hospital-welcome-thanks-editorial.html

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።