ክቡር ሞቱ ለጻዲቅ!
- Category: ዜናዎች
- Published: Monday, 21 April 2025 09:44
- Written by Samson
- Hits: 288
- 21 Apr
ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በተወለዱ በ88 ዓመታቸው በፋሲካ ማግስት ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ!
በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 3:45 የሐዋርያዊ ግምጃ ጠባቂ ካርዲናል ኬቨን ፋሬል በሚከተሉት ቃላት ከር.ሊ.ጳ. መኖርያ ሳንታ ማርታ የር.ሊ.ጳ. ፍራንቺስኮስን ዕረፍት ተናግረዋል።
"የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ! እጅግ ጥልቅ በሆነ ኀዘን የቅዱስ አባታችንን የር.ሊጳ. ፍራንቺስኮስ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን እንነግራችኋለን። ዛሬ ከጠዋት 1፡35 ሰዓት የሮም ጳጳስ ብጹዕ ወቅዱስ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቺስኮስ ሊቀ ጳጳስ ዘሮሜ ወደ ዘላለማዊ አባት ቤት ሄደዋል፤ ሕይወታቸው በሙሉ ለጌታ እና ለቤተክርስትያኑ የተሰዋ ነበረ። የወንጌልን እሴቶች፣ በተለይም ድሆችን እና የተረሱትን በሚመለከት፣ በታማኝነት፣ በጽናት እና ሁሉን አቀፍ በሆነ አባታዊ ፍቀር መኖር አስተምረውናል። እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያነት ለተኖረ ለአባታዊ አብነታቸው ያለንን ጥልቅ ምሥጋና እየገለጽን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቺስኮስን ነፍስ አንድም ሦስትም ለሆነው ለቅድስት ስላሴ ምሕረት ዐደራ እንሰጣለን”።
የኢትዮጵያ ሲታውያን መነኮሳን በር.ሊ.ጳ. ፍራንቺስኮስ ሕልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን እየገለጽን እግዚአብሔር የአባታችንን ነፍስ በዘላለማዊ እረፍት እንዲቀበል ከኲሏዊቷ ቤተ ክርስትያን ጋር በአንድ ድምጽ እንጸልያለን!
ጌታ ሆይ ለሞቱት ሰዎች የዘላለም ሕይወት ስጣቸው
የዘላለም ብርኀን አብራላቸው
በሰላም አሳርፋቸው
የሞቱት ሰዎች ነፍሳት በሰላም ይረፉ
አሜን!